Bunna Bank

ቡና ባንክ በታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋይነት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆነ

6ኛ ዙር የታማኝ ግብር ከፋዮች የምስጋናና የዕውቅና ሽልማት መርሐ ግብር ትናንት መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም በአንድነት ፓርክ ተካሂዷል።

በዚህ መርሃ ግብር ላይም ቡና ባንክ በ2016 የበጀት ዓመት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ግብር በመክፈል የበጀት አመቱ ታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋይ የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆኗል።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትርን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሃገሪቱ ባለስልጣናት በተገኙበትና በአዲስ ፓርክ (ብሄራዊ ቤተመንግስት) ግብር አዳራሽ በተካሄደው በዚሁ ስነስርዓት በተለያዩ መስፈርቶች የተመረጡ 550 ተቋማት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። ከነዚህ መካከልም 66 ኩባንያዎች በፕላቲኒየም፣ 165 ኩባንያዎች በወርቅ እንዲሁም 319 ኩባንያዎች በብር ደረጃ ተሸላሚ ሆነዋል።

ቡና ባንክ አምና በ2015 ዓ.ም በተካሄደው ተመሳሳይ መርሃ ግብር በታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋይነት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ እንደነበር ይታወሳል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

[ivory-search id="5747" title="Custom Search Form"]

This will close in 0 seconds

error: