08
Mar
አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በቡና ባንክ
-
AuthorGenet Fekade
-
Comments0 Comments
-
Category


የቡና ባንክ ሴት አመራሮች እና ሰራተኞች ዛሬ አለምአቀፉን የሴቶች ቀን በድምቀት አክብረዋል፡፡
የባንኩ ሴት አመራሮችና ሰራተኞች በኢንተርኮንቲነንታል አዲስ ሆቴል በአሉን ሲያከብሩ ክብርት አርቲስት አለምፀሃይ ወዳጆ በክብር እንግድነት ተገኝተው ለሀገርም ሆነ ለተቋማት ውጤታማነት የሴቶች ሚና በታሪክ ከፍተኛ እንደሆነ ገልፀው ሰራተኞቹን አበረታትተዋል፡፡
በበአሉ ላይ ሴት ቦርድ አመራርን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ቡና ባንክ የሴቶች የቁጠባ ሂሳብን በመክፈት የቁጠባው አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ ሴቶች የተሻለ ወለድ እንዲያገኙ ከማድረጉም ባለፈ ቁጠባን ባህል ያደረጉ ሴቶችን በማበረታታት ጠንካራ ማህበረሰብን ለማፍራት በሚደረገው ጥረት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ያለ ባንክ ነው፡፡
በተጨማሪም ባንኩ የሴት ሰራተኞች ውሳኔ ሰጭነትን ከፍ በማድረግ ለአመራርነት የማብቃት ስራ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡
Tags: