Bunna Bank

ቡና ባንክ በ3ኛው የ”ይቆጥቡ ይሸለሙ” ፕሮግራም ላይ ለተሳተፉ የዕጣ አሸናፊ መምህራን እና የጤና ባለሙያዎች ሽልማት ሰጠ!

• ወ/ሮ ፈንታዬ ደምሌ የዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል አሸናፊ ሲሆኑ ሌሎች አሸናፊዎችም ሽልማቶቻቸውን ተረክበዋል፡፡
ቡና ባንክ አክሲዮን ማህበር ለወራት ሲያካሂድ የቆየውን ሶስተኛውን ዙር የመምህራንና የጤና ባለሙያዎች ይቆጥቡ ይሸለሙ መርኀ-ግብር ማጠናቀቂያ ምክንያት በማድረግ ያዘጋጃቸውን ሽልማቶች ዛሬ ታህሳስ 23 ቀን 2016 ዓ.ም. ለዕድለኛ ደንበኞቹ በይፋ አስረከበ፡፡
በቡና ባንክ ዋና መስሪያ ቤት በተካሄደው በዚሁ የሽልማት አሰጣጥ ስነ-ስርዓት ላይ አሸናፊ ለሆኑ ባለዕድለኞች የአውቶሞቢል፣ ላፕቶፕ፣ ታብሌት እና ዘመናዊ የስልክ ቀፎ ሽልማቶችን አበርክቷል፡፡
የኢትዮጵያ የሶስተኛ ትውልድ ሀገር በቀል የፋይናንስ ተቋም የሆነው ቡና ባንክ መምህንና የጤና ባለሙያዎች በቡና ባንክ በመቆጠብ ላሳዩት ያላሰለሰ ጥረት እና በቡና ባንክ ቁጠባና ሽልማት ፕሮግራም በመሳተፍ የዕጣ አሸናፊ በመሆቸው የቁጠባ ፕሮግራሙ ተሸላሚ ሆነዋል።
እነዚህ የተከበሩ የአገር ባለውለታዎች የቁጠባ ልማዳቸውን እና አስተዋይነት የተሞላበት የፋይናንስ ውሳኔዎቻቸውን ለማበረታታት እና ለመሸለም በተቀረጸው ኢኒሼቲቭ መነሻነት ቡና ባንክ ዛሬ በተካሄደው ታላቅ የሽልማት ስነ – ስርአት የቁጠባና የሽልማት ፕሮግራም ለሶስተኛው ዙር አሸናፊዎች ሽልማት አበርክቷል።
ቡና ባንክ የሀገራችን የወደፊት እጣ ፈንታ በመቅረጽ ረገድ ትልቅ ሚና የሚጫወቱትን ድንቅ ሙያተኞችን በማክበሩ ኩራት ይሰማዋል። እነዚህ ባለሙያዎች ለትምህርት እና ለጤና አጠባበቅ ዘርፎች ያበረከቱት የማይናቅ አስተዋፅዖ በእውነት አበረታች በመሆኑ በቁጠባ ላይ ያላቸውን ቁርጠኝነት እንደ ቡና ባንክ በቋሚነት የምናስተዋውቀውና የምናበረታታው የፋይናንስ ተቋም ኃላፊነትን ማሳያ ነው።
ቁጠባ ለግለሰብ ፋይናንሺያል ደህንነት ብቻ ሳይሆን ለሀገራዊ እድገት ለውጥ የሚያመጣ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። የቁጠባ ልማዶችን በአነዚህ ጥንቁቅና ቁርጠኛ ባለሙያዎች ዘንድ እንዲዳብር በማድረግ ባንካችን የፋይናንስ ግባቸውን እንዲያሳኩ እና ለኢትዮጵያ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገትና ብልፅግና የሚጠበቅባቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ በማድረግ ላይ ይገኛል።
ቡና ባንክ መምህራንን እና የጤና ባለሙያዎችን ለመደገፍ ያላሰለሰ ሙያዊ ድጋፍና ጥረት በማድረግ የፋይናንሺያል እውቀታቸው እንዲያድግ እና የቁጠባ ባህልን በመላው ኢትዮጵያ ለማጎልበት ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋግጣል።
ባንካችን ከእነዚህ ውድ የአገራችን ባለሙያዎች ጎን በመቆም የፋይናንሺያል ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ እና በሙሉ ልባቸው በክቡር ሙያቸው ላይ እንዲያተኩሩ ለማድረግ ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል። እንደ አንድ የፋይናንስ ተቋም የቁጠባ ልማዶችን እንዲስፋፉ በማስተዋወቅ የፋይናንስ ብልጽግና ለሁሉም ተደራሽ የሆነባትን ኢትዮጵያ በጋራ መገንባት እንደምንችል በፅኑ እናምናለን።
ይህ የይቆጥቡ ይሸለሙ የቁጠባ እና የሽልማት መርሃ ግብር የቡና ባንክ ለማህበራዊ ሃላፊነት ያለውን የማያወላውል ቁርጠኝነት እና ኃላፊነት በተሞላበት የፋይናንስ አሰራር ግለሰቦችን ለማብቃት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ተግባር ነው። ስለሆነም ባንኩ የቁጠባ ልማዶችን ለማስተዋወቅ እና ለኢትዮጵያ ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገትና ልማት የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማድረግ ጥረቱን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
ቡና ባንክ በኢትዮጵያ የሶስተኛ ትውልድ ሀገር በቀል የፋይናንስ ተቋም ሲሆን ከ2 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን በቅርንጫፎች፣ በኤቲኤም እና በተለያዩ የዲጂታል አማራጮች ማበረሰቡን እያገለገለ ይገኛል። ባንኩ አዳዲስ የፋይናንሺያል አገልግሎት አማራጮችን ለማቅረብ፣ የፋይናንስ አካታችንትን ለማስተዋወቅ እና ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማድረግ የበኩሉን ጥረት በማድረግ ላይ ነው፡፡ ቡና ባንክ በኢትዮጵያውያን ዘንድ የቁጠባ ባህልን በማስተዋወቅ ረገድ ፈር ቀዳጅ ከሆኑ የፋይናንስ ተቋማት መካከል አንዱ ሲሆን የቡና ባንክ ቁጠባና ሽልማት ፕሮግራምም ለዚህ አንዱ ማሳያ ነው።
ቡና ባንክ ከ14ሺህ በላይ በሆኑ ባለአክሲዮኖች ያሉት ከ14ዓመታት በፊት የተቋቋመና 476 በሚሆኑ ቅርንጫፎቹ በኢትዮጵያ ሁሉም ክልሎች አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ የቡና ቤተሰቦችን ያሰባሰብ የባለራዕዮች ባንክ ነው፡፡ ባናካችን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን አቅም ያገናዘበ ልዩ ልዩ የቁጠባና ብድር አገልግሎቶችን በማቅረብ ተዓማኒነትን ያተረፈ የግል ባንክ ነው፡፡
,,,,,,,ቡና ባንክ ! የባለራዕዮች ባንክ!,,,,,

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

[ivory-search id="5747" title="Custom Search Form"]

This will close in 0 seconds

error: