New to site?


Login

Lost password? (X)

Already have an account?


Signup

(X)
Farooq

ቡና ባንክና ከፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ በውልክና ዶክመንቶች የሚፈጸሙ የሰነድ ማጭበርብሮችን ለመከላከል የሚረዳ የጋራ መግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

HomeNewsቡና ባንክና ከፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ በውልክና ዶክመንቶች የሚፈጸሙ የሰነድ ማጭበርብሮችን ለመከላከል የሚረዳ የጋራ መግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ
16
Aug
ቡና ባንክና ከፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ በውልክና ዶክመንቶች የሚፈጸሙ የሰነድ ማጭበርብሮችን ለመከላከል የሚረዳ የጋራ መግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ
 • Author
  Genet Fekade
 • Comments
  0 Comments
 • Category

• ከግል ባንኮች ውስጥ ስምምነቱን በመፈረም የመጀመሪያው ነው

ቡና ባንክ በሃገራችን እየተስፋፋ የመጣውንና በተለይ ባንኮችን ተጋላጭ የሚያደርገውን በውክልና ሰነዶች የማጭበርበር ወንጀል ለመከላከል የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ከፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ጋር ዛሬ ነሃሴ ቀን 2013 ዓ.ም ተፈራርሟል።

በቡና ባንክ አ.ማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ እና በፌዴራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ የተፈረመው ይኸው ስምምነት ባንኩ የሚገጥሙትን የማጭበርበር ወንጀሎች ከመከላከል ባሻገር ከኤጀንሲው ቀልጣፋና ጊዜ ቆጣቢ የውክልና ዶክመንት ማረጋገጥ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን ያስችለዋል ተብሏል።

በቡና ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት በተካሄደው በዚሁ የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ ስነስርዓት ላይ የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ ባደረጉት ንግግር ቡና ባንክ የመግባቢያ ሰነዱን በመፈረም ከግል ባንክች ቀዳሚ በመሆኑ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ይህም ባንኩ ለደንበኞቹ የተቀላጠፈ አገልግሎት ከመስጠት ባሻገር ደንበኞቹን በውክልና ሰነድ ከሚከሰት ማጭበርበር ለመጠበቅ ዋስትና ይሆነዋል ብለዋል።

ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር አንድ ግለሰብ የባንኩን ደንበኛ ሂሳብ ለማንቀሳቀስ የውክልና ሰነድ ይዞ ሲመጣ የሰነዱ ትክክለኝነት የሚጣራበት ሂደት ረጅም ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት አዳጋች እንደነበር አቶ ሙሉጌታ ተናግረዋል። ከአዲሱ አሰራር ጋር ሲነጻጸርም የቀደመው ዶክመንት የማጣራት ሂደት የማጭበርበር ወንጀልን በመከላከል በኩልም ውስንነት እንደነበረውም ነው የገለጹት። ኤጀንሲው የዘረጋው አዲስ አሰራር እነዚህን ሁሉ ችግሮች በማቃለል የባንኩን አገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋና ከወንጀል ስጋት ነጻ የሚያደርግ በመሆኑ ባንኩ ስምምነቱን በመፈረሙ ደስተኛ መሆኑንም ነው አቶ ሙሉጌታ የተናገሩት።

የፌዴራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ በበኩላቸው ኤጀንሲው ጊዜ ቆጣቢና በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራርን ተግባራዊ ለማድረግ ከተጓዘባቸው ርቀቶች አንዱ የውክልና ሰነድ ትክክለኝነትን ለማረጋገጥ የዘረጋው አዲስ አሰራር ቀዳሚ ተጠቃሽ መሆኑን ተናግረዋል።ይህ አሰራር በተለይ ባንኮችን በእጅጉ ተጠቃሚ እንደሚያደርጋቸውና በውክልና ሰነድ ማጭበርበር የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመቆጣጠር እንደሚያስችላቸው ነው ዋና ዳይሬክተሩ የገለጹት።

አቶ ሙሉቀን እንዳሉት ኤጀንሲው ከባንኮች የሚደርሱትን የውክልና ሰነዶች ትክክለኝነት ለማረጋገጥ ከዋናው ሰነድ ጋር በማመሳከር ከሚሰጠው ምስክርነት ውጪ ውክልናው ስለመሻር አለመሻሩ ማረጋገጥ የሚችልበት አሰራር አልነበረውም። በዚህ ሳቢያም በተሻሩ ውክልናዎች በርካታ የማጭበርበር ወንጀሎች ሲፈጸሙ ቆይተዋል ብለዋል። አዲሱ አሰራር ግን አስትማማኝ ከመሆኑ በተጨማሪ ባንኮች ወደኤጀንሲው ቅርንጫፎች መምጣት ሳያስፈልጋቸው በተዘረጋው ሲስተም መሰረት ባሉበት ሆነው የውክልና ዶክመንቱን ትክክለኝነት በማረጋገጥ ለደንበኞቻቸው ቀልጣፋ መስተንግዶ መስጠት እንደሚያስችላቸው ገልጸዋል።

እንደዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ ኤጀንሲው ባሉት 14 ቅርንጫፎች በቀን ከሚያስተናግዳቸው 6ሺህ 100 የአገልግሎት ጥያቄዎች ውስጥ 52 በመቶው ከውክልና ሰነድ ጋር የተያያዘ ነው። ኤጀንሲው ከባንኮች የሚቀርቡለትን የሰነድ ማረጋገጫ ጥያቄዎች ኮፒ በማመሳከር ብቻ ምላሽ ይሰጥ እንደነበርም አስታውሰዋል። ያም ሆኖ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ በኤጀንሲው የተረጋገጠ ውክልና በማንኛውም ሁኔታ ተሽሮ ቢሆን የሚያረጋግጥበት አሰራር ባለመዘርጋቱ ሳቢያ በተሻሩ ውክልናዎች በርካታ የማጭበርበር ስራዎች ይፈጸሙ እንደነበርም አስታውሰዋል። ይህ ክፍተት በተለይ ባንኮችን ተጠቂ አድርጓቸው እንደነበር የተናገሩት አቶ ሙሉቀን አዲሱ አሰራር ይህንን ችግር በመቅረፍ ወንጀልን የሚቀንስና ባንኮችም ለደንበኞቻቸው ቀልጣፋና ደህንንቱ የተጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችላቸው መሆኑንም ተናግረዋል።

Tags:

         ቡና ባንክ .

        BUNNA BANK S.C

  ለቡና ባንክ አ.ማ ባለአክስዮኖች በሙሉ

  ዕጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ ለመቀበል ተሻሽሎ የወጣ ማስታወቂያ

  የቡና ባንክ አ.ማ የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ታህሳስ 11 ቀን 2013 ዓ.ም ባካሄደው 11ኛ መደበኛ ስብሰባው ያቋቋመው “የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማና አስመራጭ ኮሚቴ” ከሐምሌ 01 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የዕጩ ጥቆማዎችን በመቀበል ላይ የሚገኝ ሲሆን የቦርድ አባላትን ለመጠቆም የሚያስችለውን የጥቆማ መሙያ ቅጽ ከቡና ባንክ አ.ማ ድረ-ገጽ https://www.bunnabanksc.com ወይም አዲስ አበባ ቦሌ መንገድ ሩዋንዳ መታጠፊያ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 8ኛ ፎቅ ከሚገኘው የኮሚቴው ጽ/ቤት ወይም ከባንኩ ቅርንጫፎች ማግኘት ይቻላል፡፡

  ስለሆነም ባለአክስዮኖች ለዳይሬክተሮች የቦርድ አባልነት ብቁ የሆኑትን ፤ ለባንኩ ሁለንተናዊ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከት የሚችሉትን እና ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉትን ዕጩዎች በቅፁ ላይ በጥንቃቄ በመሙላት እስከ ጥቅምት 01 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ብቻ ከላይ በተገለፀው የኮሚቴው ጽ/ቤት በአካል በማቅረብ ወይም አድራሻውን ለቡና ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማና አስመራጭ ኮሚቴ በማለት በባንኩ የፓ.ሣ.ቁጥር 1743 ኮድ 1110 በአደራ ደብዳቤ በመላክ ወይም የተሞላውን ቅጽ ስካን በማድረግ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው በባንኩ ኢሜይል bibnomination@bunnabanksc.com አያይዛችሁ በመላክ ለባንኩ ዕድገት የበኩላችሁን አስተዋፅኦ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

  ተጠቋሚ ዕጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡-

  1. በዜግነት ኢትዮጵያዊ/ት ወይም የውጭ ሀገር ዜግነት ካለው/ላት በትውልድ ኢትዮጵያዊ/ት የሆነ/ች፤
  2. ዕድሜው/ዋ 30 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የሆነ/ች፤
  3. የዳይሬክተሮች የቦርድ አባል ሆኖ ቢመረጥ /ሆና ብትመረጥ ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ/ች፤
  4. ከታወቀ የከፍተኛ የትምህርት ተቋም ቢያንስ በመጀመሪያ ዲግሪ ወይም በአቻ የትምህርት ደረጃ የተመረቀ/ች፤
  5. የዳይሬክተሮች የቦርድ አባላት ስብስብ በባንክ ስራ፣ በፋይናንስ፣ በአካውንቲንግ፣ በማኔጅመንት፣ በኢኮኖሚክስ፣ በሕግ፣ በቢዝነስ አስተዳደር ፣ በኦዲቲንግ ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ወይም በኢንቨስትመንት ማኔጅመንት መሠረታዊ ክህሎትን /ችሎታን ያካተተ እና የፆታ ስብጥርን ያገናዘበ ቢሆን ይመረጣል፤
  6. የፋይናንስ ድርጅት የቦርድ ዳይሬክተር ያልሆነ/ች ወይም ዳይሬክተሩ/ሯ 10% ወይም ከዚያ በላይ የባለቤትነት ድርሻ ያልያዘበት/ችበት የንግድ ድርጅት፤
  7. የማንኛውም ባንክ ተቀጣሪ ሠራተኛ ያልሆነ/ች፤
  8. የቡና ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥቆማና አስመራጭ ኮሚቴ አባል ያልሆነ/ች፤
  9. በግሉ/ሏ ወይም ሌላ ባለአክስዮንን በመወከል በቡና ባንክ አ.ማ ውስጥ ለተከታታይ ስድስት ዓመታት በቦርድ አባልነት አገልግሎ/ላ ከሆነ/ች ከለቀቀበት/ችበት ጊዜ ጀምሮ ስድስት ዓመታት ያለፈው/ፋት፤
  10. በብሔራዊ ባንክ እምነት መሰረት ታማኝ ፣ ሐቀኛ፣ ጠንቃቃ እና መልካም ዝና ያለው/ላት፤
  11. መልካም የፋይናንስ ታሪክና አቋም ያለው/ያላት ፤ የንግድ ሥራን ከመተግበር ወይም ድርጅትን ከመምራት አኳያ በፍርድ ቤት የመክሰር ውሳኔ ያልተላለፈበት/ባት፣ ከታክስ እና ከባንክ ክፍያዎች ጋር በተያያዘ ግዴታዎቹን/ቿን በአግባቡ የተወጣ/ች፤
  12. መልካም ስነምግባር ያለው/ላት፣ከዚህ በፊት በንግድ ማህበር አደራጅነት፣ ዳይሬክተርነት፣ ስራ አስኪያጅነት፣ተቆጣጣሪነት፣ኦዲተርነት ወይም በሌሎች የአመራር ኃላፊነቶች ላይ ተመድቦ/ባ ሲሰራ/ስትሰራ ከኃላፊነቱ/ቷ ጋር በተያያዘ ወይም በማናቸውም ሌላ ሁኔታ በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ በእምነት ማጉደል፣ በስርቆት ፣ በማጭበርበር፣ በውንብድና ወይም በሌላ ለቦርድ አባልነት ብቁ በማያደርግ ተመሳሳይ ወንጀል በፍ/ቤት ተከሶ/ሳ የጥፋተኝነት ውሳኔ ያልተሰጠበት/ባት፤
  13. ከመንግስት ባለስልጣናት መረጃን በመደበቅ፣ የተሳሳቱ የሂሳብ ወይም ሌሎች ሰነዶችን በመስጠት፣ የተቆጣጣሪ አካላትን ማረጋገጫዎች ባለመቀበል፣ መስፈርቶችን ባለማሟላት ፣ የእርምት ወይም የማስተካከያ እርምጃዎችን ባለመውሰድ ሪከርድ የሌለበት/ባት፤
  14. በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በውጭ ሃገር በሚገኝ በማናቸውም በፈረሰ ባንክ ውስጥ ዳይሬክተር የነበረ/ች ከሆነ በቅድሚያ ከብሔራዊ ባንክ የጽሁፍ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል/ ምትችል፤
  15. ዕጩ ተጠቋሚው በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው ድርጅት ከሆነ፤ ድርጅቱን ወክሎ የሚያገለግል ቋሚ ተወካይ (የተፈጥሮ ሰው) መመደብ ያለበት ሲሆን ይህ ተወካይ ሁሉንም መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅበታል፤
  16. መስፈርቱን የሚያሟሉ ሴት ዕጩዎች ይበረታታሉ፤

   

  ለበለጠ መረጃ ባለአክስዮኖች በስልክ ቁጥር 011-8-722845/011-1-264357 ደውለው ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

   

  ማሳሰቢያ፤

  ኮሚቴው ከጥቅምት 01 ቀን 2014 . በኋላ የሚቀርቡ ጥቆማዎችን የማይቀበል መሆኑን ከወዲሁ ያሳስባል!!!

  NameDownloads
  እጩ መጠቆሚያ ቅጽ

  የቡና ባንክ አ.ማ

  የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት አስመራጭ ኮሚቴ

  Bunna Bank