በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ አንቀፅ 366/1/፣ 367/1/፣ 370፣ እና በባንኩ መመስረቻ ፅሑፍ አንቀፅ 21 እና 22 መሰረት የቡና ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 16ኛ መደበኛ እና 7ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ህዳር 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል ስለሚያካሂድ፤ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ተወካዮች በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ በጉባዔው ላይ እንድትገኙ የማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ የአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡
- አክሲዮን ማህበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች፣
- የአክሲዮን ማህበሩ ስም፡- ቡና ባንክ አክሲዮን ማህበር፣
- የአክሲዮን ማህበሩ ዓይነት፡- የባንክ ሥራ ላይ የተሰማራ አክሲዮን ማህበር፣
- የአክሲዮን ማህበሩ የተፈረመና የተከፈለ ዋና ገንዘብ /ካፒታል/፡- 5,054,935,700 ብር፣
- የአክሲዮን ማህበሩ የምዝገባ ቁጥር፡-AR/AA/3/0003357/2006፣
- የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መ/ቤት አድራሸ፡-አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የቤት ቁጥር አዲስ፣
ድረ ገጽ፡ http://www.bunnabanksc.com/
- የ16ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፣
- በባንኩ ውስጥ የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን እና ሽያጭ ማጽደቅ፤
- እ.ኤ.አ የ2024/25 የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥና መወሰን፤
- እ.ኤ.አ የ2024/25 የውጭ ኦዲተሮችን ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርት ማዳመጥና ማጽደቅ፤
- በ2024/25 ሒሳብ ዓመት የተጣራ ትርፍ ክፍፍል ላይ መወሰን፤
- እ.ኤ.አ የ2025/26 ሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ አበልና እ.ኤ.አ የ2024/25 ሒሳብ ዓመት ዓመታዊ ክፍያ መወሰን፤
- የጉባዔውን ቃለጉባዔ ማጽደቅ፣ የሚሉት ናቸው፡፡
- የ7ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፣
- የባንኩን ካፒታል ለማሳደግ በቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ላይ መወሰን፣
- የባንኩን የመመስረቻ ጽሁፍ ማሻሻያ ማጽደቅ፣
- የጉባዔውን ቃለጉባዔ ማጽደቅ፣ የሚሉት ናቸው፡፡
ማሳሰቢያ
- በጉባዔው ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ስልጣን ባለው አካል የተሰጠ የውክልና ሰነድ ወይም በንግድ ህግ አንቀጽ 377 መሰረት ጉባዔው ከመካሄዱ ሦስት ቀን በፊት በባንኩ ዋና መ/ቤት አክሲዮን አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ በባንኩ የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ በመሙላትና በመፈረም ተወካይ መሾምና ተወካዩም የውክልና ማስረጃውን በመያዝ የጉባዔው ተካፋይ ለመሆንና ድምጽ ለመስጠት የሚችል መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡ ሆኖም አንድ ባለአክሲዮን በማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ በማንኛውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ሰው ብቻ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
- የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን የሚያሳይ የብሔራዊ መታወቂያ / ፋይዳ/ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ዋናውንና ኮፒ በመያዝ በጉባዔው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የሆኑ የውጪ ዜግነት ያላቸው ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈበት መታወቂያ/ቢጫ ካርድ/ ይዘው እንዲቀርቡ እናሳውቃለን፡፡ የድርጅትና የማህበር ተወካዮች ድርጅቱን/ማህበሩን ወክለው በስብሰባው እንዲገኙና ድምፅ እንዲሰጡ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዘው መቅረብ ያለባቸው መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
- የሚወከሉ ባለአክሲዮኖች የሚቀበሉት የውክልና መጠን የራሳቸውን አክሲዮን ጨምሮ ከባንኩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ ከአስር በመቶ /10% / መብለጥ የለበትም፡፡
- ባለአክሲዮኖች በስራ ላይ ያሉ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትና ሰራተኞች በባለአክሲዮኖች ጉባዔ ላይ እንዲሳተፉና ድምጽ እንዲሰጡ መወከል አይችሉም፡፡
- የጉባዔው ቦታ ከሲኤም ሲ ቤቶች በተቃራኒ ከፀሐይ ሪል ስቴት አጠገብ ወደወሰን መሄጃ በስተግራ በኩል የሚገኘው አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል መሆኑን ያስታውሱ፡፡ የጉግል ማፕ ማስፈንጠሪያውን በመጫን ያገኛሉ፡፡ https://maps.app.goo.gl/doGA9Ly9QpzfezeBA
የቡና ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ
