New to site?


Login

Lost password? (X)

Already have an account?


Signup

(X)
Farooq

ቡና ባንክና የኢትዮጲያ ቡና ስፖርት ክለብ የዘላቂ አጋርነት ስምምነት ተፈራረሙ

HomeNewsቡና ባንክና የኢትዮጲያ ቡና ስፖርት ክለብ የዘላቂ አጋርነት ስምምነት ተፈራረሙ
28
Dec
ቡና ባንክና የኢትዮጲያ ቡና ስፖርት ክለብ የዘላቂ አጋርነት ስምምነት ተፈራረሙ
 • Author
  Genet Fekade
 • Comments
  0 Comments
 • Category

በባለአክሲዮን ብዛት ከቀዳሚ ባንኮች ተርታ የሚመደበው ቡና ባንክ እና በደጋፊ ቁጥር ቀዳሚ የሆነው የኢትዮጲያ ቡና ስፖርት ክለብ የዘላቂ አጋርነት ስምምነት ተፈራረሙ።

ሁለቱ “ቡናዎች” በሁሉም ዘርፍ በጋራ ለመስራትየሚያስችላቸውን የጋራ ስምምነት ተፈራርመው ወደስራ መግባታቸውን ይፋ ያደረጉት ዛሬ በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

ስምምነቱ ይፋ በተደረገበት ወቅት እንደተገለጸው ባንኩም ሆነ ክለቡ የሚጋሩት ስም የሁሉም ኢትዮጲያዊ ከመሆኑ ባሻገር ህዝባዊ መሰረት  ያላቸው መሆናቸው  አንድ የሚያደርጋቸው የጋራ መለያቸው ነው ተብሏል ።

ስምምነቱ የተፈረመው በባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ እና በክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ ሲሆን በስነስርዓቱ ላይ የባንኩና የክለቡ የስራ አመራር  አባላት ተገኝተዋል።

በስምምነቱ መሰረትም ቡና ባንክ ለኢትዮጵያ ስፖርት ክለብ የ 5 ሚሊዮን ብር የአንድ አመት ስፖንሰርሺፕ ክፍያ የሚከፍል ሲሆን ስምምንቱም በየዓመቱ የሚታደስ ይህናል።

በስምምነቱ መሰረት ክለቡ የባንኩን አርማ በተጫዋቾች ቲሸርትና ቁምጣ ላይ በማሳየት ባንኩን ያስተዋውቃል፡፡በተጨማሪም በሜዳውም ይሁን ያለሜዳው ጨዋታ በሚኖረው ወቅት የባንኩ ቢልቦርድ ማስታወቂያ በጨዋታው ሜዳ አካባቢ እንዲቀመጥ ያደርጋል።

ክለቡ በተቻለው መጠን የባንኩን ብራንድ እና አገልግሎቶች እንዲያስተዋውቅም በስምምነቱ ተካትቷል።

ስምምነቱ ከዚህ በተጨማሪ የስፖርት ክለቡ የባንክ ሂሳቡን በባንኩ እንዲከፍት ከማድረግ  ጀምሮ የክለቡ አባላትና ደጋፊዎች የባንኩ ደንበኛ እንዲሆኑ ማድረግን የመሳሰሉ  የባንክ አገልግሎቶችን ከባንኩ እንዲያገኙ  የሚያደርግ ነው ተብሏል።

እንደስምምነቱ ባንኩ  የስፖርት ክለቡ ደጋፊዎች ማህበር ወርሃዊ የአባልነት መዋጮአቸውን በዘመናዊ የቴክኖሎጂ አሰራር በመታገዝ በባንኩ በኩል እንዲከፍሉ  የሚያስችላቸው አሰራር ይዘረጋል። በተለያየ የሀገሪቱ ክፍል ለሚገኙ የክለቡ አባላትም የባንክ አገልግሎት እገዛ ያደርጋል ተብሏል፡፡

ቡና ባንክና የኢትዮጲያ ቡና ስፖርት ክለብ  እንደስማቸው አንድ መሆን የጋራ እድገት ለማስመዝገብ የሚያስችሉ ሌሎች በርካታ ስራዎችንም በጥምረት ለመስራት መስማማታቸውን ነው በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ያበሰሩት፡፡

ከተመሰረተ 11 ዓመታት  የሆነውና ከ13ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖች ያሉት  ቡና  ባንክ

የእግር ኳስ ስፖርቱን በመደገፍና በዓለም አደባባይ አርማውን በማስተዋወቅ ከቀዳሚዎቹ ተርታ የተሰለፈ ባንክ ሆኗል፡፡

Tags:

  

  ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ የ11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 4ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ
  

  በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ አንቀጽ 418፣ 419 እና 423 እንዲሁም በባንኩ መመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 11.3.7 እና በመተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 6.3 መሠረት የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 4ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ ታህሳስ 11 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ ጦርሃይሎች አካባቢ በሚገኘው ጎልፍ ክለብ ውስጥ ይካሄዳል፡፡

  ስለሆነም የባንኩ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም በሕጋዊ ተወካዮቻችሁ አማካኝነት በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ ጉባኤው ላይ እንድትገኙ ባንኩ በአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡

  የ4ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

  1) ረቂቅ አጀንዳዎችን ማጽደቅ፣

  2) በባንኩ የመመስረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ

  3) የጉባኤውን ቃለ-ጉባኤ ማጽደቅ

  የ11ኛ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

  1) ረቂቅ አጀንዳዎችን ማጽደቅ፣

  2) በባንኩ ውስጥ የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን እና የአዲስ አክሲዮኖችን ሽያጭ መርምሮ ማጽደቅ፣

  3) እ.ኤ.አ የ2019/20 የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ፣

  4) እ.ኤ.አ የ2019/20 የውጭ ኦዲተሮች ቦርድ ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርትን ማዳመጥ፣

  5) በተራ ቁጥር 3 እና 4 የቀረቡትን ሪፖርቶች ተወያይቶ ማጽደቅ፣

  6) የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማ እና ምርጫ አፈፃፀም የአሰራር ደንብ ማሻሻያን መርምሮ ማጸደቅና የአስመራጭ ኮሚቴ አባላት አበልን መወሰን፣

  7) የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴን መምረጥ፣

  8) እ.ኤ.አ የ2020/21 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ አበልና ዓመታዊ ክፍያ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣

  9) እ.ኤ.አ የ2020/21 በጀት ዓመት የውጭ ኦዲተሮችን ሹመት ማጽደቅና አበል መወሰን፣

  10) በዘመኑ የተጣራ ትርፍ አደላደል እና አከፋፈል ላይ የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ መወሰን፣

  11) የጉባኤውን ቃለ-ጉባኤ ማጽደቅ፣ የሚሉት ናቸው፡፡

  ማሳሰቢያ

  1. በጉባኤው ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች አግባብነት ካለውና ሕጋዊ ውክልና መስጠት ከሚችል የመንግሥት አካል የተሰጠ’ በስብሰባው ላይ ለመገኘትና ድምጽ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ሰነድ ወይም ከስብሰባው ሶስት ቀን ቀደም ብሎ ቦሌ መንገድ ከወሎ ሰፈር አደባባይ ቀጥሎ ርዋንዳ መታጠፊያ ከመድረሱ በፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 4ኛ ፎቅ የባንኩ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድርስ በመቅረብ የውክልና ፎርም (ቅጽ) በመሙላት፣ ሌላ ሰው በመወከል የውክልና ሰነዱን ወይም ቅጹን ዋናውንና አንድ ቅጂ ይዘው በመምጣት በጉባዔው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እናስታውቃለን፡፡

  2. ባለአክስዮኖችም ሆኑ ህጋዊ ወኪሎቻቸው ወደ ስብሰባው ቦታ ሲመጡ የራሳቸውንም ሆነ የተወካዮቻቸውን ሕጋዊ የታደሰ መታወቂያ ካርድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን መያዝ አለባቸው፡፡

  3. ባንኩ የባለአክሲዮኖችን የመለያ ቁጥር ባስመዘገባችሁት ተንቀሳቃሽ ስልክ የሚልክ ሲሆን& ይህንኑ ቁጥር በስብሰባው ዕለት ይዛችሁ እንድትመጡ በአጽንኦት እንጠይቃለን፡፡

  4. ከላይ በተ.ቁ. 2 ላይ የተገለፀውን የወካዩን ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሚያረጋግጥ ሕጋዊና የታደሰ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ኮፒ ይዘው የማይመጡ ተወካዮች በጉባኤው ላይ መሳተፍ የማይችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡ በተጨማሪም የድርጅት ተወካዮች ድርጅቱን ወክለው በስብሰባው እንዲገኙና ድምጽ እንዲሰጡ መወከላቸውን የሚያረጋግጥ የተመዘገበ ቃለ-ጉባዔ ወይም በውል አዋዋይ ፊት የተሰጠ ውክልና ዋናውን እና ኮፒውን ይዘው መቅረብ ያለባቸው መሆኑን እናስታውቃለን፣፡

  5. የብሄራዊ ባንክ ያስቀመጠውን የውክልና አሰጣጥ መጠን ገደብ ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ለጊዜው ያነሳ በመሆኑ ወረርሽኙን ለመከላከል ሲባል ባለአክሲዮኖች በጉባዔው በውክልና እንዲሳተፉ ይበረታታሉ፡፡

  6. ተጨማሪ መረጃ ቦሌ መንገድ ከወሎ ሰፈር አደባባይ ቀጥሎ ወደሩዋንዳ መታጠፊያ ከመድረሱ በፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ 0111580880 / 262822 / 262810 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

  የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ

  የዳይሬክተሮች ቦርድ

  ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ

  የባለራዕዮች ባንክ!!!

  Bunna Bank