ግንቦት 12 ቀን 2017 ዓ.ም፤ የቡና ባንክ ቄራ ቅርንጫፍ የተመሰረተበትን 8ኛ አመት በአል በደማቅ ዝግጅት አክብሮ ዉሏል፡፡ በዝግጅቱ ላይ የቅርንጫፉ ደንበኞች፤ የዲስትሪክት ሀላፊዎች፤ የቅርንጫፍ ሰራተኞች እንዲሁም ከዚህ በፊት በቅርንጫፉ ይሰሩ የነበሩ ሰራተኞች ተሳትፈዉበታል፡፡
በዝግጅቱ ላይ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክትን ያስተላለፉት የቄራ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አደስ በየነ ፤ በንግግራቸዉ ፕሮግራሙ ላይ ተሳታፊ ለሆኑ ሁሉ ላቅ ያለ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል፡፡ ለቄራ ቅርንጫፍ ስኬታማ መሆን ቁልፍ ምክንያቱ በሰራተኞች መካከል ያለዉ መልካም ግንኙነት እንደሆነ ገልፀዉ፤ በዝግጅቱ ላይ ለነበሩ የቄራ ቅርንጫፍ ሰራተኞችና የረጅም ጊዜ ደንበኞች ላላቸዉ መልካም ግንኙነት ከፍተኛ ክብር እና ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በበአሉ መጨረሻ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ መልሰዉ አጉመስ፤ የደቡብ አዲስ አበባ ዲስትክት የባንክ ቢዝነስ ክፍል ኃላፊ(manager-south addis ababa bank business division)፤ ለቄራ ቅርንጫፍ ሰራኞች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ፤ እንደዚህ አይነት ዝግጅቶች ለሌሎች ቅርንጫፎች ተምሳሌት ሊሆኑ እንደሚገባ መልክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡






