×

Error

Cannot retrive forecast data in module "mod_sp_weather".

News

 ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ.

Bunna International Bank S.C.

የሎተሪ ዕጣ እድለኞች

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ከመጋቢት 18 ቀን እስከ ሀምሌ 17 ቀን 2009 ዓ.ም. ከውጭ አገር በዓለም አቀፍ የሀዋላ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን ለማበረታታት ባዘጋጀው የሎተሪ ዕጣ ሽልማት ዓርብ ነሀሴ 5 ቀን 2009 ዓ.ም. በብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር የእድል አዳራሽ በሕዝብ ፊት ወጥቷል፡፡ የባለዕድለኞቹ ዝርዝር እንደሚከተሉት ናቸው፡፡

ተ.ቁ

የዕጣ ቁጥር

የቅርንጫፉ ስም

የአሸናፊው ደንበኛ ስም

የሽልማቱ አይነት

1

0009229

ጅጅጋ

አብዱሰላም መሃመድ

ሊፋን የቤት አውቶሞቢል

2

0015438

ኮተቤ

ወ/ሮ ዘርፌ አዳፍሬ

የልብስ ማጠቢያ

3

0013217

ሜክሲኮ

አቶ ኢብራሂም አራርሶ

የልብስ ማጠቢያ

4

0008810

ይርጋዓለም

ወ/ሮ መዓዛ ስዩም

ስማርት ሞባይል ሳምሰንግ J76

5

0009035

ድሬዳዋ

ወ/ሮ ሃስነት አባስ

ስማርት ሞባይል ሳምሰንግ J76

6

0016590

ሾላ ገበያ

ወ/ሮ ቤተልሄም መኳንንት

ስማርት ሞባይል ሳምሰንግ J76

7

0009545

3 ቁጥር ማዞሪያ

ወ/ሮ ውድነሽ ወርዶፋ

ስማርት ሞባይል ሳምሰንግ J76

8

0015482

ዓቢይ

አቶ ሲሳይ መንግስቴ

ስማርት ሞባይል ሳምሰንግ J76

9

0004838

ጋምቤላ

አቶ ኮንግ ፓን ጆክ

የውሃ ማጣሪያ

10

0011204

መሳለሚያ

አቶ ቅጣው ገብሩ

የውሃ ማጣሪያ

11

0008203

ሆሳዕና

አቶ ዮሀንስ ገሚሶ

የውሃ ማጣሪያ

 

በመሆን የወጣ ሲሆን፤ለዕድለኛ ክቡራን ደንበኞቻችን እንኳን ደስ ያላችሁ እንላለን!!

 

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ

የባለራዕዮች ባንክ!!

  

 የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ዋና መስሪያ ቤት የህንፃ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ የዋናው መስሪያ ቤት የህንጻ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ቅዳሜ ህዳር 3 ቀን 2009 ዓ.ም የባንኩ የቦርድ አባላት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በደማቅ ስነስርዓት ተቀመጠ፡፡

በሜክሲኮ ከዋቢ ሸበሌ ሆቴል አጠገብ ከከተማ አስተዳደሩ በጨረታ ተወዳድሮ ባሸነፈውና በተረከበው 1043 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የመሰረት ድንጋዩን ያስቀመጡት የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ ኢንጅነር ጥበቡ እሸቴ ናቸው፡፡ እንደ ኢንጅነር ጥበቡ ገለፃ ግንባታው አስፈላጊው የአፈር ምርመራ በማድረግ እና የግንባታ አማካሪዎችና ባለሙያዎችን በመቅጠር በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ እንደሚገባ ባደረጉት ገለፃ መገንዘብ ተችሏል፡፡

በመቀጠልም የሚፈለገው ቅድመ ክንውን ከተፈጸመ በኋላ ባንኩ ለአካባቢው የሚመጥን እና ለስራው አስፈላጊ ይሆናል ብሎ የሚያምነውን ህንፃ በመገንባት ለደንበኞች ምቹ አገልግሎት ለመስጠት እንደተዘጋጀ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

አቶ አበባው ዘውዴ የባንኩ የህዝብ ግንኙነት ኮምኒኬሽን ዋና ክፍል ስራ አስኪያጅ ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ከተመሰረተ ሰባት ዓመት ያስቆጠረ ሆኖ እያለ፤ የራሱ የሆነ ህንጻ ባለመኖሩ በኪራይ ሲገለገል መቆየቱን አውስተው ላለፉት ሶስት ዓመታት የራሱን ህንፃ ለመገንባት ከግለሰቦች ከመንግስት መሬት ለማግኘት በድርድርና በግዢ ሂደት ከፍተኛ ጥረት መደረጉን አብራርተዋል፡፡

አቶ አበባው በተጨማሪም ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ በተረከበውና የፋይናንስ ተቋማት ግንባት ያካሂዱባቸዋል ተብለው በተለዩት የሜክሲኮ አካባቢ ቦታዎች ላይ የሚገነቡ የዝቅተኛ ፎቅ ግንባታ መጠን 19 ፎቅ እና ከዚያ በላይ መሆኑን ከከተማ አስተዳደሩ ያገኙትን መረጃ ዋቢ በማድረግ ገልጸዋል፡፡

                                                                           የቡና ኤቴኤም ካርድ

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ በነሐሴ 2008 ዓ.ም የኢትዮስዊችን በመቀላቀል የኤቴም ካርድ አገልግሎቱን ለደንበኞቹ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ሁሉም የቡና ካርድ የያዙ ደንበኞች በአገሪቱ በሚገኙት በየትኛውም ባንክ የኤቴኤም ማሽን ላይ የቡና ኤቴኤም ማሽንን ጨምሮ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ፡፡

የቀን ተቀን ግብይቶችን ቀላልና አስተማማኝ በሆነ መንገድ ማድረግ ይፈልጋሉ?

Ø  ለአጠቃቀም ቀላልና ምቹ

Ø  ከሳምንት እስከ ሳምንት የ24 ሰዓት አገልግሎት

Ø  በአካውንትዎ ላይ ያለዎት የገንዘብ መጠን ለማሳየት

Ø  ባስፈለገዎት ጊዜ በቀላሉ ገንዘብዎት ለማውጣት

Ø  በቀላሉ ገንዘብ ከአካውንት ወደ ሌላ አካውንት ለማስተላለፍ

Ø  ለወዳጅ ዘመድዎ ገንዘብ ለመላክ

ቀላልና ግልጽ ነው፤ የቡና ካርድ ለቀን ተቀን ግብይትዎ ያስፈልግዎታል!

  ዛሬውኑ የቡና ካርድዎን ይውሰዱ

የኤቴኤም የባንክ አገልግሎት 24 ሰዓት ብርዎን ለማንቀሳቀስ ያስችልዎታል፡፡ የቡና ባንክ ኤቴኤም ካርድን ከያዙ በመላው አገሪቱ በሚገኙ የማንኛውም ባንክ ኤቴኤም ማሽን መጠቀም ያስችሎዎታል፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ባንኮች በኢትዮ ስዊች የተሳሰሩ በመሆናቸው ነው፡፡

የኤቴኤም አገልግሎት ሚስጥራዊ፤ ፈጣንና ቀላል የባንክ አገልግሎት ነው፡፡

የባንክ አገልግሎት ፋላጎትዎን በቡና ኤቴኤም ካርድ አገልግሎት አስተማማኝ እና ቀልጣፋ ያድርጉ!

የቡና ካርድዎን ለመውሰድ

በአቅራቢያዎ ወደሚገኙ የቡና ባንክ ቅርንጫፎች ጎራ ብለው ለኤቴኤም ካርድ አገልግሎት የተዘጋጁ ፎርሞች በመሙላት በጣም በአጭር ጊዜ ውስጥ የቡና ካርድ ባለቤት መሆን ይችላሉ፡፡ ለአዲስ ደንበኞች የቡና ባንክ አካውንት መክፈት የሚያስፈልግ ሲሆን፤ የተዘጋጀውን ፎርም በመሙላት በቀላሉ የቡና ካርድ ባለቤት መሆን ይችላሉ፡፡

 ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ.

የባለራዕዮች ባንክ!!!

BIB's 2016/17 Fiscal year Annual Report

download the Amharic report
download the English report

BIB's 2015/16 Fiscal year Annual Report

download the Amharic report
download the English report

BIB's 2014/15 Fiscal year Annual Report

download the Amharic report
download the English report

BIB's 2013/14 Fiscal year Annual Report

download the Amharic report
download the English report

 

BIB has started extended working hour service

We are delighted to inform our esteemed customers that BIB has extended working hour service until 6:00 PM in all of the branches in Addis and in all the branches outside of Addis.

Exchange Rate

December 09, 2017 

 Currency

Buying

Selling

USD 27.1806 27.7242
GBP 36.2508 37.9858
CHF 27.3832
27.9309
SEK 3.2173 3.2816
DKK 4.3060
4.3921
DJF 0.1510 0.1540
INR 0.4209 0.429318
KSH 0.2636 0.2689
JPY 0.2411 0.245922
CAD 21.1901 21.6139
AUD 20.4398
20.8486
SAR 7.2474 6.3923
AED 7.3987 7.5467
ZAR
1.9979 2.0379
EUR 32.0432 32.6841
CNY 4.1058 4.1879