New to site?


Login

Lost password? (X)

Already have an account?


Signup

(X)
Farooq

አራተኛው ዙር የታክሲ እና ባጃጅ ሹፌሮች እና ባለንብረቶች ዕለታዊ የቁጠባ ማበረታቻ ሽልማት ሎተሪ ዕጣ ወጣ

HomeNewsአራተኛው ዙር የታክሲ እና ባጃጅ ሹፌሮች እና ባለንብረቶች ዕለታዊ የቁጠባ ማበረታቻ ሽልማት ሎተሪ ዕጣ ወጣ
20
Aug
አራተኛው ዙር የታክሲ እና ባጃጅ ሹፌሮች እና ባለንብረቶች ዕለታዊ የቁጠባ ማበረታቻ ሽልማት ሎተሪ ዕጣ ወጣ
  • Author
    Genet Fekade
  • Comments
    0 Comments
  • Category

የቤት መኪና አሸናፊው የኮተቤ ቅርንጫፍ ደንበኛ ሆኗል

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ለአራተኛ ጊዜ ያዘጋጀው የታክሲ እና ባጃጅ ሹፌሮች እና ባለንብረቶች ዕለታዊ የቁጠባ ማበረታቻ ሽልማት የሎተሪ ዕጣ ነሀሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ም በብሄራዊ ሎተሪ በዕድል አዳራሽ በህዝብ ፊት በይፋ ወጥቷል፡፡

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ በየአመቱ ከሚያካሂዳቸው የሴልስ ፕሮሞሽን መርሃ ግብሮች መካከል የታክሲ እና ባጃጅ ሹፌሮች እና ባለንብረቶች ዕለታዊ ቁጠባ የማበረታቻ ሽልማት ደንበኞቹን የሚያበረታታበትና የሚያተጋበት አንዱ ሲሆን፤ ባለፉት ሶስት ዙሮች የቆጣቢዎች ቁጥር ዕድገት እያሳዬ የመጣ እና በአራተኛው ዙር የታክሲ እና ባጃጅ ሹፌሮች እና ባለንብረቶች ቆጣቢዎች ቁጥር ወደ 42ሺ 744 መድረሱን እንዲሁም የተቀማጭ ገንዘባቸውም ከ236,478,800.30 በላይ መድረሱ ታውቋል፡፡

የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ተ/ቺፍ ስትራቴጂ ኦፊሰር አቶ መንክር ሃይሉ የእጣ ማውጣት ስነስርዓቱን በይፋ ሲከፍቱ እንደገለጹት፤ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ በአገሪቱ የፋይናንስ ኢንደስትሪ አይነተኛ ሚና በመጫወት ላይ የሚገኝ ባንክ መሆኑንና በዚህ ስኬታማ ጉዞው በመላ አገሪቱ በከፈታቸው ከ242 በላይ ቅርንቻፎቹ ለበርካቶች የስራ እድል በመፍጠርና ህብረተሰቡን በማገልገል በአገሪቱ የፋናንስ ዘርፍ አይነተኛ ሚና በመጫወት ተመራጭና ተወዳጅ ለመሆን የበቃ ህዝባዊ ባንክ ነው ብለዋል፡፡

ባንኩ ከሚሰጣቸው ፈጣን ፤ቀልጣፋና ዘመናዊ የባንክ አገልግሎቶች በተጨማሪ ደንበኞቹን የሚያበረታታበት የሎተሪ ሽልማቶችን በማዘጋጀት በርካቶች የዚህ ሽልማት ተካፋይ እንዲሆኑ ሲያደርግ መቆየቱን የገለጹት አቶ መንክር፤ የታክሲና ባጃጅ ሹፌሮችና ባለንብረቶች ወጣቶች በመሆናቸው የነገ ራዕያቸው የራሳቸውን ተሽከርካሪ ከመግዛት አንስቶ ወደፊት የሚያቅዱትን እድገት መስመር ለማሳካት ከባለራዕዮች ባንክ ጋር መስራታቸው ትክክለኛ ምርጫና ውሳኔ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በዚሁ መሰረትም በትራንስፖርት ዘርፉ ላይ የተሰማሩ ወገኖች የቁጠባ ባህላቸውን እያሳደጉ ከባንኩ ጋር በመስራት ወደ ስኬታቸው እንዲሸጋገሩ ጥሪ ያቀረቡት አቶ መንክር፤በቀጣይ አምስተኛው ዙር የታክሲ እና ባጃጅ ሹፌሮች እና ባለንብረቶች ዕለታዊ ቁጠባን በቅርብ ቀን እንደሚቀጥል እና በሌሎችም ዘርፎች የተለያዩ የቁጠባ መርሃግብሮችን በሴልስ ፕሮሞሽን መርሃ ግብር ተዘጋጅተው ለገበያ እንደሚቀርቡ አስታውቀዋል፡፡

በእለቱ በተካሄደው የእጣ ማውጣት ስነስርዓት በአንደኛ ደረጃ ባለዕድል የሆኑትና የሱዙኪ ዲዛየር መኪና አሸናፊ የሆኑት የቡና ኮተቤ ቅርንጫፍ ደንበኛ ሲሆኑ፤በሁለተኛ ደረጃ የሶስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች አሸናፊ የሆኑት የአዲሱ ገበያ እና የቤተል ቅርንጫፍ ደንበኞች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

የአስር ቅንጡ የሞባይል አፓራተስ አሸናፊ ደንበኞች በቅደም ተከተል የበሻሌ ቅርንጫፍ ሁለት ደንበኞች፤የካህን ሰፈር፤የበላይ ዘለቀ፤የአሰላ፤የአያት፤የአዲግራት፤የባህርዳር ጊዮን፤የመካኒሳ አቦ እና የባህርዳር ቅርንጫፍ ደንበኞች መሆናቸው ተገልጻል፡፡

የሰባተኛው ዘር የውጭ ምንዛሬ ማስገኛ የፕሮሞሽን ሎተሪ እጣ ነሀሴ 16 ቀን የሚጠናቀቅ ሲሆን፤የእጣ ማውጣት ስነስርዓቱም በቅርቡ የሚከናወን መሆኑን ከኮርፖሬት ኮምኒኬሽንና ፕሮሞሽን ዋ/ክ/ ሥራ አስኪያጅ አቶ አበባው ዘውዴ አስታውቀዋል፡፡

Tags:

    Bunna Bank