Branch/ATM Locator   |

Announcement    |

FAQs   |

+25111150861    |

ቡና ባንክ እና የአማራ  ቤቶች ልማት ድርጅት የአጋርነት ውል ተፈራረሙ !

ቡና ባንክ እና የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ቤቶች ልማት ድርጅት (አቤልድ) ደንበኞች ወርሃዊ የኪራይ ገቢያቸውን ከሃምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በባንክ እንዲከፍሉ የሚያስችላቸውን ሲስተም ስራ ላይ ለማዋል ተፈራርመዋል፡፡

የሁለትዮሽ ስምምነቱ ከዚህ በፊት የአብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት የኪራይ ገቢ አሰባሰብ ሂደት ላይ በደንበኞች በኩል የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል ነው፡፡

የኪራይ ገቢ አሰባሰብ ሂደት ላይ በደንበኞች በኩል የሚፈጠሩ ችግሮችን ሊፈታ እንዲችል ተደርጎ የሲስተም መተግበሪያ እንዲዘጋጅ በባንኩ እና አቤልድ ተደጋጋሚ ውይይትና ምክክር በማድረግ ትግበራውን ከሃምሌ 1 ቀን2014 ዓ.ም ጀምሮ በባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት በሙከራ ደረጃ የጀመሩ ሲሆን በቀጣይ በሁሉም የድርጅቱ ቤቶች ባሉበት ከተሞች ሲስተሙ እንዲጀምር ይደረጋል፡፡

ቡና ባንክ ከላይ የተገለጹትን ችግሮች የሚፈታ ሲስተም ከመዘርጋት ባለፈ ወደባንኩ መሄድ ሳያስፈልግ በየዕለቱ ማን እንደከፈለ እና ከየት እንደተከፈለ እንዲሁም የመኖሪያና የንግድ ቤት ኪራይ ገቢ መሆኑን ለመለየት የሚያስችለውን  መተግበሪያ በተመረጠ ኮምፒዩተር በመጫን መከታተል እንዲቻል እንደሚያደርግ ገልጿል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ከዚህ በፊት የባንክ ስቴትመንት ለማምጣት በየሳምንቱ ወደባንኮች በመሄድ የሚባክነውን ጊዜ በማስቀረት የባንክ ስቴትመንቱን ድርጅቱ ራሱ በፈለገበት ሰዓት ፕሪንት አድርጎ መጠቀም እንዲችልም ተደርጓል፡፡

ውሉን የተፈራረሙት የአብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አበረ ሙጬ እና የቡና ባንክ ግሽ  አባይ ቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ አበበ ተፈራ ናቸው፡፡

በቀጣይ ድርጅቱና ቡና ባንክ ከኪራይ ገቢ ባለፈ በኮንስትራክሽን ፋይናንሲንግ ዘርፍ አጋር ሆነው ለመቀጠልም ተስማምተዋል፡፡

Популярное решение на рынке беттинга называют казино Вавада (зеркало казино Вавада), принимающий игроков из большинства стран мира без необходимости включать VPN для получения доступа.