Branch/ATM Locator   |

Announcement    |

FAQs   |

+25111150861    |

ቡና በንክ 11ኛውን ዙር የውጭ ምንዛሪ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ ይሸለሙ መርሃግብር ጀመረ

ደንበኞች የውጭ ምንዛሪ ከወዳጅ ዘመድ ሲላክላቸው እና በቡና ባንክ በኩል ሲቀበሉ እና ሲመነዝሩ ተሸላሚ የሚሆኑበት የ11ኛው ዙር በቡና ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ መርሃግብር ተጀምሯል፡፡

ላለፉት 10 ጊዜያት ያህል ብዙዎችን በርካታ ሽልማቶች የሸለመው ቡና ባንክ የ11ኛውን ዙር የውጭ ምንዛሪ ይቀበሉ፣ይመንዝሩ፣ይሸለሙ መርሃግብር ተሳታፊ የሆኑ ደንበኞቹንም መኪና እና ሌሎች አጓጊ ሽልማቶች ሊሸልም ተዘጋጅቷል።

በቡና ባንክ ደንበኞች ከውጭ አገር ወዳጅ ዘመድ የሚላክላቸውን ገንዘብ ሲቀበሉ እና ሲመነዝሩ እድለኛ ሊያደርጋቸው የሚችል የሎተሪ ቁጥር ወዲያውኑ በእጅ ስልካቸው ያደርሳቸዋል፣ በተጨማሪም  የሞባይል ካርድ ስጦታ ይሰጣቸዋል፡፡

ባንኩ የ2022 ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች፣ ዘመናዊ ማቀዝቀዣዎች፣ የውሃ ማጣሪያዎች እና ስማርት የሞባይል ስልኮችን ለመርሃ ግብሩ አሸናፊዎች አዘጋጅቷል፡፡