ቡና ባንክ ከአዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ጋር የቁጠባና ብድር ክፍያዎችን በቡና ባንክ በኩል ለመፈፀም የሚያስችል የሁለትዮሽ ስምምነት ህዳር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ተፈራርመዋል፡፡
በፊርማ ስነ- ስርዓቱ አቶ ለውጤ ጥሩሰው የቡና ባንክ ቺፍ ባንኪንግ ሰርቪስ ኦፊሰር እና አቶ ዘሪሁን ሸለመ የአዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ተቋማቸውን ወክለው ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱ የአዋጭ የገንዘብና ብድር ህብረት ስራ ማህበር አባላት ማንኛውም የቁጠባና የብድር ክፍያዎቻቸውን በቡና ባንክ ቅርንጫፎች አማካኝነት መክፈል የሚያስችላቸው ሲሆን የሁለቱን ተቋማት ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክርና ለደንበኞቻቸው ቀልጣፋ አገልግሎትን የሚሰጥ ነው።