New to site?


Login

Lost password? (X)

Already have an account?


Signup

(X)
Farooq

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ የብር ኖቶች ለውጥ ከተጀመረ በኋላ በተከፈቱ የቁጠባ ሂሳቦች ወደ አንድ ነጥብ አንድ ቢሊየን ብር የሚጠጋ ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ መቻሉን አስታወቀ

HomeNewsቡና ኢንተርናሽናል ባንክ የብር ኖቶች ለውጥ ከተጀመረ በኋላ በተከፈቱ የቁጠባ ሂሳቦች ወደ አንድ ነጥብ አንድ ቢሊየን ብር የሚጠጋ ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ መቻሉን አስታወቀ
16
Oct
ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ የብር ኖቶች ለውጥ ከተጀመረ በኋላ በተከፈቱ የቁጠባ ሂሳቦች ወደ አንድ ነጥብ አንድ ቢሊየን ብር የሚጠጋ ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ መቻሉን አስታወቀ
 • Author
  Genet Fekade
 • Comments
  0 Comments
 • Category

 • ባንኩ ገበታ ለሃገርእና ለተማሪዎች ምገባ ፕሮጀክቶች 11 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል

(ጥቅምት  06 ቀን 2013 . አዲስ አበባ) 

ነባሮቹን የብር ኖቶች በአዲሶቹ የመቀየር ስራ ከተጀመረ  በኋላ ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ቅርንጫፎች በተከፈቱ 66 ሺህ በላይ አዳዲስ የቁጠባ ሂሳቦች እስከትናንት ጥቅምት 5 ቀን ድረስ ብቻ ወደ 836 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ መቻሉን አስታወቀ።

መስከረም 4 ቀን 2013 . ይፋ የተጀመረውን  የባለ 10 50 እና 100 ነባር የብር ኖቶች ለውጥና አዲሱን የባለ 200 ብር ኖት የማስተዋወቅ ሃገርአቀፍ እንቅስቃሴ ተከትሎ  ባንኩ በመላው ሃገሪቱ በከፈታቸው 245 ቅርንጫፎቹ አሮጌውን የገንዘብ ኖት በአዲስ የመቀየር እና አዳዲስ የቁጠባ ሂሳብ በማስከፈት ውጤታማ ተግባር ማከናወኑንም ዛሬ በዋና መስሪያ ቤቱ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው  መግለጫ አብራርቷል።

የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንደተናገሩት ባንኩ እስከትናንትናው ቀን ድረስ ከብሄራዊ ባንክ የተላኩለትን 966 ሚሊዮን 200 ሺህ አዳዲስ የብር ኖቶች በፍጥነት በመላው የሃገሪቱ ክፍሎች ወደሚገኙት ቅርንጫፎቹ አሰራጭቷል።

ባንኩ ነባሮቹን የብር ኖቶቹ  በአዲሶቹ ከመቀየር በተጨማሪ 66 ሺህ 828 አዳዲስ የባንክ ቁጠባ ሂሳቦችን ማስከፈት መቻሉን የተናገሩት አቶ ሙሉጌታ ይህም ከዚህ በፊት ከነበረው የቁጠባ ሂሳብ አከፋፈት ልምድ ጋር ሲነጻፀር የ49 በመቶ እድገት ያሳየ መሆኑን ተናግረዋል።

የብር ኖቶች ለውጥ ከተጀመረበት ቀን አንስቶ በተከፈቱት አዳዲስ የባንክ ሂሳቦች ውስጥ 835 ሚሊዮን 956 ሺህ 863 ብር ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን ይህ አፈጻፀም ከዚህ ቀደም ከነበረው ልምድ  ጋር ሲነጻፀር  የ52 በመቶ እድገት ማሳየቱን አብራርተዋል፡፡

እንደዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ ገለጻ ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ከብሄራዊ ባንክ የተላኩለትን አዳዲስ የብር ኖቶች በስሩ ለሚገኙት ሁሉም ቅርንጫፎች በፍጥነት በማዳረስ  ህብረተሰቡ ነባሩን የብር ኖት ያለምንም  ውጣ ውረድ በአዲሱ እንዲቀይርና የቁጠባ ሂሳብ በመክፈትም ገንዘቡን እንዲያስቀምጥ ማድረግ ችሏል ብለዋል ሁሉም የኤቲኤም ማሽኖቹም በአዲሱ የብር ኖት እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።

አዲሱ የብር ለውጥ በገበያ ውስጥ ያለው የገንዘብ ዝውውር ህጋዊ የባንክ ስርዓትን እንዲከተል ከማገዙ በተጨማሪ ባንኮች ህብረተሰቡ የቁጠባ እና ባንክ አጠቃቀም ባህል እንዲዳብር በማስቻል ረገድ የድርሻቸውን እንዲወጡ አድርጓቸዋ ነው ያሉት አቶ ሙሉጌታ

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ በገንዘብ ቅያሬው ላይ ትኩረት ሰጥቶ በሁሉም ቅርንጫፎቹ እያካሄደ በሚገኘው ጠንካራ እንቅስቃሴም  እስካሁን  1 ቢሊየን 785 ሚሊዮን 601 ሺህ ብር ነባር የብር ኖቶችን ለብሄራዊ ባንክ ገቢ ማድረግ መቻሉንም ገልፀዋል

በአፈጻፀም ረገድ የገንዘብ ለውጡ የባንኩን ደንበኞች ቁጥር በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ 7 ነጥብ 7 በመቶ በላይ ማሳደግ ሲችል የቁጠባ ገንዘብ መጠኑንም ወደ 7 በመቶ ከፍ አድርጎታል ብለዋል።

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ በብሄራዊ ባንክ በወጣው መመሪያ መሰረት የጊዜ ገደቡ እስኪጠናቀቅ ድረስ አዳዲስ የብር ኖቶችን የማሰራጨትና አሮጌዎቹን የማሰባሰብ ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልፀዋል፡፡

በተያያዘ ዜናም ባለፉት ዓመታት በሃገሪቱ የሚካሄዱ የልማት ፕሮጀክቶችን በመደገፍ የኮርፖሬት ማህበራዊ ሃላፊነቱን ሲወጣ የቆየው ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ዘንድሮም  የተመሰረተበትን 11 ዓመት ምክንያት በማድረግ በሃገርአቀፍ ደረጃ ይፋ ለተደረገውየገበታ ለአገር ፕሮጀክት 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን ዋና ስራ አስፈጻሚው ይፋ አድርገዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ባንኩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ተቀርጾ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ላለው የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራምና የትምህርት ግብዓቶች ማሟያ  የሚውል የአንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉንም አቶ ሙሉጌታ ጨምረው ገልጸዋል።ባንኩ የሚያደርጋቸው መሰል ድጋፎች ወደፊትም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ላለፉት 11 ዓመታት በመላው የሃገሪቱ አካባቢዎች በሚገኙ 245 ቅርንጫፎቹ ለደንበኞቹ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ የግል ባንክ ነው።

Tags:

  

  ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ የ11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 4ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ
  

  በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ አንቀጽ 418፣ 419 እና 423 እንዲሁም በባንኩ መመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 11.3.7 እና በመተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 6.3 መሠረት የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 4ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ ታህሳስ 11 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ ጦርሃይሎች አካባቢ በሚገኘው ጎልፍ ክለብ ውስጥ ይካሄዳል፡፡

  ስለሆነም የባንኩ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም በሕጋዊ ተወካዮቻችሁ አማካኝነት በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ ጉባኤው ላይ እንድትገኙ ባንኩ በአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡

  የ4ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

  1) ረቂቅ አጀንዳዎችን ማጽደቅ፣

  2) በባንኩ የመመስረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ

  3) የጉባኤውን ቃለ-ጉባኤ ማጽደቅ

  የ11ኛ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

  1) ረቂቅ አጀንዳዎችን ማጽደቅ፣

  2) በባንኩ ውስጥ የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን እና የአዲስ አክሲዮኖችን ሽያጭ መርምሮ ማጽደቅ፣

  3) እ.ኤ.አ የ2019/20 የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ፣

  4) እ.ኤ.አ የ2019/20 የውጭ ኦዲተሮች ቦርድ ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርትን ማዳመጥ፣

  5) በተራ ቁጥር 3 እና 4 የቀረቡትን ሪፖርቶች ተወያይቶ ማጽደቅ፣

  6) የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማ እና ምርጫ አፈፃፀም የአሰራር ደንብ ማሻሻያን መርምሮ ማጸደቅና የአስመራጭ ኮሚቴ አባላት አበልን መወሰን፣

  7) የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴን መምረጥ፣

  8) እ.ኤ.አ የ2020/21 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ አበልና ዓመታዊ ክፍያ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣

  9) እ.ኤ.አ የ2020/21 በጀት ዓመት የውጭ ኦዲተሮችን ሹመት ማጽደቅና አበል መወሰን፣

  10) በዘመኑ የተጣራ ትርፍ አደላደል እና አከፋፈል ላይ የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ መወሰን፣

  11) የጉባኤውን ቃለ-ጉባኤ ማጽደቅ፣ የሚሉት ናቸው፡፡

  ማሳሰቢያ

  1. በጉባኤው ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች አግባብነት ካለውና ሕጋዊ ውክልና መስጠት ከሚችል የመንግሥት አካል የተሰጠ’ በስብሰባው ላይ ለመገኘትና ድምጽ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ሰነድ ወይም ከስብሰባው ሶስት ቀን ቀደም ብሎ ቦሌ መንገድ ከወሎ ሰፈር አደባባይ ቀጥሎ ርዋንዳ መታጠፊያ ከመድረሱ በፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 4ኛ ፎቅ የባንኩ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድርስ በመቅረብ የውክልና ፎርም (ቅጽ) በመሙላት፣ ሌላ ሰው በመወከል የውክልና ሰነዱን ወይም ቅጹን ዋናውንና አንድ ቅጂ ይዘው በመምጣት በጉባዔው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እናስታውቃለን፡፡

  2. ባለአክስዮኖችም ሆኑ ህጋዊ ወኪሎቻቸው ወደ ስብሰባው ቦታ ሲመጡ የራሳቸውንም ሆነ የተወካዮቻቸውን ሕጋዊ የታደሰ መታወቂያ ካርድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን መያዝ አለባቸው፡፡

  3. ባንኩ የባለአክሲዮኖችን የመለያ ቁጥር ባስመዘገባችሁት ተንቀሳቃሽ ስልክ የሚልክ ሲሆን& ይህንኑ ቁጥር በስብሰባው ዕለት ይዛችሁ እንድትመጡ በአጽንኦት እንጠይቃለን፡፡

  4. ከላይ በተ.ቁ. 2 ላይ የተገለፀውን የወካዩን ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሚያረጋግጥ ሕጋዊና የታደሰ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ኮፒ ይዘው የማይመጡ ተወካዮች በጉባኤው ላይ መሳተፍ የማይችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡ በተጨማሪም የድርጅት ተወካዮች ድርጅቱን ወክለው በስብሰባው እንዲገኙና ድምጽ እንዲሰጡ መወከላቸውን የሚያረጋግጥ የተመዘገበ ቃለ-ጉባዔ ወይም በውል አዋዋይ ፊት የተሰጠ ውክልና ዋናውን እና ኮፒውን ይዘው መቅረብ ያለባቸው መሆኑን እናስታውቃለን፣፡

  5. የብሄራዊ ባንክ ያስቀመጠውን የውክልና አሰጣጥ መጠን ገደብ ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ለጊዜው ያነሳ በመሆኑ ወረርሽኙን ለመከላከል ሲባል ባለአክሲዮኖች በጉባዔው በውክልና እንዲሳተፉ ይበረታታሉ፡፡

  6. ተጨማሪ መረጃ ቦሌ መንገድ ከወሎ ሰፈር አደባባይ ቀጥሎ ወደሩዋንዳ መታጠፊያ ከመድረሱ በፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ 0111580880 / 262822 / 262810 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

  የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ

  የዳይሬክተሮች ቦርድ

  ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ

  የባለራዕዮች ባንክ!!!

  Bunna Bank