New to site?


Login

Lost password? (X)

Already have an account?


Signup

(X)
Farooq

ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የቡና ባንክ አ.ማ ዓመታዊ የዕቅድ አፈጻጸም ስብሰባ ተጠናቀቀ

HomeNewsለሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የቡና ባንክ አ.ማ ዓመታዊ የዕቅድ አፈጻጸም ስብሰባ ተጠናቀቀ
25
Aug
ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የቡና ባንክ አ.ማ ዓመታዊ የዕቅድ አፈጻጸም ስብሰባ ተጠናቀቀ
  • Author
    Genet Fekade
  • Comments
    0 Comments
  • Category

==========

ከነሃሴ 17 ቀን እስከ ነሃሴ 19 ቀን 2013ዓ.ም ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የቡና ባንክ አ.ማ የ2020/21 በጀት ዓመት የስራ አመራር አባላት ዓመታዊ የዕቅድ አፈጻጸም ስብሰባ ተጠናቋል።

በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል ሲካሄድ የቆየው ይኸው ስብሰባ በባንኩ የበጀት አመት የዕቅድ አፈጻጸም እና የ2021/22 የበጀት አመት ዕቅዶች ላይ ሰፊ ውይይቶችን አካሂዷል።

በበጀት አመቱ ባንኩ የነበሩትን ጠንካራ የዕቅድ አፈጻጸሞችበመገምገም ለተገኙት አመርቂ ውጤቶች ዕውቅና የሰጠ ሲሆን የታዩ ክፍተቶችን በማሻሻል በያዝነው በጀት አመት የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ በሚቻልባቸው አካሄዶች ላይም ጥልቅ ውይይቶች ተደርግዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የባንኩ ስራ አመራር አባላት በባንኩ ተዘጋጅቶ በቀረበው የላቀ አፈጻጸም ድርጅታዊ ባህል (High performance organizational culture) ሰነድ ላይ ሃሳብ በመለዋወጥ ሰነዱን ከባንኩ እሴቶች ጋር በማዋሃድ ለተሻለ አፈጻጸም ያግዛል ባሏቸው አንኳር ነጥቦች ላይም ተወያይተዋል።

በተጨማሪም ባንኩ ለያዘው እቅድ መሳካት የሰራተኞችንና የስራ አመራሮችን የስራ ሂደት እና ውጤት በምዘና ላይ የተመረኮዘ ለማድረግ በተቀረጸው አዲሱ የስራ አፈጻጸም ምዘና ሰነድ ላይ በተደረገው ውይይት ለአፈጻጸም አመቺ ይሆናሉ ተብለው የተለዩ አሰራር ነጥቦች ተጠቁመዋል። የተጀመረውን የስራ አፈጻጸም ምዘና አሰራር በመያዝ ለዚሁ ዓላማ የተቀረጸው አዲሱ ሰነድ ወደስራ እንዲገባ በሚያስችሉ አሰራሮች ላይም አቅጣጫ ተሰጥቷል።

በስብሰባው መጨረሻ ቀን ላይ በሃገር አቀፍ ደረጃ ተቀርጾ ወደአፈጻጸም በወረደው ዲጆታል ኢትዮጵያ 2025/ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራተጂ ሰነድ ላይ ከኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በመጡ ሶስት ባለሙያዎች ገለጻ ና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ከገለጻው በኋላም በሰነዱ አጠቃላይ ሃሳቦችና ፣በተለይም ስትራተጂው በባንክና ፋይናንስ ኢንደስትሪ የስራ አፈጻጸምና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ባለው ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ አንደምታ ዙሪያ እንዲሁም ከዲጂታላይዜሽን ጋር ተያይዘው በሚመጡ የሳይበር ሴኪዩሪቲ ስጋቶች እና መልካም እድሎች ላይ የስራ አመራር አባላቱና ባለሙያዎቹ መካከል ጥልቅ ውይይቶች ተካሂደው ስብሰባው ተጠናቋል።

በስብሰባው ላይ የባንኩን ዋና ስራ አስፈጻሚ ጨምሮ ሁሉም ቺፍ ኦፊሰሮች፣ ዳይሬክተሮች እና የዲስትሪክት ስራ አስኪያጆች ተካፋይ ሆነዋል።

Tags:

    Bunna Bank