ቡና ባንክ እ.ኤ.አ. በ2009 ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተሰጠው ፈቃድ የተመሠረተ የግል ባንክ ነው። ባንካችን ፈጣን ዕድገት በማስመዝገብ በአገሪቱ ውስጥ ካሉ ጠንካራ የግል ባንኮች አንዱ ለመሆን በቅቷል። ከ5.1 ቢሊዮን ብር በላይ የተከፈለ ካፒታል እና ከ14,000 በላይ ባለአክሲዮኖች ያሉት ባንካችን፣ ለባለራዕይ ደንበኞቻችን ስኬት ፈጠራ የታከለባቸው የፋይናንስ መፍትሄዎችን በማቅረብ ታማኝ አጋር ለመሆን ቁርጠኛ ነው።
ለላቀ ውጤት እንተጋለን – ደንበኞቻችንን የእሴቶቻችን ማዕከል በማድረግ፣ በላቀ የሙያ ብቃትና እንክብካቤ እናገለግላቸዋለን። ከ4,000,000 በላይ ደንበኞች ያሉትና ቁጥሩም በየጊዜው እየጨመረ የመጣው ባንካችን፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ሕዝብን መሠረት ካደረጉ የግል ባንኮች በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው።
ራዕያችን
እ.ኤ.አ. በ2030 በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ቀዳሚ ሶስት የፋይናንስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አንዱ መሆን ነው።
ተልዕኮአችን
ከአጋሮቻችን ጋር በመተባበር ዘመኑን የዋጀ የፋይናንስ አገልግሎት መስጠት፣ ለዋና ዋና ባለድርሻ አካላት የሚሰጠውን እሴት ከፍ ማድረግ እና የሕዝብን አመኔታ ማትረፍ ሲሆን ይህንን ግብ በተወዳጁ የቡና መገለጫችን፣ በዲጂታል እውቀት በበለፀጉ ባለሙያዎቻችን እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች በመደራጀት ለማሳካት ቁርጠኞች ነን።
መሠረታዊ እሴቶቻችን
01 አሸናፊነት (WINNING) ለላቀ ደረጃ በመትጋት እና ከፍተኛ የሙያ ብቃትን በተግባር በማዋል፣ በዘርፉ ውስጥ ያለውን ውድድር በሙያዊ ስነ-ምግባር ታጅበን እንደምናሸንፍ ፅኑ እምነት አለን።
02 መከባበር (RESPECT) ለእያንዳንዳችን የልዩነት እሴት፣ ለደንበኞቻችን፣ ለባለአክሲዮኖቻችን፣ ለራሳችን፣ ለአቅራቢዎቻችን እና ለማህበረሰባችን የምናበረክተውን አስተዋጽኦ እናከብራለን። እያንዳንዱ ባለድርሻ አካል አስፈላጊ መሆኑን እና የራሱ ሚና እንዳለው እንገነዘባለን።
03 ኃላፊነት (RESPONSIBILITY) የባለድርሻ አካላቶቻችንን ፍላጎት በተገቢው መጠን ለማሟላት በኃላፊነት ስሜት እንሠራለን።
04 ትብብር (COLLABORATION) ደንበኞቻችንን፣ ባለአክሲዮኖቻችንን፣ ተቆጣጣሪ አካላትን እና ማህበረሰቡን ስናገለግል መደጋገፍ፣ መተባበር እና መተሳሰብ ላይ ትኩረት እናደርጋለን።
05 ፈጠራ (INNOVATION) የወደፊቱን ጊዜ አስቀድሞ ለመቅረጽ አዳዲስና ቀዳሚ የሆኑ የፈጠራ ሃሳቦችን ያለማቋረጥ እንከተላለን።
