New to site?


Login

Lost password? (X)

Already have an account?


Signup

(X)
Farooq

ሰባተኛው ዙር የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ የሎተሪ ዕጣ ወጣ

HomeNewsሰባተኛው ዙር የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ የሎተሪ ዕጣ ወጣ
28
Aug
ሰባተኛው ዙር የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ የሎተሪ ዕጣ ወጣ
  • Author
    Genet Fekade
  • Comments
    0 Comments
  • Category

የቤት መኪና አሸናፊው የ ገርጂ ቅርንጫፍ ደንበኛ ሆኗል

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ለሰባተኛ ጊዜ ያዘጋጀው የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ የሎተሪ እጣ ነሃሴ 21 ቀን 2012 ዓ.ም በብሄራዊ ሎተሪ በዕድል አዳራሽ በህዝብ ፊት በይፋ ወጥቷል፡፡

በሰባተኛው ዙር የውጭ ምንዛሬ ማስገኛ ፕሮሞሽን ደንበኞች ከውጭ ሀገር ከወዳጅ ዘመዶቻቸው በተለያዩ ገንዘብ ማስተላለፊያ ድርጅቶች በኩል ገንዘብ ሲላክላቸውና በቡና ባንክ በኩል ሲቀበሉ እንዲሁም የውጭ አገር ገንዘብ በቡና ባንክ ቅርንጫፎች ሲመነዝሩ እድለኛ የሚሆኑበት የሎተሪ መርሃ ግብር ባንኩ በየአመቱ ከሚያካሂዳቸው የሴልስ ፕሮሞሽን መርሀግብሮች መካከል አንዱ ነው፡፡

የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ስትራቴጂ ዋና ኦፊሰር አቶ መንክር ሃይሉ የእጣ አወጣጥ ስነስርአቱን በይፋ ሲከፍቱ እንደገለጹት ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ላለፉት አስር ስኬታማ አመታት በባንክ አገልግሎት ማለትም በቁጠባ፤ በብድር ፋይናንስ እንዲሁም በአለም አቀፍ የባንክ አገልግሎት ህብረተሰቡን በማገልገል ተመራጭና ተወዳጅ ለመሆን የበቃ ህዝባዊ ባንክ መሆኑንና ባንኩ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል አንዱ በሆነው የውጭ ምንዛሪ ማስገኘት ስራ ላይ ሲሰራ መቆየቱን አስረድተዋል፡፡

በተለይም ከቅርብ አመታት ወዲህ በአገሪቱ የተፈጠረውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለማሻሻል ቡና ባንክ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ መንክር፤ባንኩ የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ መርሃግብሩ ከውጭ ሀገር ያለው ዲያስፖራ ወደ ሀገር ውስጥ የሚልከውን ገንዘብ ህጋዊ የባንክ መስመርን እንዲከተል ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ማድረጉን፤ በጥቁር ገበያ የሚደረገውን የገንዘብ ግብይት ወደ ባንክ እንዲመጣ ከማድረግና በሰውና በዘመድ የሚላክበት የገንዘብ አላላክ በተቀባዩ ዘንድ የሚፈጥረውን ተግዳሮት ለመቅረፍና የባንክ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥረት በማድረግ ከፍተኛ እገዛ አድርጓል ብለዋል፡፡

ባንኩ ባለፉት ሰባት ዙሮች ባካሄደው የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ መርሀግብር ካገኛቸው ልምዶች በመነሳት የባንኩን ደንበኞች የበለጠ ለማበረታታትና ለማትጋት ስምንተኛውን ዙር የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ ፕሮሞሽን መርሃግብሩን በቅርቡ እንደሚጀምር አስታውቀዋል፡፡

Tags:

    Bunna Bank