Branch/ATM Locator   |

Announcement    |

FAQs   |

+25111150861    |

የቡና ባንክ የስራ አመራር ከፌዴራል የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ጋር በጋራ ለመስራት በሚቻልባቸው የትብብር መስኮች ላይ መክሯል።

በፌዴራል ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ቢሮ በተካሄደው በዚሁ ምክክር ላይ የቡና ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ እንደተናገሩት ቡና ባንክ በቀዳሚነት የዘረጋውና የትራንስፖርት ዘርፍ ተዋንያን የባንክ ተጠቃሚ በመሆን በቁጠባ ህይወታቸውን እንዲለውጡ የሚያስችለው የቁጠባና ሽልማት መርሃ ግብር የዘርፉን ተዋንያን በመጥቀም ረገድ ውጤት አስገኝቷል ብለዋል።

ትራንስፖርት የማንኛውም ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት እንደመሆኑ ቡና ባንክ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራባቸው መስኮች አንዱ ነው ያሉት አቶ ሙሉጌታ ባንኩ ወደፊትም ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በመተባበር የተጀመረውን ስራ በዲጂታል አማራጮች ጭምር በመታገዝ በተጠናከረና በላቀ መልክ ለማስቀጠል ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።

የባንኩ ዋና የስትራተጂ መኮንን አቶ መንክር ሃይሉ በበኩላቸው ቡና ባንክ በትራንስፖርት ዘርፍ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ያለ ባንክ መሆኑን በመግለጽ ከባህር ትራንዚት እና ሎጀስቲክስ አገልግሎት፣ ከኢትዮ ጂቡቲ ባቡር አገልግሎት እና ከፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ አገልግሎት ድርጅቶች ጋር ያለውን የስራ ግንኙነት በአብነት አንስተዋል።

ቡና ባንክ በታክሲ አገልግሎት ሰጪዎች ላይ ተወስኖ የቆየውን የትራንስፖርት ዘርፍ ቁጠባ እና ሽልማት ዘርፍ መርሃ ግብር ወደከተማና ሃገር አቋራጭ አውቶቡሶች እንዲሁም የደረቅና ፈሳሽ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ በማሳደግ በዘርፉ የሚሰጠውን ሁሉን አቀፍ የባንክ አገልግሎት በብቃት ለማዳረስ በትጋት እየሰራ ነው ብለዋል።

የፌዴራል የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊ ሞገስ በምክክሩ ላይ እንደገለጹት መስሪያ ቤታቸው እንደቡና ባንክ ካሉ የትራንስፖርት ዘርፍን ለማሳደግ ትኩረት ሰጥተው ከሚሰሩ የግል ተቋማት ጋር ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት አለው ብለዋል።

ሚኒስቴሩ ከባንኩ ጋር አስቀድሞም ለአቅራቢዎች ከሚሰጥ ብድር ጋር በተያያዘ የስራ ግንኙነት እንደነበረው በመግለጽ በወቅቱ ቡና ባንክ ለነበረው ፈጣንና አጥጋቢ ምላሽ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

ሚኒስቴሩ ወደፊት በትራንስፖርት ዘርፍ ላይ ለውጥ ለማምጣት መጠነ ሰፊ ተግባራት በማከናወን ላይ መሆኑን ያብራሩት ወይዘሮ ዳግማዊት ቡና ባንክ እና የስራ አመራር አባላቱ ዘርፉን ለማሳደግና ተደጋግፎ ለውጤት ለመብቃት ለሰጡት ከፍ ያለ ትኩረትና እያከናወኑት ላለው ተጨባጭ ተግባርም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

እርሳቸው የሚመሩት የፌዴራል ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ከቡና ባንክ ጋር ያለውን የስራ ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ቃል የገቡት ሚኒስትሯ ከሁለቱም ተቋማት ቡድን ተዋቅሮ ቀጣይ ተግባራትን እና የትብብር መስኮችን እንዲለይ እና ወደስራ እንዲገባም አቅጣጫ ሰጥተዋል።

Популярное решение на рынке беттинга называют казино Вавада (зеркало казино Вавада), принимающий игроков из большинства стран мира без необходимости включать VPN для получения доступа.