New to site?


Login

Lost password? (X)

Already have an account?


Signup

(X)
Farooq

ቡና ባንክ የውጭ ገንዘብ በባንክ የመነዘሩ ደንበኞቹን ሸለመ

HomeNewsቡና ባንክ የውጭ ገንዘብ በባንክ የመነዘሩ ደንበኞቹን ሸለመ
17
Nov
ቡና ባንክ የውጭ ገንዘብ በባንክ የመነዘሩ ደንበኞቹን ሸለመ
  • Author
    Genet Fekade
  • Comments
    0 Comments
  • Category

• የዕጣ አሸናፊ ደንበኞች ከዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል እስከ ሞባይል ስልክ ቀፎዎች  ባለቤት የሚያደርጋቸው ዕጣ ወጥቶላቸዋልቡና ባንክ ጥቁር ገበያ በኢኮኖሚው ላይ የሚያሳደረውን ተጽዕኖ ለመከላከል በማቀድ የውጭ ገንዘብን በህጋዊ መንገድ መመንዘርን ለማበረታታት የቀረጸው “የውጭ ገንዘብ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ዘጠነኛ ዙር መርሃ ግብር በይፋ በተካሄደ የዕጣ አወጣጥ ስነስርዓት ተጠናቋል።

ህዳር 08 ቀን 2014 ዓ.ም በብሄራዊ ሎተሪ አዳራሽ በተካሄደው የዕጣ አወጣጥ ስነስርዓትም የዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል አሸናፊው ቁጥር 29322 መሆኑ ተረጋግጧል ።  

ባንኩ ላለፉት  ወራት ያካሄደው ይኸው የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ መርሃ ግብር “ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” በሚል መርህ የተካሄደ ሲሆን ደንበኞች ከውጭ ሀገር ከወዳጅ ዘመዶቻቸው በተለያዩ ገንዘብ ማስተላለፊያ ድርጅቶች በኩል ገንዘብ ሲላክላቸውና በቡና ባንክ በኩል ሲቀበሉ እንዲሁም የውጭ አገር ገንዘብ በቡና ባንክ ሲመነዝሩ እድለኛ የሚሆኑበት የሎተሪ መርሃ ግብር ነው፡፡


በዚሁ የሎተሪ ዕጣ አወጣጥ ስነስርአት ወቅት አንደኛ ዕጣ የሆነውን የ2020 ሞዴል ሱዙኪ ዲዛየር መኪና ጨምሮ ዘመናዊ የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች ፣ ፍሪጆች፣የውሃ ማጣሪያዎች፣ ፍላት ስክሪን ቴሌቪዥኖችና ስማርት ስልኮች ለዕድለኞች ደርሰዋል፡፡


በስነስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የቡና ባንክ ­ኢንተርናሽናል ባንኪንግ ዳይሬክተር  አቶ ጠና ሀይለማሪያም እንደተናገሩት አንድ ሃገር በምጣኔ ሃብት ጎልብታ ዜጎቿን ተጠቃሚ ማድረግ የምትችለው ጤናማ የገንዘብ ዝውውር ስርዓት ማስፈን ስትችል መሆኑን ገልጸው የገንዘብ ዝውውር በኢኮኖሚው ውስጥ ገንቢ ሚና እየተወጣ እንዲቀጥል ለማድረግ ደግሞ ባንኮች የማይተካ ድርሻ አላቸው ብለዋል።


ቡና ባንክም በየጊዜው በሚያካሂደው ጥናት ብዙሃኑን ህብረተሰብ ወደባንክ ስርዓት እንዲገባ፣ በዚህም የቁጠባ ባህሉን በማሳደግ ህይወቱን እንዲያሻሽል ለማስቻል የተለያዩ አገልግሎቶችን እየቀረጸ ለጥቅም ሲያውል ቆይቷል። በዚህም ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን በማፍራት ወደራዕዩ ስኬት የሚያደርገውን ግስጋሴ ቀጥሏል ብለዋል።


እንደ ዳይተሬክተሩ ገለፃ ወደሃገራችን ከሚመጣው የውጭ ገንዘብ ውስጥ አብዛኛው ከመደበኛ የባንክ አገልግሎት ይልቅ በተለያየ ምክንያት ወደጥቁር ገበያ የሚገባ በመሆኑ ሃገሪቱ በተደጋጋሚ ጊዜ ለሚገጥማት የውጭ ምንዛሪ እጥረት አንዱ ምክንያት ተደርጎ ሊጠቀስ ይችላል። የውጭ ምንዛሪ እጥረት አንድ ሃገር ለሚያስፈልጋት ማናቸውም የንግድ ልውውጥ ተግባር ከፍተኛ እንቅፋት የሚፈጥር መሆኑን የተናገሩት አቶ ጠና በዚህም ሳቢያ የሚከሰት የገቢ ንግድ መቀዛቀዝ የሸቀጦች ዋጋ መጨመርን ብቻ ሳይሆን የአስፈላጊ ግብዓቶችን እጥረት በመፍጠር የኑሮ ውድነትን እንደሚያባብስና ዜጎችም በመሰረታዊ ግብዓቶች እጥረት ለችግር እንዲጋለጡ ምክንያት እንደሚሆን አብራርተዋል።የውጭ ገንዘቦች ምንዛሪና መቀበል ሂደት በባንክ ብቻ እንዲተገበርና ከጥቁር ገበያ ተጽዕኖ እንዲላቀቅ ፣ በውጤቱም ሃገርና ህዝብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማስቻል ቡና  ባንክ የበኩሉን ሃላፊነት ለመወጣት በተከታታይ ዙሮች ለውጭ ገንዘብ ተቀባዮችና መንዛሪዎች የማበረታቻ ሽልማት በማዘጋጀት የዘመቻ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ነው አቶ ጠና ያስታወቁት።

እስካሁን ባንኩ በዘጠኝ ዙር ባካሄደው “የውጭ ገንዘብ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” መርሃ ግብር በርካቶች በህጋዊ መንገድ የውጭ ገንዘብ እንዲመነዝሩ ከማስቻሉ ባሻገር ወደጥቁር ገበያ የሚገባውን የውጭ ገንዘብ መጠን ለመቀነስ የበኩሉን አስተዋጽዖ ማበርከቱንም አክለው ተናግርዋል።

እንደአቶ ጠና ሀይለማሪያም ገለጻ ቡና ባንክ ባለፉት ዘጠኝ ዙሮች ባካሄደው የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ መርሀግብር ካገኛቸው ልምዶች በመነሳት የባንኩን ደንበኞች የበለጠ ለማበረታታትና ለማትጋት አስረኛውን ዙር የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ  መርሃግብሩን በቅርቡ ይጀምራል፡፡ከ13 ሺህ በላይ በሆኑ ባለአክሲዮኖች የተቋቋመው ቡና ባንክ ከ320 በላይ በደረሱ ቅርንጫፎቹ በመላው ኢትዮጲያ የባንክ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ የግል ባንክ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የደንበኞቹን ቁጥር ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ማድረስ ችሏል። 

Tags:

    Bunna Bank