ከጥር 23 እስከ 24 ቀን 2014 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል ሲካሄድ የቆየው ይኸው ስብሰባ በአጠቃላይ አገልግሎት አሰጣጥ እና በባንኩ የግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ውጤቶች ላይ መክሯል።
በውይይቱ ላይ ዓለምአቀፋዊና ሃገራዊ አሉታዊ ክስተቶች በባንክ ኢንደስትሪው በአጠቃላይ ፣ በተለይም በቡና ባንክ የዕቅድ አፈጻጸም ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ ተገምግሟል።
ኢንደስትሪው በገጠመው ገቺ ሁኔታዎች ውስጥም ቢሆን ቡና ባንክ በዕቅድ ከያዛቸው ተግባራት መካከል አብዛኞቹን ማሳካቱ ተገምግሟል።
በባንኩ ድርጅታዊ ባህል አሁናዊ ሁኔታ እና የወደፊት አቅጣጫዎች ፣ በአጠቃላይ ቢዝነስ እድገት ስትራተጂ እንዲሁም በአምስቱ ዓመት የባንኩ ስትራተጂ ዶክመንት አፈጻጸም ላይ መግለጫዎች ቀርበው ሰፊ ውይይቶችም ተካሂደዋል።
በቀጣዩ ስድስት ወራት የተሻለ የዕቅድ አፈጻጸም በማስመዝገብ የባንኩን ዓመታዊ ዕቅድ ከግብ ለማድረስ በሚቻልባቸው ነጥቦች ላይ ምክክር የተደረገ ሲሆን ለዚህ የሚረዱ የማስፈጸሚያ ስልቶች ላይም ጥልቅ ውይይት ተካሂዷል።
በስብሰባው ላይ የባንኩን ዋና መኮንኖች፣ ዳይሬክተሮች እና የዲስትሪክት ሃላፊዎችን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ አመራር አባላቱ ተሳታፊ ነበሩ።