New to site?


Login

Lost password? (X)

Already have an account?


Signup

(X)
Farooq

የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ቺፍ ስትራተጂ ኦፊሰር አቶ መንክር ሃይሉ ዛሬ በተካሄደው የሽልማት ስነስርአት ላይ ያደረጉት ንግግር

HomeNewsየቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ቺፍ ስትራተጂ ኦፊሰር አቶ መንክር ሃይሉ ዛሬ በተካሄደው የሽልማት ስነስርአት ላይ ያደረጉት ንግግር
27
Oct
የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ቺፍ ስትራተጂ ኦፊሰር አቶ መንክር ሃይሉ ዛሬ በተካሄደው የሽልማት ስነስርአት ላይ ያደረጉት ንግግር
  • Author
    Genet Fekade
  • Comments
    0 Comments
  • Category

(ጥቅምት  17 ቀን 2013 . አዲስ አበባ) 

ክቡራን የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ደንበኞችና እድለኞች

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ለሰባተኛ ዙር ሲያካሂድ በቆየው የውጭ ምንዛሬ “ይቀበሉ ይሸለሙ” ፕሮግራም እና ለአራተኛ ዙር ባካሄደው የታክሲና ባጃጅ የሹፌሮችና ባለንብረቶች የቁጠባ መርሃ ግብር ፕሮግራም ማጠናቀቂያ  ላይ ሽልማታችሁን ለመቀበል እዚህ በመገኘታችሁ ሁላችሁንም እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ።

የባለራዕዮች ባንክ የሆነው  ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ የሃገራችንን የቁጠባ ባህል ለማሳደግ እና ዘመናዊ የባንክ አገልግሎቶችን በስፋት ተደራሽ ለማድረግ በአዲስ አበባና በሁሉም የሃገራችን አካባቢዎች 248 ቅርንጫፎችን ከፍቶ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ የህዝብ ባንክ ነው።

በባንክ አገልግሎት ዘርፍ 11 ዓመታት በማስቆጠር የካበተ ልምድ ያለው ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ለደንበኞቹ ምቹና ቀላል አማራጮችን በመፍጠር የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያደርገው ጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ የቁጠባ ባህል እንዲዳብር እና የገንዘብ ዝውወር ህጋዊ መሰረት ይዞ ለታለመው ግለሰባዊና ሃገራዊ ጥቅም እንዲውል ለማስቻል መጠነ ሰፊ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል።

በዚህም የተለያዩ ዘመናዊና ተደራሽ የባንክ አገልግሎቶችን በማቅረብ ክቡራን ደንበኞቹ በቀላሉ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አሰራር በማዳረስ ላይ ይገኛል።  ከነዚህ አገልግሎቶች አንዱ  “ይቀበሉ ይሸለሙ” በሚል መርሃ ግብር ያዘጋጀው  አገልግሎት ነው።

ይህ አገልግሎት ደንበኞች ከውጭ የሚላክላቸውን የውጭ ምንዛሪ በባንኩ በኩል እየተቀበሉ በአንድ በኩል የውጭ ምንዛሪ መቀበልም ሆነ መመንዘር ህጋዊ የባንክ ስርዓትን እንዲከተል የበኩላቸውን ሚና በመጫወት  የሃገርን ኢኮኖሚ እንዲያሳድጉ፣ በሌላ በኩልም ደንበኞች በባንኩ የውጭ ምንዛሪ ሲቀበሉም ሆነ ሲመነዝሩ ባንኩ ያዘጋጀላቸውን የማበረታቻ ሽልማቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተዘረጋ አሰራር ነው።

ይህ “የይቀበሉ ይሸለሙ” መርሃ ግብር ላለፉት ሰባት ዙሮች የተካሄደ ሲሆን በርካታ የባንኩን ደንበኞች በባንኩ ቅርንጫፎች በኩል የውጭ ምንዛሪ ሲቀበሉም ሆነ ሲመነዝሩ  በሚሰጣቸው የዕጣ ኩፖን የተሽከርካሪዎችና የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ሽልማቶች እድለኛ ሆነውበታል።

የዛሬው 7ኛ ዙር የይቀበሉ ይሸለሙ ፕሮግራም  በብሄራዊ ሎተሪ በተካሄደው ይፋ የዕጣ አወጣጥ ስነስርዓት መሰረት እጣ ለወጣላችሁ እድለኞች የተዘጋጀውን የሱዙኪ የቤት አውቶሞቢል፣ የፍላት ስክሪን ቴሌቪዠኖችና የሳተላይት ዲኮደሮች ሽልማት  በማስረከብ ይጠናቀቃል። የዚህ ፕሮግራም ስምንተኛ ዙር በቅርቡ የተጀመረ ሲሆን ደንበኞች እንደተመለደው አገልግሎቱን በመጠቀም የሽልማት አሸናፊ እንዲሆኑ የሚያስችላቸውን የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ባንኩ ይጋብዛል።

ሁለተኛው የአገልግሎት አይነት የታክሲና ባጃጅ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች የቁጠባ ሂሳብ በመክፈት የየዕለት ቁጠባ ልምዳቸውን እንዲያዳብሩና ነገ ያሰቡበት ራዕይ ላይ እንዲደርሱ የተመቻቸ “የታክሲና ባጃጅ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች ቁጠባ አገልግሎት” ነው። ለአራት ተከታታይ ዙሮች በተካሄደው በዚህ አገልግሎት ባንካችን በሃገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የየዕለት ገቢ ያላቸውን የታክሲና የባጃጅ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች የቁጠባ ባህል ለማሳደግ ነገን ከወዲሁ እንዲሰሩት የሚያስችል እድል ከፍቷል።

ይህንን አገልግሎት የሚጠቀሙ ደንበኞችን ለማበረታታትም ባንኩ የዕጣ ኩፖኖችን በማዘጋጀት ላለፉት ሶስት ዙሮች የተለያዩ ዓይነት ሽልማቶችን አዘጋጅቶ ለእድለኞች አስረክቧል። በዛሬው አራተኛው ዙር ማጠናቀቂያ ፕሮግራምም በተመሳሳይ እጣ ለወጣላቸው እድለኞች ሱዙኪ የቤት አውቶሞቢል፣ ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎችና ዘመናዊ የሞባይል ቀፎዎችን  ለሽልማት አዘጋጅቷል።  የዚህ አገልግሎት አምስተኛ ዙር በቅርቡ ተጀምሮ በሂደት ላይ በመሆኑ የታክሲና ባጃጅ ባለንብረቶች የቁጠባ ሂሳብ በመክፈት የቁጠባውም ፣ የማበረታቻ ዕጣውም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ባንካችን ይጋብዛል።

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ዛሬ እዚህ ዋና መስሪያ ቤቱ ድረስ የተገኛችሁና የሁለቱም አገልግሎቶች ተጠቃሚ በመሆን የሽልማቶቹ እድለኛ የሆናችሁትን ደንበኞቹን በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ይወዳል።

ወደፊትም ባንካችን የባለራዕዮች ባንክ ነውና ለጋራ ራዕያችን መሳካት ከባንኩ ጋር ያላችሁን ደንበኝነት በማጠናከር የአገልግሎቶቹ ተጠቃሚ አንድትሆኑ፣ ከወዳጅ ዘመዶቻችሁ ጋር በጋራ በመሆን በቡና ባንክ ቤተሰብነታችሁም እንድትቀጥሉ  ጥሪዬን አቀርባለሁ።

ሁላችሁም እንኳን ደስ አላችሁ !!!

አመሰግናለሁ

Tags:

    Bunna Bank