Branch/ATM Locator   |

Announcement    |

FAQs   |

+25111150861    |

ቡና ባንክ የሦስትዮሽ ስምምነት አደረገ፡፡

ቡና ባንክ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ እና ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር የታክስ ክፍያ አሰራር ስርዓትን በኤሌክትሮኒክስ መተግበሪያ ለማስተዳደር እና ለማዘመን የሦስትዮሽ ስምምነት ጥቅምት 11 ቀን 2015 ዓ.ም በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር መስሪያ ቤት በመገኘት የፊርማ ስነ- ስርዓት አከናወነ፡፡

በሶስትዮሽ ስምምነቱ ቡና ባንክን ጨምሮ 17 የሀገር ውስጥ ባንኮች ተሳትፈዋል ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ገቢዎች ቢሮ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ባበለጸገው “ደራሽ” ዲጅታል መተግበሪያ አማካኝነት ስምምነቱን የሚፈርሙ ባንኮች ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በጋራ የግብር አሰባሰብ ስርዓቱን በማዘመን ውጤታማ እንዲሆን ለማስቻል የተፈጸመ የጋራ ስምምነት ነው፡፡

በፊርማ ስነ- ስርዓቱ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክትር ወይዘሮ ትእግስት ሀሚድ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ተፈራ ተቋማቸውን ወክልው የተፈራረሙ ሲሆን በቡና ባንክ አ.ማ በኩል የባንኩ ቺፍ ኮርፖሬት ሰርቪስ ኦፊሰር አቶ ሙሉነህ አያሌው የሦስትዮሽ ፊርማውን ተፈራርመዋል፡፡

ባንኩ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር ዘመናዊ የክፍያ አሰራር ስርዓትን ለማስፈን ተመሳሳይ የሦስትዮሽ ስምምነት ሲያደርግ፣ በበጀት ዓመቱ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ የተፈጸመ ነው፡፡

ስምምነቱ የዲጅታል ባንኪንግ ስራ እንዲስፋፋ እና የባንኩ ደንበኞች፣ እና ግብር ከፋዮች በአጠቃላይ በኤሌክትሮኒክስ መተግበሪያ በመጠቀም የሚጠበቅባቸውን ግብር በዘመናዊ መንገድ ባሉበት ቦታ ሆነው ክፍያቸውን በቀላሉ እንዲፈጽሙ ያደርጋል፡፡ ጊዜን እና ጉልበትን በመቆጠብ የግብር አሰባሰብ ስርዓቱን እንደሚያዘምንም በስነ- ስርዓቱ ተገልጿል፡፡

Популярное решение на рынке беттинга называют казино Вавада (зеркало казино Вавада), принимающий игроков из большинства стран мира без необходимости включать VPN для получения доступа.