New to site?


Login

Lost password? (X)

Already have an account?


Signup

(X)
Farooq

የቡና ባንክ ኢንተርናሽናል ባንኪንግ ዳይሬክተር አቶ ጠና ሀይለማሪያም በ9ኛው ዙር “የውጭ ገንዘብ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” እጣ አወጣጥ ስነስርአት ላይ ያደረጉት ንግግር

HomeNewsየቡና ባንክ ኢንተርናሽናል ባንኪንግ ዳይሬክተር አቶ ጠና ሀይለማሪያም በ9ኛው ዙር “የውጭ ገንዘብ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” እጣ አወጣጥ ስነስርአት ላይ ያደረጉት ንግግር
18
Nov
የቡና ባንክ ኢንተርናሽናል ባንኪንግ ዳይሬክተር አቶ ጠና ሀይለማሪያም በ9ኛው ዙር “የውጭ ገንዘብ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” እጣ አወጣጥ ስነስርአት ላይ ያደረጉት ንግግር
 • Author
  Genet Fekade
 • Comments
  0 Comments
 • Category

ህዳር   08  ቀን 2014 . አዲስ አበባ 

 • የተከበራችሁ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ሰራተኞ
 • የተከበራችሁ የቡና ባንክ የስራ አመራር አባላ
 • የተከበራችሁ የዘጠነኛው ዙር “የውጭ ምንዛሬ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ ይሸለሙ” ፕሮግራም ተሳታፊዎ
 • እንዲሁም ይህንን ኹነት ለመዘገብ እዚህ የተገኛችሁ የሚዲያ ባለሙያዎች

በቅድሚያ ሁላችሁም ጥሪያችንን አክብራችሁ በዚህ ፕሮግራም ላይ በመገኘታችሁ ምስጋናዬን ማቅረብ እወዳለሁ።

ክቡራትና ክቡራን

በኢትዮጲያ ውስጥ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚው ህብረተሰብ ቁጥር ከአጠቃላዩ ህዝብ አንጻር ሲለካ ያለው ክፍተት ሰፊ በመሆኑ የህዝቡን የባንክ አጠቃቀም ባህል ማሳደግ ከፍ ያለ ስራ የሚጠይቅ ሃላፊነት ነው። በአንጻሩም  ባንኮች የሚሰጡት አገልግሎት ይህንን ክፍተት ለማጥበብ ወሳኝ በመሆኑ ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ እና ለሁሉም ተደራሽ የሆነ አገልግሎት አሰጣጥን ማጠናከርም  ግድ ነው።

ወደሃገራችን ከሚመጣው የውጭ ገንዘብ ውስጥ አብዛኛው ከመደበኛ የባንክ አገልግሎት ይልቅ በተለያየ ምክንያት ወደጥቁር ገበያ የሚገባ በመሆኑ ሃገሪቱ በተደጋጋሚ ጊዜ ለሚገጥማት የውጭ ምንዛሪ እጥረት አንዱ ምክንያት ተደርጎ ሊጠቀስ ይችላል። የውጭ ምንዛሪ እጥረት አንድ ሃገር ለሚያስፈልጋት ማናቸውም የንግድ ልውውጥ ተግባር ከፍተኛ እንቅፋት የሚፈጥር መሆኑም ግልጽ ነው :: ይህም የሸቀጦች ዋጋ መጨመርን ብቻ ሳይሆን የአስፈላጊ ግብዓቶችን እጥረት በመፍጠር የኑሮ ውድነትን በማባባስ ዜጎች ለችግር እንዲጋለጡ ምክንያት ይሆናል፡፡

በባንክ አገልግሎት ዘርፍ 12 ዓመታት ያስቆጠረው ቡና ባንክ የሃገራችንን የቁጠባ ባህል ለማሳደግ እና ዘመናዊ የባንክ አገልግሎቶችን ለመስጠት በአዲስ አበባና በሁሉም የሃገራችን አካባቢዎች 320 ቅርንጫፎችን ከፍቶ አገልግሎቱን ተደራሽ በማድረግ ላይ ይገኛል።

የቡና ባንክ ደንበኞች ከውጭ የሚላክላቸውን የውጭ ምንዛሪ በባንኩ በኩል ሲቀበሉ የውጭ ምንዛሪ መቀበልም ሆነ መመንዘር ህጋዊ የባንክ ስርዓትን እንዲከተል በማድረግ የጥቁር ገበያን ተጽዕኖ ለመቀነስ ላበረከቱት አስተዋዕዖ “ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ.፣ ይሸለሙ” በሚል መሪ ቃል የማበረታቻ ሽልማቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ አሰራር ዘርግቶ ተግባራዊ ሲያደርግ ቆይቷል። በዚህም በስምንት ዙሮች በርካታ እድለኞች የዘመናዊ አውቶሞቢሎችን ጨምሮ የግል እና የቤት ውስጥ መገልገያ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ተሸላሚ ለመሆን በቅተዋል።

ዛሬም እንደቀደሙት ጊዜያት ሁሉ በቡና ባንክ 9ኛ ዙር “የውጭ ምንዛሬ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ ይሸለሙ” ፕሮግራም ለተሳተፉ ደንበኞች ባንካችን ያዘጋጃቸውን የ2020 ሱዙኪ የቤት አውቶሞቢል፣ ማቀዝቀዣዎች፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች፣ የፍላት ስክሪን ቴሌቪዠኖች፣ የውሃ ማጣሪያዎች፣ እና ዘመናዊ የስልክ ቀፎ ማበረታቻ ሽልማቶች ዕጣ ይወጣል።

ዕጣ የወጣላቸውም ሆነ ያልወጣላቸው በዚህ መርሃ ግብር ውስጥ ተሳታፊ የነበሩ ደንበኞቻችን በእጃቸው የገባ የውጭ ገንዘብን በህጋዊ መስመር በባንክ በኩል በመመንዘር ህገወጥነትን ለመከላከል ላደረጉት ጥረት ቡና ባንክ የከበረ ምስጋናውን ሊቸራቸው ይወዳል። በቅርቡም ባንካችን አስረኛውን ዙር የውጭ ምንዛሪ ይቀበሉ ይመንዝሩ ይሸለሙ ፕሮግራም ከበርካታና አጓጊ ሽልማቶች ጋር ለመጀመር  ተዘጋጅቷል።ደንብኞቻችን እንደወትርው ሁሉ በዚህ ፕሮግራማችን ላይ በንቃት እንደሚሳተፉም እምነታችን የጸና ነው።

ክቡራትና ክቡራን

ቡና ባንክ አ.ማ ከ12 ዓመታት በፊት የተቋቋመና ከ320 በላይ በደረሱ ቅርንጫፎቹ በኢትዮጵያ ሁሉም ክልሎች አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ የግል ባንክ ሲሆን ከ13ሺህ በላይ በሆኑ ባለአክሲዮኖች ባለቤትነት የሚተዳደርና በሃገሪቱ ከሚገኙ ባንኮች ውስጥ የብዙሃን ባንክ ተብሎ በመጠራት በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ የግል ባንክ ነው።

ቡና ባንክ ከ 1.5 ሚሊዮን በላይ ለደረሱ ደንበኞቹ ቀልጣፋ የባንክ አገልግሎት በመስጠትና በየጊዜው አዳዲስ ደንበኞችን በማፍራት በብዙ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ተዓማኒነትን ያተረፈ ባንክ ነው።

በመጨረሻም በባንኩ ስራ አመራር አካላት ስም  እዚህ ብሄራዊ ሎተሪ አዳራሽ በህዝብ ፊት በወጣው እጣ እድለኛ የሆናችሁትን ደንበኞቹን በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ። ወደፊትም ባንካችን የባለራዕዮች ባንክ ነውና ለጋራ ራዕያችን መሳካት ከባንኩ ጋር ያላችሁን ደንበኝነት በማጠናከር የአገልግሎቶቹ ተጠቃሚ አንድትሆኑ፣ ከወዳጅ ዘመዶቻችሁ ጋር በጋራ በመሆን በቡና ባንክ ቤተሰብነታችሁም እንድትቀጥሉ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

አመሰግናለሁ

Tags:

  Bunna Bank