New to site?


Login

Lost password? (X)

Already have an account?


Signup

(X)
Farooq

Archive by Category "Uncategorized"

HomeArchive by Category "Uncategorized"

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ከመጋቢት 11 እስከ ሰኔ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. በዓለም አቀፍ የሃዋላ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን ለማበረታታት ሲካሄድ የነበረው የሎተሪ ዕጣ ሽልማት እስከ ሐምሌ 11 ቀን 2010 ዓ/ም መራዘሙን እናሳውቃለን፡፡

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ከመጋቢት 11 እስከ ሰኔ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ከውጭ አገር በዓለም አቀፍ የሃዋላ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን ለማበረታት ለሦስተኛ ጊዜ የሎተሪ ዕጣ ሽልማት አዘጋጅቷል!!!

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ BUNNA INTERNATIONAL BANK S.C ለቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ እጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ ለመቀበል የወጣ ማስታወቂያ የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ የቦርድ አባላት ምርጫ የሚከናወነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር SBB/54/2012 እና SBB/62/2015 እንዲሁም በኩባንያው ባለአክሲዮኖች 8ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በጸደቀው የቦርድ አባላት ጥቆማና ምርጫ አፈጻጸም የአሰራር ደንብ […]

Bunna International Bank s.c new website is designed to maximize convenience and help us better meet the ever-changing needs of our customers. Discover the modern, action-based navigation that makes it easier than ever for customers and visitors to learn about Bunna Bank. The enhanced functionality of our website communicates our desire to provide up-to-date technology […]

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ዓመታዊ የሰራተኞች ቀን በዓል ጥር 19 ቀን 2010 ዓ.ም በያያ ቪሌጅ የመዝናኛ ማዕከል በደማቅ ሥነሥርዓት ተከበረ፡፡ ከአንድ ሺ በላይ በአዲስ አበባ የሚገኙ ቅርንጫፍ ሰራተኞች፣ የዋናው መስሪያ ቤት ሰራተኞች እና የክልል ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች በተገኙበት፤ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ታደሰ ጭንቅል እደገለጹት፣ የሰራተኞች ቀንን ስናከብር በሰራተኞች ዘንድ ህብረት እና መተዋወቅ የምንፈጥርበት […]

Employees of Bunna International Bank colorfully celebrated their annual staff day of January 27, 2018 at the YaYa Village Garde. Attended by more than a thousand employees from all branches in Addis Ababa, Head office organs and outlying Branch Managers the event was officially inaugurated by the opening remark of the CEO of the bank, […]

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክየባለራዕዮች ባንክ!!የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ዋና መስሪያ ቤት የህንፃ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ/center> የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ የዋናው መስሪያ ቤት የህንጻ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ቅዳሜ ህዳር 3 ቀን 2009 ዓ.ም የባንኩ የቦርድ አባላት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በደማቅ ስነስርዓት ተቀመጠ፡፡   በሜክሲኮ ከዋቢ ሸበሌ ሆቴል አጠገብ ከከተማ አስተዳደሩ በጨረታ ተወዳድሮ ባሸነፈውና በተረከበው […]

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ.Bunna International Bank S.C.ለሁለተኛ ጊዜ የሎተሪ ዕጣ እድለኞችቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ከጰጉሜ 1 ቀን እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ከውጭ አገር በዓለም አቀፍ የሃዋላ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን ለማበረታት ለሁለተኛ ጊዜ ባዘጋጀው የሎተሪ ዕጣ ሽልማት ሀሙስ የካቲት 8 ቀን 2010 ዓ.ም. በብሄራዊ ሎተሪ አዳራሽ በእድል አዳራሽ በሕዝብ ፊት ወጥቷል፡፡ የባለ ዕድለኞቹ ዝርዝር እንደሚከተሉት […]

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ
BUNNA INTERNATIONAL BANK S.C
ለቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

እጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ ለመቀበል የወጣ ማስታወቂያ

የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ የቦርድ አባላት ምርጫ የሚከናወነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር SBB/54/2012 እና SBB/62/2015 እንዲሁም በኩባንያው ባለአክሲዮኖች 8ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በጸደቀው የቦርድ አባላት ጥቆማና ምርጫ አፈጻጸም የአሰራር ደንብ መሠረት ነው፡፡ እነዚህን መመሪያዎች መሠረት በማድረግ በቀጣይ ባንኩን በቦርድ አባልነት የሚመሩ አባላትን ለማስመረጥ ጥቅምት 12 ቀን 2010 ዓ.ም በተካሄደው የባለአክሲዮኖች 8ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የቦርድ አባላት አስመራጭ ኮሚቴ መቋቋሙ ይታወሳል፡፡
በጠቅላላ ጉባኤው የተቋቋመው አስመራጭ ኮሚቴ እጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማዎችን ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

ባለአክሲዮኖች ብቁ ናቸው ብላችሁ የምታምኑባቸውን እጩ የቦርድ አባላት ለመጠቆም የሚያስችላችሁን የጥቆማ መሙያ ወይም ማስፈሪያ ቅጽ በቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ድረ ገጽ http://www.bunnabanksc.com ወይም የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ጎን ካለው ዳብር ሕንጻ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 በሚገኘው የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ ጽ/ቤት ወይም በባንኩ ቅርንጫፎች በአካል በመቅረብ ለጥቆማ መስጫ የተዘጋጀውን ቅጽ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን አስመራጭ ኮሚቴው ያሳውቃል፡፡
ስለሆነም የባንኩ ባለአክሲዮኖች ለኩባንያው ሁለንተናዊ እድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ይችላሉ ብለው የሚያምኑባቸውን ብቁ እጩዎችን በቅጹ ላይ በጥንቃቄ በመሙላት ከሚያዝያ 15 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 15 ቀን 2010 ድረስ እንዲጠቁሙ አስመራጭ ኮሚቴው በአክብሮት ይጋብዛል፡፡

ባለአክሲዮኖች የሞሉትን ቅጽ በቡና ኢንተርሽናል ባንክ አ.ማ ዋና መ/ቤት 4ኛ ፎቅ በዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 401 በአካል በመቅረብ መስጠት ወይም በባንኩ የፓ.ሣ.ቁጥር 1743 ኮድ 1110 ላይ በአደራ ደብዳቤ አድራሻውን ለቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ በማለት ወይም የተሞላውን ቅፅ ስካን በማድረግ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው በባንኩ ኢሜል bibnomination@bunnabanksc.com አያይዘዉ መላክ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ተጠቋሚ እጩ የቦርድ አባላት የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፤

 1. ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሆነ/ች እንዲሁም ዕድሜው/ዋ 30 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ/ች፤
 2. የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮን የሆነ/ች እና ቢመረጥ/ብትመረጥ በዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት ለመሥራት ፈቃደኛ የሆነ/ች፣
 3. ለቦታው ተስማሚ እና መጣኝ (Fit and Proper) የሆነ/ች እና የተስማሚ እና መጣኝ መገለጫ የሆነው እውቀት ቢያንስ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቀ/ች፣
 4. በቢዝነስ ማኔጅመንት፤ በባንክ ሥራ፤ በፋይናንስ፤ በአካውንቲንግ፤ በሕግ፣ በኦዲቲንግ፤ በኢኮኖሚክስ፤ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፤ በኢንቨስትመንት ማኔጅመንት የትምህርት መስክ የተመረቁና የጾታ ስብጥራቸውም ተመጣጣኝ ቢሆን ይመረጣል፣
 5. የቡና ኢንተርናሽናል ባንክም ሆነ የሌሎች ባንኮች ተቀጣሪ ሠራተኛ ያልሆነ/ነች፤ እንዲሁም የማንኛውም የፋይናንስ ተቋም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይም የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ያልሆነ/ነች፤
 6. ተጠቋሚው የሕግ ሰውነት ያለው ድርጅት ከሆነ ድርጅቱን ወክሎ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ለመሆን የሚወዳደረው የተፈጥሮ ሰው ማንነትና የትምህርት ደረጃ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ ነገሮች ሁሉ መጥቀስ፤
 7. የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ አባል ያልሆነ/ነች፤
 8. ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አክሲዮን ማህበርን ለስድስት ተከታታይ ዓመታት በቦርድ አባልነት አገልግለው ከቦርድ አባልነት የለቀቁ ከሆነ ከለቀቁበት ጊዜ ጀምሮ ስድስት ዓመታት የሆናቸው (የሞላቸው) መሆን አለበት፤
 9. በሕዝብ ዘንድ ተአማኒነት ያለው/ያላት እና የጸዳ የፋይናንስ አቋም ያለው/ያላት፤
 10. በሕዝብ ዘንድ መልካም ስነ ምግባር፣ ማህበራዊ ተቀባይነት ያለው/ያላት እና ሕግን በመተላለፍ በኢትዮጵያም ሆነ በውጭ ሀገራት በወንጀል በመከሰስ ተፈርዶበት/ባት የማያውቅ/ታውቅ፤
 11. ለመንግሥት ባለስልጣናት መረጃን በመከልከል፤ የተሳሳቱ የሂሳብ ወይም ሌሎች ሰነዶችን በመስጠት የተቆጣጣሪ አካላትን መመሪያዎች ባለመቀበል እና ባለመገዛት በመንግስት ባለስልጣናት አስተዳደራዊ የእርምት እርምጃዎች ተወስዶበት/ባት የማያውቅ/ታውቅ፤
 12. የንግድ ሥራን ከመተግበር ወይም ድርጅትን ከመምራት አኳያ በፍርድ ቤት የመክሰር ውሳኔ ያልተላለፈበት/ባት፣ ከታክስ እና ከባንክ ክፍያዎች ጋር በተያያዘ ግዴታዎቹን/ቿን በአግባቡ የተወጣ/ች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ ባለአክሲዮኖች በስልክ ቁጥር 0118722845 ወይም በ0903-200309/10 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፤
አስመራጭ ኮሚቴው ከሚያዝያ 15 ቀን 2010 ዓ.ም በፊትም ሆነ ከሐምሌ 15 ቀን 2010 ዓ.ም በኋላ የሚቀርቡ ጥቆማዎችን የማይቀበል መሆኑን ከወዲሁ ያሳስባል፡፡

የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ
የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት አስመራጭ ኮሚቴ

ፎርሙን ለማግኘት ከዚህ በታች የሚገኘውን ሊንክ ይጫኑ