Branch/ATM Locator   |

Announcement    |

FAQs   |

+25111150861    |

አዲሱ የቡና ባንክ ብራንድ አርማ

አዲሱ የቡና ባንክ ብራንድ አርማ ከሶስት ምስሎች የተዋቀረ ነው። እነዚህም ምስሎች ዐይን፣ አድማስ  እና ክብ ቅርጽ ናቸው።

  1. ዐይን

የሎጎው የታችኛው ክፍል የዓይን ቅርጽ አለው። ይህም መንቃትን ይወክላል።መንቃት በአዲስ መንፈስና ጉልበት የመነሳት የመጀመሪያው ምዕራፍ ነው።  ትጋት እና አዲስ ለውጥ ለማየት መዘጋጀት የመንቃት መገለጫዎች ናቸው።

ይህም የቡና ባንክን በአዲስ መንፈስና ጉልበት ለለውጥ መነሳትን ይወክላል።

  • አድማስ

የሎጎው መካከለኛ ክፍል የአድማስ ቅርጽ አለው። አድማስ የአዲስ ቀን ጅማሮና የብሩህ ተስፋ መገለጫ ነው።  በሩቅ የሚታይ ፣ እንደራዕይ መዳረሻነት የሚቆጠር ምልክትም ነው።

ይህም የቡና ባንክን ባለራዕይነት የሚገልጽ ሲሆን  የስኬት መዳረሻውን በአዲስ ጅማሮ፣ በብሩህ ተስፋና በጠንካራ መንፈስ ተልሞ መነሳቱንም ይወክላል።

  • ክብ ቅርጽ

የሎጎው ሙሉ ቅርጽ ክብ ነው። ክብ ቅርጽ ብዙ ሆነን  እንደአንድ  የምንሰባሰብበት፣  የምንመክርበት፣  የምንረዳዳበት፣ ክፉና ደግን የምንካፈልበት ፣ ከትውልድ ትውልድ የተቀባበልነውን ትውፊት፣  ባህል እና ልማዳችንን የሚወክል ምልክት ነው።

ይህም ቡና ባንክ ልክ እንደቡና ስርዓታችን ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በአንድ ዓላማ ጥላ ስር ያሰባሰበ ባንክ መሆኑን፣በዚህ መሰባሰብ ውስጥም  ለእድገት ፣ለብልጽግና እና ለእኩል ተጠቃሚነት በአንድነት በጋራ መቆሙን ይወክላል።

Популярное решение на рынке беттинга называют казино Вавада (зеркало казино Вавада), принимающий игроков из большинства стран мира без необходимости включать VPN для получения доступа.