አዲሱ የቡና ባንክ ብራንድ መሰረታዊ ቀለማት ሁለት ሲሆኑ እነርሱም ‘ማሩን ሬድ’ እና ‘ኮርፖሬት ብሉ’ ናቸው።
እነዚህ ቀለማት የቀይ እና የሰማያዊ ቀለማት ንዑሳን ዘሮች ሲሆኑ ቡና ባንክን የሚገልጹ የብራንድ መለያዎች እንዲሆኑ በጥናት የተመረጡ ናቸው። ለቡና ባንክ አርማም ይሁን ለብራንድ መለያ እንዲሆኑ የተመረጡት ሁለቱ ቀለማት እንደአገባባቸው በስብጥርና በተናጥል ጥቅም ላይ ይውላሉ። የቀለማቱ ትርጉምም የሚከተለውን ይመስላል
- ማሩን ሬድ (የቀይ ቀለም ዘር) የዓላማ ጥንካሬን፣ ጥልቅ የማገልገል ፍላጎትን፣ ለስራ መነሳሳትን የሚወክል ሲሆን
- ኮርፖሬት ብሉ ( የሰማያዊ ቀለም ዘር) የምንጊዜም ታማኝነትን ፣ ለዓላማ ቁርጠኝነትን እና በእውቀት መስራትን ይወክላል
የቡና ባንክ ብራንድ ከነዚህ ሁለት መሰረታዊ ቀለማቱ (primary colors) ባሻገር ለተለያዩ የማስተዋወቂያ አገልግሎቶች በተተኪነት የሚጠቀምባቸው 42 ዝርያ ያላቸው ሰባት ተለዋጭ ቀለማት (secondary colors) አሉት። እነዚህ ቀለማት የተቀዱት ከቡና ፍሬ የህይወት ዑደት ሲሆን ቡና ማፍራት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ደርሶ እስከሚለቀምበት ወቅት ድረስ በየጊዜው የሚኖሩትን ተለዋዋጭ ቀለማት የሚወክሉ ናቸው።