በደረቅ እና ፈሳሽ ትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማሩ ደንበኞቹን ለማበረታታት ያዘጋጀውን ሽልማት በዛሬው እለት በዋና መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የሽልማት ስነ ስርዓት ለባለእድለኞች አስረክቧል፡፡ የአንደኛ እጣ አሸናፊ ወ/ሮ ሔለን በቀለን ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል ተሸላሚ ሲሆን ሌሎች የእጣ አሸናፊዎችም በስነ ስርዓቱ ሽልማታቸውን ወስደዋል ፡ ፡ በሽልማት መርሃግብሩ ቡና ባንክ ባለራዕየችን የቡና ቤተሰብ በመሆን ከባንኩ ጋር እንዲሰሩ ጥሪ አድርጓል፡፡
ባንኩ ደንበኞቹን እንዲቆጥቡ አሁንም የሚያበረታታ መሆኑኑ በመግለጽ ለመምህራን እና የጤና ባለሙያዎች ለ3ኛ ጊዜ በተዛጋጀው የይቆጥቡ ይሸለሙ መርሀ ግብር ሁሉም በዘርፉ የምትሰሩ ተዋንያኖች በአቅራቢያዎ በሚገኙ የቡና ባንክ ቅርንጫፎች በመቆጠብ እንዲሸለሙ ይጋብዛል፡፡
ግንቦት 15፣ 2015 ዓ.ም.
ቡና ባንክ የባለራዕዮች ባንክ!!
