Bunna Bank

ቡና ባንክ ከ ኪ ሃውሲንግ ፋይናንሺያል ሶሉሽን ጋር የአጋርነት ስምምነት ተፈራረመ

ኪ ሃውሲንግ ፋይናንሺያል ሶሉሽን አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ቤት ፈላጊዎች የቤት ባለቤት ለማድረግ የ Key CHF ሞዴል በመቅረጽ ወደስራ የገባ ተቋም ነው። ይህ ተቋም በዕቁብ የመኖሪያ ቤት ለማግኘት የሚመዘገቡ ደንበኞቹ ክፍያቸውን በዝግ ሂሳብ በቡና ባንክ እንዲያስቀምጡ ከቡና ባንክ ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሶ ስራ ጀምሯል።

በቡና ባንክ እና በኪ ሃውሲንግ ፋይናንሺያል ሶሉሽን የተደረሰው በጋራ የመስራት ስምምነት ይፋዊ የፊርማ ስነስርዓት ዛሬ ግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል እና ስፓ ተካሂዷል።

ስምምነቱን ከቡና ባንክ ወገን የባንኩ ቺፍ . ኮርፖሬት ሰርቪስ ኦፊሰር አቶ ለውጤ ጥሩሰው ከኪ ሃውሲንግ ፋይናንሺያል ሶሎሽን መስራችና ስራ አስኪያጅ ጋር ተፈራርመዋል።
በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ አቶ ለውጤ እንደተናገሩት ቡና ባንክ ከተቋሙ ጋር የገባበት ስምምነት በሁለት መንገድ የሚመጡ የደንበኞች ክፍያዎችን በማስቀመጥ የባንክ አገልግሎትን መስጠት ላይ ያተኮረ ነው። ይኸውም ተቋሙ ከደንበኞች የሚሰበስበውን የመኖሪያ ቤት መግዣ ቅድመ ክፍያ እንዲሁም ሌሎች ከግዢው ጋር የተያያዙ ክፍያዎች በደንበኛው ስም በባንኩ በተከፈተ ዝግ ሂሳብ ማስቀመጥና ደንበኛው የቤቱ ባለቤት ሲሆን ለተቋሙ መልቀቅ ፣ እንዲሁም የአገልግሎት ክፍያዎችን በባንኩ በተከፈተ የተቋሙ ተንቀሳቃሽ ሂሳብ መሰብሰብና የተመለደ የባንክ አገልግሎትን መስጠት ላይ ያተኮረ ነው።
በተጨማሪም ቡና ባንክ ከተቋሙ ስራ ጋር የሚሄድና የደንበኞችን የባንክ አገልግሎት ማዘመን የሚያስችሉ ዘመናዊ አሰራሮችን ለመተግበር ዝግጁ መሆኑንም አቶ ለውጤ በስነስርዓቱ ላይ ጠቁመዋል።
ኪ ሃውሲንግ ፋይናንሺያል ሶሉሽን በዕለቱ ከቡና ባንክ በተጨማሪ ከጸሃይ ባንክ እና ከቡና ኢንሹራንስ ጋር ስለገባው ስምምነት ገለጻ አድርጓል። ከአዲስ አበባ ሆቴልና ቱሪዝም ማህበር አባል ሰራተኞችን የቤት ባለቤት ለማድረግ በሚያስችለው አሰራር ዙሪያም ከተቋሙ ሰራተኞች እና ከማርኬቲንግ ኩባንያዎች ጋር ውይይት አድርጓልማርኬቲንግ ኩባንያዎች ጋር ውይይት አድርጓል።

የተቋሙ ስራ የባንክ የኢንሹራንስ አጋርነት ያለው፤ በአነስተኛ ክፍያና አነስተኛ ወርሀዊ ቁጠባ በመቆጠብ ከወለድ ነፃ በሆነ የረዥም ጊዜ አከፋፈል አባላቶቹ የቤት ባለቤት የሚሆኑበት የዕቁብ (የተዘዋዋሪ ፈንድ) ሞዴል ተግባራዊ ያደረገ መሆኑም ተጠቁሟል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

[ivory-search id="5747" title="Custom Search Form"]

This will close in 0 seconds

error: