Branch/ATM Locator   |

Announcement    |

FAQs   |

+25111150861    |

ቡና ባንክ 6ኛውን የህዝብና የጭነት ማመላለሻ ትራንስፖርት ዘርፍ ይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃ ግብር አሸናፊ ደንበኞቹን ይፋ አደረገ

• የዘመናዊ የቤት አውቶሞቢሎች አሸናፊ የሎተሪ ዕጣ ቁጥሮች

    9776731 እና 7537610 ሆነዋል

(አዲስ አበባ መጋቢት 27 ቀን 2014 ዓ.ም)

በተለያየ ስራ ላይ የተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የቁጠባ ባህላቸውን እንዲያሳድጉ ልዩ ልዩ መርሃግብሮችን ቀርጾ ተግባራዊ እያደረገ የሚገኘው ቡና ባንክ በህዝብና ጭነት ማመላለሻ ትራንስፖርት ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ያዘጋጀውን 6ኛ ዙር የቁጠባና ሽልማት መርሃ ግብር በማጠናቀቅ የሎተሪ ዕጣዎቹን መጋቢት 27 ቀን 2014 ዓ.ም በብሄራዊ ሎተሪ አዳራሽ በህዝብ ፊት በይፋ አውጥቷል፡፡ የሽልማቱ አሸናፊዎችም በይፋ ታውቀዋል።

ባንኩ ለአምስት ዙሮች ሲያካሂድ የቆየውንና በመደበኛና ሜትር ታክሲና ባጃጅ ሹፌሮችና ባለንብረቶች ላይ ብቻ የተወሰነውን የይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃ ግብር በማስፋት ወደፈሳሽና ደረቅ ጭነቶች ማመላለሻ እንዲሁም አነስተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ የህዝብ ትራንስፖርት ዘርፍ አሳድጎታል። በዚህም በአጠቃላይ የትራንስፖርት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ባለንብረቶችን፣ አሽከርካሪዎችንና ረዳቶችን ያካተተ የቁጠባ መርሃ ግብር በመዘርጋት የተሳታፊዎችን ቁጥር ከፍ ማድረግ ችሏል።

ለመርሃ ግብሩ የተዘጋጁት ሁለት የ2020 ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢሎች፣ ሁለት ባለሶስት እግር ተሽካርካሪዎች፣ አምስት የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች፣ አምስት ዘመናዊ ማቀዝቀዣዎች፣ አምስት 55 ኢንች ቴሌቪዠኖች፣ አምስት የውሃ ማጣሪያዎች እና አስር ስማርት የሞባይል ስልኮችም በይፋ ዕጣ አወጣጥ ስነስርአት ለዕድለኞች ደርሰዋል፡፡

ባንኩ በአጠቃላይ 34 ደንበኞቹን የሽልማት አሸናፊ አድርጓል።

ቡና ባንክ ላለፉት 12 ዓመታት ቁጠባን ባህል ያደረገ ህብረተሰብ እንዲፈጠር ባደረገው ጥረት ከ1.8 በላይ ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን በማፍራት ጠንካራ ማህበራዊ መሰረት መገንባት ችሏል።

ከግለሰቦች ህይወት ማሻሻል ባሻገር ለሃገር ኢኮኖሚ ግንባታ መሰረታዊ ሚና እንደሚጫወት የሚታመነው ቁጠባ በህብረተሰቡ ዘንድ ባህል እንዲሆን ለማስቻል ቡና ባንክ በየጊዜው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተደራሽ የሚያደርጉ አዳዲስ የቁጠባ ፕሮግራሞችን ከማበረታቻ ሽልማቶች ጋር በመዘርጋት ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የማህበረሰብ ክፍል የባንክ ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል።

ከነዚህ መካከልም በጭነትና በህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የዘረጋው የቁጠባና ሽልማት መርሃ ግብር አንዱ ነው።
የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ነው የሚባለው የትራንስፖርት ዘርፍ የሃገራችን ምጣኔ ሃብት እጅግ አስፈላጊ አካል ከመሆኑ ባሻገር የልማትና ዕድገት ማሳለጫ አይነተኛ መሣሪያም ጭምር ነው። የትራንስፖርት መሠረተ ልማት መስፋፋት ከከፍተኛ የእድገት ደረጃዎች ጋር የተቆራኘ እንደመሆኑ የትራንስፖርት ሥርዓቶች ቀልጣፋ ሲሆኑ ለተሻለ የገበያ ተደራሽነት ፣ ለበርካታ የሥራ ስምሪት እና እንደተጨማሪ ኢንቨስትመንቶች ላሉ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዕድሎች እና ጥቅሞች በር ይከፍታል። ቡና ባንክ የዚህን ዘርፍ ተዋናዮች ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችል የቁጠባና ሽልማት መርሃ ግብር በመዘርጋቱ የበርካታ ደንበኞቹን ህይወት መቀየር ችሏል።

በአሁኑ ወቅት የደንበኞቹን ቁጥር ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ማድረስ የቻለው ቡና ባንክ ከ 13 ሺ በላይ በሆኑ ባለአክሲዮኖች የተቋቋመ ሲሆን ከ336 በላይ በደረሱ ቅርንጫፎቹ በመላው ኢትዮጲያ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ የግል ባንክ ነው ።

Популярное решение на рынке беттинга называют казино Вавада (зеркало казино Вавада), принимающий игроков из большинства стран мира без необходимости включать VPN для получения доступа.