


በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ የካቲት 29 ‹‹ማርች 8›› የሴቶች ቀን ተብሎ ታስቦ ይውላል። ቡና ባንክ ቀኑን ታሳቢ በማድረግ ‘’women’s development program on the international womens’ day’’ በሚል መሪ ቃል ለባንኩ ሴት ሰራተኞች ስልጠና ሰጥቷል።
ስልጠናው በቡና ባንክ ታለንት ዲቬሎፕመንት ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት የተዘጋጀ ሲሆን፣ BITS Education & consultancy PLC ቀኑን በማስመልከት ‘Adapting in the Digital Age, Empowering Women in the Era of Digital Transformation, Women’s Empowerment, Leadership and Communication’ ርዕስ ጉዳዮች ላይ በባለሞያዎች ስልጠና ለተሳታፊዎች ሠጥቷል።
የስልጠና መርሃ ግብሩን በማስመልከት የባንኩ ቺፍ ኮርፖሬት ሰርቪስ ኦፊሰር የሆኑት አቶ ሙሉነህ አያሌው የመክፈቻ ንግግር እና እንኳን አደረሳቹ መልዕክት ለታዳሚዎች አስተላልፈዋል።
በመርሃ ግብሩ ሴቶችን በማብቃት ዙሪያ ሰፊ የፓናል ውይይት የተደረገ ሲሆን በርካታ ተሳታፊዎችና የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።