New to site?


Login

Lost password? (X)

Already have an account?


Signup

(X)
Farooq

ቡና ባንክ ለዳያስፖራው ማህበረሰብ ያዘጋጃቸው አገልግሎቶች

HomeNewsቡና ባንክ ለዳያስፖራው ማህበረሰብ ያዘጋጃቸው አገልግሎቶች
03
Feb
ቡና ባንክ ለዳያስፖራው ማህበረሰብ ያዘጋጃቸው አገልግሎቶች
 • Author
  Genet Fekade
 • Comments
  0 Comments
 • Category

1 መግቢያ

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ የተለያዩ የባንከ አገልግሎቶችን ለደንበኞቹ በማቅረብ  እ.ኤ.አ ከ2009 ጀምሮ ሥራ የጀመረ የግል ባንክ ነው ፡፡ በአሁኑ ወቅት ባንኩ ከ265 በላይ በደረሱ ቅርንጫፎቹ እና በዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ ግብይቶች በኩል ማለትም እንደ ኢንተርኔት ባንክንግ፣ ሞባይል ባንኪንግ ፣  ኤቲኤም እና ፖስ ማሽን ባሉ አማራጮች አማካይነት የተለያዩ አገልግሎቶችን ያቀርባል ፡፡

ከዳያስፖራ ማህበረሰብ ጋር በተያያዘ ባንኩ በውጭ ሀገር ከአንድ ዓመት በላይ ለኖሩ እና/ ወይም የውጭ ሀገር ዜግነት ላላቸው ኢትዮጵያዊያን  ማራኪ የዲያስፖራ ተቀማጭ ሂሳቦችን አዘጋጅቷል ፡፡ በተጨማሪም ባንኩ ለዳያስፖራ ማህበረሰብ ዝቅተኛ የወለድ ምጣኔ ያለው  የዳያስፖራ የብድር  አገልግሎት አዘጋጅቶ ደንበኞቹን ተጠቃሚ አድርጓል ፡፡  

የአገልግሎት አይነቶቹም ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል ፡፡

 1. የዲያስፖራ የተቀማጭ ሂሳብ አገልግሎት

ከአንድ አመት በላይ በውጭ ሃገር ለኖሩ እና / ወይም ትውልደ ኢትዮጲያዊ ለሆኑ የውጭ አገር ዜጎች የዳያስፖራ ተቀማጭ ሂሳቦች አዘጋጅቷል ፡፡ ዓላማውም የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ ገንዘቡን አመርቂ በሆነ የወለድ ተመን እንዲቆጥብ እና ሀብቱን በትውልድ ሐገሩ ላይ ኢንቨስት እንዲያደርግ ማገዝ ነው ፡፡

ሂሳቡ በአሜሪካ ዶላር ፣ ፓውንድ ስተርሊንግ ፣ ዩሮ እና ሌሎች ሊለወጡ በሚችሉ እንደ አውስትራሊያ ዶላር ፣ የካናዳ ዶላር ፣ የጃፓን ዬን ፣ የሳውዲ ሪያል እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ድርሃም ባሉ የተቀማጭ ገንዘብ አይነቶች በውጭ አገር በሚኖሩ ግለሰቦች እና ኩባንያዎች ሊከፈት ይችላል ፡፡

የዲያስፖራ ተቀማጭ ሂሳብ አገልግሎት የሚከተሉትን ያካትታል

የዲያስፖራ የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎት፡-ከፍተኛ የወለድ ምጣኔ የሚከፈልበት የዲያስፖራ የቁጠባ ሂሳብ ሲሆን የቁጠባ ሒሳብ ደብተርን በመጠቀም የሚንቀሳቀስ ነው፡፡  ሌላኛው የዲያስፖራ ተቀማጭ ሒሳብ አገልግሎት ደግሞ የዲስፖራ ተንቀሳቃሽ ሒሳብ አግልግሎት በመባል ይታወቃል፤  ይኸውም ምንም አይነት የወለድ ምጣኔ የሌለው ሲሆን ሒሳቡም በማንኛውም ጊዜ በቼክ የሚንቀሳቀስ ይሆናል፡፡ ሌላኛው የዲያስፖራ ተቀማጭ ሒሳብ አገልግሎት የዲየስፖራ በጊዜ ገደብ የሚቀመጥ የሒሳብ አገልግሎት ሲሆን   ቀደም ብሎ በሚደረግ ድርድር የወለድ ምጣኔዉ ይወሰናል  ፤ ይህንንም የሂሳብ አይነት ለመክፈት ከ 5ሺህ ዶላር በላይ ወይም የሱን ተመጣጣኝ የሆነና ከላይ ከተጠቀሱት በአንዱ አይነት መገበያያ ገንዘብ የሚያስፈልግ ሲሆን ይህንን አገልግሎት ለማግኘት በትንሹ ለሶስት ወር ያህል ገንዘቡን ማስቀመጥ ይጠይቃል። ከዚህ ሂሳብ  የሚገኝ ወለድ ከገቢ ግብር ነፃ ይሆናል፡፡ ገንዘብ ማስተላለፍ

ይህ አገልግሎት ከላይ ከተጠቀሱት የገንዘብ አይነቶች በአንዱ የገንዘብ አይነት ወደ ኢትዮጵያ ለሚኖሩ ዘመዶች ፣ ወዳጆች ወይም ኩባንያዎች ዓለም አቀፍ  የገንዘብ ማስተላለፊያ ዘዴዎችን በመጠቀም ገንዘብ ማስተላለፍ የሚቻልበት ነው። የገንዘብ ማስተላለፉ በባንኩ የSWIFT ወይም በዓለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ወኪሎች በኩል ሊከናወን ይችላል ፡፡ ከባንኩ ጋር አብረው የሚሰሩ  ወኪሎች ዉስጥ እንደ ዌስተርን ዩኒየን ፣ መኒ ግራም ፣ ኤክስፕስ መኒ ፣ ትራንስፋስት  ፣ ወርልድ ሪሚት ፣ ካህ ፣ ካሽ ኤክስፕረስ ይገኙበታል.

የዲያስፖራ ብድር አገልግሎት

 የዲያስፖራ የቤት መግዣ/መስሪያ ብድር አገልግሎት

በኢትዮጲያ ነዋሪ ያልሆኑ ኢትዮጵያዊ ዳያስፖራዎች እና ነዋሪ ያልሆኑ የውጭ ሐገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጰያውያን ለተወሰነ ጊዜ በውጭ ምንዛሪ በቅድሚያ የተወሰነውን ገንዘብን በማስቀመጥ በኢትዮጵያ ውስጥ የመኖሪያ ወይም የንግድ ሕንፃዎችን እንዲገዙ ወይም እንዲገነቡ የሚያስችል የብድር አይነት ነው ፡፡  ባንኩ እስከ 80% የሚሆነውን የሕንፃ ግንባታ ወይም የግዥ መጠን ፋይናንስ ሊያደርግ ይችላል ፡፡ ለዚህ ዓይነቱ ብድር የተተመነው የወለድ መጠን እንደ ተበዳሪው የውጭ ምንዛሬ መዋጮ መጠን ይለያያል ፡፡

ዲያስፖራ የመኪና ብድር አገልግሎት

አዲስ ወይም ያገለገለ አውቶሞቢል ለመግዛት ፍላጎት ላለው ዲያስፖራ የተመቻቸ የብድር አይነት ነው ፡፡ ባንኩ ለአዳዲስ (ዜሮ ማይሌጅ) አውቶሞቢል ከተሽከርካሪው ዋጋ እስከ 80% እና አገልግሎት ለሰጡ አውቶሞቢሎች  እስከ 60% ሊያበድር  ይችላል ፡፡ ለዚህ ዓይነቱ ብድር የተተመነው የወለድ መጠን እንደ ተበዳሪው የውጭ ምንዛሬ መዋጮ መጠን ይለያያል፡፡

ለግል ጉዳይ የሚሰጥ የዲያስፖራ ብድር

ለዕቃዎች መግዣ ፣ ለቤት እድሳት ፣ ለትምህርት ፣ ለህክምና  ፣ ለመኪና እድሳት እና ለሌሎች አንዳንድ የግል የገንዘብ ፍላጎቶች የሚመቻች የብድር አይነት ነው ፡፡ ከላይ እነደተጠቀሱት ብድሮች ሁሉ ለዚህ ዓይነቱ ብድርም የተተመነው የወለድ መጠን እንደ ተበዳሪው የውጭ ምንዛሬ መዋጮ መጠን ይለያያል፡፡

የዲያስፖራ የኢንቨስትመንት ብድር አገልግሎት

በንግድ ሥራ ወይም በኢንቨስትመንት ለመሰማራት ፍላጎት ላለው ዳያስፖራ የሚሰጥ የብድር አገልግሎት አይነት ነው ፡፡ ለዚህ ዓይነቱ ብድር የተተመነው የወለድ መጠን እንደ ተበዳሪው የውጭ ምንዛሬ መዋጮ መጠን ይለያያል ፡፡

ከላይ ለተጠቀሱት የባንክ አገልግሎቶች የብቁነት መስፈርቶች

ሂሳብ ለመክፈት

ከአንድ አመት በላይ በውጭ ሀገር የኖሩ እና / ወይም ትውልደ ኢትዮጲያዊ የሆኑ የውጭ ሀገር ዜጎች የዲያስፖራ አካውንቶች ሊከፍቱ ይችላሉ ፡፡ የሥራ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት እንደ ማረጋገጫ ያገለግላሉ፡፡

ብድር ለማግኘት ብቁ የሚያደርጉ መስፈርቶች

አመልካቹ ለመበደር ብቁ ለመሆን የዲያስፖራ አካውንት ከፍቶ የሥራ ፈቃድ ፣ የተረጋገጠ የሥራ ውል እና የግብር ሰነድ ሊኖረው ይገባል ፡፡ ሌሎች የሚያስፈልጉ ሰነዶች  ማለትም፡- የጋብቻ  ሁኔታ ማረጋገጫ ፣ ማመልከቻ ፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር ፣ የሂሳብ መግለጫ እና / ወይም የፕሮጀክት ፕሮፖዛል የመሳሰሉት በተጨማሪነት ያሰፈልጋሉ።

Tags:

  እጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ ለመቀበል የወጣ ማስታወቂያ

  የቡና ባንክ አ.ማ የቦርድ አባላት ምርጫ የሚከናወነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር SBB/79/2021 እና SBB/71/2019 እንዲሁም በኩባንያው ባለአክሲዮኖች 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በጸደቀው የቦርድ አባላት ጥቆማና ምርጫ አፈጻጸም የአሠራር ደንብ መሠረት ነው፡፡ እነዚህን መመሪያዎች መሠረት በማድረግ በቀጣይ ባንኩን በቦርድ አባልነት የሚመሩ አባላትን ለማስመረጥ ታህሳስ 11 ቀን 2013 ዓ.ም በተካሄደው የባለአክሲዮኖች 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የቦርድ አባላት አስመራጭ ኮሚቴ መቋቋሙ ይታወሳል፡፡ በጠቅላላ ጉባኤው የተቋቋመው አስመራጭ ኮሚቴ እጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማዎችን ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

  ስለሆነም ባለአክሲዮኖች ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት ብቁ ናቸው ብላችሁ የምታምኑባቸውን እጩ የቦርድ አባላት ለመጠቆም የሚያስችላችሁን የጥቆማ መሙያ ወይም ማስፈሪያ ቅጽ በቡና ባንክ አ.ማ ድረ ገጽ https://www.bunnabanksc.com ወይም የባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኝበት ቦሌ መንገድ ሩዋንዳ መታጠፊያ አካባቢ ባለው የቡና ባንክ አ.ማ ሕንፃ 8 ፎቅ በሚገኘው የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ ጽ/ቤት ቢሮ ወይም በባንኩ ቅርንጫፎች በአካል በመቅረብ ለጥቆማ መስጫ የተዘጋጀውን ቅጽ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን አስመራጭ ኮሚቴው ያሳውቃል፡፡

  ስለሆነም የባንኩ ባለአክሲዮኖች ለባንኩ ሁለንተናዊ እድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት ይችላሉ ብለው የሚያምኑባቸውን ብቁ እጩዎችን በቅጹ ላይ በጥንቃቄ በመሙላት ከሐምሌ 01 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 01 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ከታች በተመለከቱት አማራጮች በመጠቀም እንዲጠቁሙ አስመራጭ ኮሚቴው በአክብሮት ይጋብዛል፡፡

  ባለአክሲዮኖች የሞሉትን ቅጽ በቡና ባንክ አ.ማ ዋና መ/ቤት 8ኛ ፎቅ በዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ቅጹን መሙላት ወይም አድራሻውን ለቡና ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ በማለት በባንኩ የፓ.ሣ.ቁጥር 1743 ኮድ 1110  በአደራ ደብዳቤ መላክ ወይም የተሞላውን ቅፅ ስካን በማድረግ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው በባንኩ ኢሜል bibnomination@bunnabanksc.com አያይዘዉ መላክ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  ተጠቋሚ እጩ የቦርድ አባላት የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፤

  1. ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሆነ/ች እንዲሁም ዕድሜው/ዋ 30 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ/ች፤
  2. የቡና ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮን የሆነ/ች እና ቢመረጥ/ብትመረጥ በዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት ለመሥራት ፈቃደኛ የሆነ/ች፣
  3. ለቦታው የተገቢነት እና የብቃት መስፈርት (Fit and Proper) የሚጠይቀውን  የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ያጠናቀቀ/ች፣
  1. በቢዝነስ ማኔጅመንት፤ በባንክ ሥራ፤ በፋይናንስ፤ በአካውንቲንግ፤ በሕግ፣ በኦዲቲንግ፤ በኢኮኖሚክስ፤ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፤ በኢንቨስትመንት ማኔጅመንት የትምህርት መስክ የተመረቁና የጾታ ስብጥራቸውም ተመጣጣኝ ቢሆን ይመረጣል፣
  2. የቡና ባንክም ሆነ የሌሎች ባንኮች ተቀጣሪ ሠራተኛ ያልሆነ/ነች፤ እንዲሁም የማንኛውም የፋይናንስ ተቋም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይም የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ያልሆነ/ነች፤
  3. ተጠቋሚው የሕግ ሰውነት ያለው ድርጅት ከሆነ ድርጅቱን ወክሎ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ለመሆን የሚወዳደረው የተፈጥሮ ሰው ማንነትና የትምህርት ደረጃ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ ነገሮች ሁሉ መጥቀስ፤
  4. የቡና ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ አባል ያልሆነ/ነች፤
  5. ቡና ባንክ አክሲዮን ማህበርን ለስድስት ተከታታይ ዓመታት በቦርድ አባልነት አገልግለው ከቦርድ አባልነት የለቀቁ ከሆነ ከለቀቁበት ጊዜ ጀምሮ ስድስት ዓመታት የሆናቸው (የሞላቸው)፤
  6. በሕዝብ ዘንድ ተአማኒነት ያለው/ያላት እና የጸዳ የፋይናንስ አቋም ያለው/ያላት፤
  7. በሕዝብ ዘንድ መልካም ሥነምግባር፣ ማሕበራዊ ተቀባይነት ያለው/ያላት እና ሕግን በመተላለፍ በኢትዮጵያም ሆነ በውጭ አገራት በወንጀል በመከሰስ ተፈርዶበት/ባት የማያውቅ/የማታውቅ፤
  8. ለመንግሥት ባለሥልጣናት መረጃን በመከልከል፤ የተሳሳቱ የሂሳብ ወይም ሌሎች ሰነዶችን በመስጠት የተቆጣጣሪ አካላትን መመሪያዎች ባለመቀበል እና ባለመገዛት በመንግሥት ባለሥልጣናት አስተዳደራዊ የእርምት እርምጃዎች ተወስዶበት/ባት የማያውቅ/የማታውቅ፤
  9. የንግድ ሥራን ከመተግበር ወይም ድርጅትን ከመምራት አኳያ በፍርድ ቤት የመክሰር ውሳኔ ያልተላለፈበት/ባት፣ ከታክስ እና ከባንክ ክፍያዎች ጋር በተያያዘ ግዴታዎቹን/ቿን በአግባቡ የተወጣ/ች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

  ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-8-722845 ወይም በ011-1-264357 በመደወል ባለአክሲዮኖች ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

  ማሳሰቢያ፤

  አስመራጭ ኮሚቴው ከሐምሌ 01 ቀን 2013 ዓ.ም በፊትም ሆነ ከጥቅምት 01 ቀን 2014 ዓ.ም በኋላ የሚቀርቡ ጥቆማዎችን የማይቀበል መሆኑን ከወዲሁ ያሳስባል፡፡

  NameDownloads
  እጩ መጠቆሚያ ቅጽ

  የቡና ባንክ አ.ማ

  የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት አስመራጭ ኮሚቴ

   

  Bunna Bank