×

Error

Cannot retrive forecast data in module "mod_sp_weather".

Amharic News

ቡና ባንክ 7ኛውን የባለ አክሲዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አካሄደ

ባንኩ 250.4 ሚሊዮን ብር አጠቃላይ ትርፍ አስመዘገበ

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ.በ2015/16 የበጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም አስመዘገበ፤ ባንኩ ላሳየው ስኬታማ አፈጻጸም የብድር እና የተቀማጭ ሂሳብ ስራዎች ማደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደነበራቸው የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ ኢንጂነር ጥበቡ እሸቴ በበጀት ዘመኑ የተፈጸሙ ተግባራትን ሪፖርት ለጉባኤው ባቀረቡበት ወቅት አስታውቀዋል፡፡

ኢንጂነር ጥበቡ ህዳር 11 ቀን 2009 ዓ.ም. በሚሊኒየም አዳራሽ በተካሄደው የባለአክሲዮኖች 7ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለጹት ፤በተጠናቀቀው የ2015/16 የበጀት ዓመት ባንኩ ተከታታይነት ያለው አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉንና ባንኩ ያስመዘገበው ትርፍም ከባለፈው የበጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ38 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

ቡና ባንክ በ2014/15 የበጀት ዓመት  ባንኩ ከታክስ በፊት 182 ሚሊዮን ብር ትርፍ ያስመዘገበ ሲሆን፤ በ2015/16  ወደ 250.4 ሚሊዮን ብር ማሳደግ መቻሉን የቦርድ ሰብሳቢው ገልጸዋል፡፡

ባንኩ በበጀት ዓመቱም የ735 ሚሊዮን ብር ገቢ ያስመዘገበ ሲሆን፤ ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ52 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን አስታውቀዋል፡፡

የባንክ ስራን በአግባቡ ለማከናወን ወሳኝነት ያለውን የተቀማጭ ሂሳብ በማሳደግ ረገድ አበረታች ውጤት የታዬ ሲሆን፤ በበጀት ዘመኑ መጨረሻ ተቀማጭ ገንዘብ 5.4 ቢሊዮን ብር መድረሱንና፤ ይህም የ1.9 ቢሊዮን ብር ወይም የ54 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን አስረድተዋል፡፡

የባንኩ የብድር ክምችት 3.7 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፤ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር በንጽጽር ሲታይ የ51 በመቶ ጭማሪ ማስመዝገቡን በሪፖርታቸው አስታውቀዋል፡፡

በበጀት ዘመኑ የባንኩ ደንበኞች ቁጥር ወደ 175 ሺ ያሳደገ ሲሆን፤ ይህም በበጀት ዘመኑ ከተቀመጠው አዳዲስ ደንበኞችን የማፍራት እቅድ አንጻር ብልጫ አሳይቷል፡፡ የባንኩ የውጭ ምንዛሬ ግኝት የ23.1 በመቶ እድገት በማሳየት በበጀት ዘመኑ 98.5 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ማንቀሳቀስ ተችሎአል፡፡

የቡና ባንክ አጠቃላይ የሃብት መጠን የ53.2 በመቶ ወይም የ2.4 ቢሊዮን ብር ጭማሪ በማሳየት 6.8 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፤ ጠቅላላ ካፒታሉ  በ42 በመቶ በማሳደግ ወደ 961 ሚሊዮን ብር አድጓአል፡፡

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ባለፉት ሰባት ዓመታት ለበርካታ ኢትጵያዊያን የስራ እድል መፍጠር የቻለ ሲሆን፤ በ2015/16 የበጀት ዓመት መዝጊያ ላይ የቋሚ ሰራተኞቹን ቁጥር ከ1000 በላይ ማድረሱን እና በተመሳሳይም ለበርካታ ጊዜያዊና ኮንትራት ሰራተኞች የስራ እድል መፍጠር ችሎአል፡፡

የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ ኢንጂነር ጥበቡ እሸቴ በጉባኤው ወቅት እንዳሉት ፤በበጀት ዘመኑ ምንም እንኳን በንግዱ ዘርፍ መቀዛቀዝ ቢታይም፤ ባንኩ ስትራቴጅዎችን በመቀየስ የባንኩን አገልግሎት ተደራሽነት በማስፋፋት፣ የተቀማጭ ሂሳቡን በማሳደግና የብድር አቅርቦቱን በማስፋፋት ረገድ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡

 

የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ዋና መስሪያ ቤት የህንፃ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ የዋናው መስሪያ ቤት የህንጻ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ቅዳሜ ህዳር 3 ቀን 2009 ዓ.ም የባንኩ የቦርድ አባላት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በደማቅ ስነስርዓት ተቀመጠ፡፡

በሜክሲኮ ከዋቢ ሸበሌ ሆቴል አጠገብ ከከተማ አስተዳደሩ በጨረታ ተወዳድሮ ባሸነፈውና በተረከበው 1043 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የመሰረት ድንጋዩን ያስቀመጡት የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ ኢንጅነር ጥበቡ እሸቴ ናቸው፡፡ እንደ ኢንጅነር ጥበቡ ገለፃ ግንባታው አስፈላጊው የአፈር ምርመራ በማድረግ እና የግንባታ አማካሪዎችና ባለሙያዎችን በመቅጠር በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ እንደሚገባ ባደረጉት ገለፃ መገንዘብ ተችሏል፡፡

በመቀጠልም የሚፈለገው ቅድመ ክንውን ከተፈጸመ በኋላ ባንኩ ለአካባቢው የሚመጥን እና ለስራው አስፈላጊ ይሆናል ብሎ የሚያምነውን ህንፃ በመገንባት ለደንበኞች ምቹ አገልግሎት ለመስጠት እንደተዘጋጀ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

አቶ አበባው ዘውዴ የባንኩ የህዝብ ግንኙነት ኮምኒኬሽን ዋና ክፍል ስራ አስኪያጅ ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ከተመሰረተ ሰባት ዓመት ያስቆጠረ ሆኖ እያለ፤ የራሱ የሆነ ህንጻ ባለመኖሩ በኪራይ ሲገለገል መቆየቱን አውስተው ላለፉት ሶስት ዓመታት የራሱን ህንፃ ለመገንባት ከግለሰቦች ከመንግስት መሬት ለማግኘት በድርድርና በግዢ ሂደት ከፍተኛ ጥረት መደረጉን አብራርተዋል፡፡

አቶ አበባው በተጨማሪም ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ በተረከበውና የፋይናንስ ተቋማት ግንባት ያካሂዱባቸዋል ተብለው በተለዩት የሜክሲኮ አካባቢ ቦታዎች ላይ የሚገነቡ የዝቅተኛ ፎቅ ግንባታ መጠን 19 ፎቅ እና ከዚያ በላይ መሆኑን ከከተማ አስተዳደሩ ያገኙትን መረጃ ዋቢ በማድረግ ገልጸዋል፡፡ 

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ 143ኛ ቅርንጫፉን ከፈተ

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ 143ኛ ቅርንጫፉን ቡና እዳግሀሙስ ቅርንጫፍ በሚል ስያሜ ከፈተ፡፡

አዲሶቹ ቅርንጫፍ በኮር ባኪንግ የተሳሰሩ በመሆናቸው የተሟላ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

የቅርንጫፎቹ መከፈት የባንኩ ደንበኞች በአቅራቢያው የባንክ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. በቅርቡ ተጨማሪ አዳዲስ ቅርንጫፎችን በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች በመክፈት የተሟላ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት ወደ ደንበኞ በር ቀስ በቀስ እየቀረበ ይገኛል፡፡

 

•    ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ የሁለት ሚሊዮን ብር ቦንድ ገዛ
ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ  በራስ ሃይልና የፋይናንስ ምንጭ ለሚገነባው ለታላቁ ህዳሴ ግንባታ የሁለት ሚሊዮን ብር ቦንድ ግዢ በማድረግ ለሀገራዊ ልማት አጋርነቱን ማረጋገጡን የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ እሸቱ ፋንታዬ አስታውቀዋል፡፡
አቶ እሸቱ የቦንድ ቼኩን መጋቢት 10 ቀን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽ/ቤት ተገኝተው ለምክር ቤቱ ስራ አስፈፃሚ አባል ለአቶ አለማየሁ ተገኑ ካስረከቡ በኋላ እንደገለጹት፤ ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ወደ 12 ሺህ የሚጠጉ ባለ አክሲዮኖች የተቋቋመና ወደ ስራ ከገባም የአምስት ዓመት እድሜ ብቻ ያለው ባንክ ነው ብለዋል፡፡ይሁን እንጂ በኢንዱስትሪው እንዳለው ጀማሪነት ሳይሆን ስራውን ከጀመረበት ሰዓት አንስቶ በአገራዊና ክልላዊ የልማት ስራዎች በመሳተፍ አገራዊ ሃላፊነቱን በመወጣት ላይ የሚገኝ ህዝባዊ ባንክ ነው ሲሉ ዋና ስራ አስፈጻሚው አስታውቀዋል፡፡
በዚህም መሰረት የባንካችን ሰራተኞች እና የስራ አመራሮች የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በራሳችን ባለሙያዎች እና በራሳችን የፋይናንስ ምንጭ የሚገነባ መሆኑ በተበሰረበት ወቅት፤ የወር ደመወዛቸውን ለግድቡ ቦንድ በመግዛትና በንቃት በመሳተፍ አጋርነታቸውን በተግባር ያስመሰከሩ መሆናቸውን አቶ እሸቱ ገልጸዋል፡፡
በዛሬው ዕለትም የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድና የስራ አመራሩ በታላቁ ህዳሴ ግንባታና በዚህ ታላቅ የአገር ልማት ላይ የድርሻውን ለመወጣትና አሻራውን ለማስቀመጥ የሁለት ሚሊዮን ብር ቦንድ በመግዛት አጋርነቱን ለማሳየት መወሰኑን ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልጸው፤ በዚህ ብቻ ሳይበቃ የግድቡ ቦታ ድረስ በመሄድ የግንባታው ሂደት ምን እንደሚመስል በማየት በስራው ላይ የሚገኙትን ለማበረታታት እንዲሁም ግድቡን ላልተመለከቱ ወገኖች ምስክርነታቸውን ለመስጠት እቅድ መያዛቸውንም አስታውቀዋል፡፡
በመጨረሻም ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ በቀጣይም ከመንግስትም ሆነ ከህዝብ ለሚቀርብለት አገራዊ የልማት ስራዎች ጥያቄ ላይ በመሳተፍ አገራዊ ሃላፊነቱን የሚወጣና በህዝብ አጋርነቱ የሚቀጥል ህዝባዊ ባንክ መሆኑን አቶ እሸቱ አመልክተዋል፡፡
የውሃ መስኖ ኢነርጂ ሚኒስቴርና የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ብሄራዊ ምክር ቤት ስራ አስፈጻሚ አባል አቶ አለማየሁ ተገኑ የቦንድ ግዢ ርክክቡን ከፈጸሙ በኋላ ባደረጉት ንግግር፤ በአንድ አገር ልማት ላይ የባንኮች አገልግሎት ከፍተኛ መሆኑንና ለዚህም የህዳሴ ግድብ ግንባታ የቦንድ ግዢ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የህዳሴ ግድቡ ግንባታ ለባንኮች የፋይናንስ ስራ ያልተቋረጠ የሃይል አቅርቦት ሊኖራቸው እንደሚያስችላቸው አቶ አለማየሁ ገልጸው፤ ለዚህ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ላለውና ብሄራዊ ጥቅምን ለሚያስጠብቀው የህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡ በዚህ የቦንድ ግዢ ርክክብ ስነ-ስርዓት ላይ የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ማንደፍሮት በላይ፤ የስትራቴጂክ ዋና መኮንን አቶ ደመላሽ ደምሴ፤ የምርት ማሳደግ፤ ፈጠራና ገበያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በላይ ዘለቀ እና የህዝብ ግንኙነትና ኮምኒኬሽን ዋና ክፍል ስራ አስኪያጅ አቶ አበባው ዘውዴ መገኘታቸው ታውቋል፡፡

Exchange Rate

September 22 & 23, 2017 
Currency Buying Selling
USD 23.3658 23.8331
GBP 31.4831 32.1128
CHF 23.9821
24.4617
SEK 2.9200 2.9784
DKK 3.7361
3.8108
DJF 0.1298 0.1324
INR 0.3606 0.367812
KSH 0.2260 0.2305
JPY 0.2076 0.211752
CAD 18.8983 19.2763
AUD 18.5244
18.8949
SAR 6.2304 6.3550
AED 6.3610 6.4882
ZAR
1.7473 1.7822
EUR 28.7983 28.3543
CNY 3.5438 3.6147