
ከዚህ ቀደም በሁለት ዙር በርካቶችን አሸናፊ ያደረገው የትምህርትና ጤና ባለሙያዎች የተሳተፉበት የቡና ባንክ የመምህራንና የጤና ባለሙያዎች ይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃ ግብር ሶስተኛ ዙር የካቲት 20 ቀን 2015 ዓ.ም ተጀምሯል።
ለሶስት ወራት በሚቆየውና በትምህርትና በጤና ዘርፍ ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎች በተዘጋጀው በዚህ የቁጠባና ሽልማት መርሀ-ግብር ተሳታፊ ለሚሆኑ ደንበኞች ባንኩ ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢልን ጨምሮ በርካታ ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶችን በሽልማት መልክ አዘጋጅቷል፡፡
በቁጠባ ህይወትን መለወጥ እና በሽልማት ፍላጎትን መሙላትን በተግባር ያሳየው ቡና ባንክ ቀደም ሲል በተካሄዱትና በርካቶች በተሳተፉባቸው የቁጠባ መርሀ-ግብሮች ሁለት ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢሎችን፣ 24 ላፕቶፖችን፣ 24 ታብሌቶችን፣ 48 የሞባይል ቀፎዎችን፣ እንዲሁም ለ16 ዕድለኞች የታሪካዊ ቦታ ጉብኝት ዕጣዎችን ለአሸናፊዎች በሽልማት አበርክቷል፡፡
ቡና ባንክ የሁለተኛው ዙር የመምህራን እና የጤና ባለሞያዎች ይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃግብር አንደኛ ዕጣ አሸናፊ የሆኑትን መምህርት አስናቀች አበበ የ 2021 ሞዴል ሱዙኪ ዲዛየር መኪና ተሸላሚ ከማድረጉ በተጨማሪ ለሌሎች 94 ደንበኞቹም የተለያዩ ሽልማቶችን በማበርከት መጠናቀቁ የሚታወስ ነው፡፡

በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ መምህራንና የትምህርት አስተዳደር ሰራተኞችን ጨምሮ በጤና የሙያ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሞያዎችን በሚያሳትፈው በዚህ ሶስተኛ ዙር የቡና ባንክ ይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃግብርም ሱዙኪ ዲዛየር የቤት አውቶሞቢልን ጨምሮ በርካታ ላፕቶፖች፣ ታብሌቶች እና ሞባይል ስልኮች ለአሸናፊዎች በሽልማት መልክ ተዘጋጅተዋል፡፡
በዚህ መርሃግብር ተሳታፊ የሚሆኑ መምህራን እና የጤና ባለሞያዎች 400 ብር ሲቆጥቡ ለሽልማት እጩ የሚደርጋቸው አንድ የዕጣ ቁጥር በሞባይል ስልካቸው የሚደርሳቸው ሲሆን ቁጠባቸው በሰፋ ቁጥር ሽልማቱን የማሸነፍ እድላቸውን ከፍ ያደርጋሉ።
እስከ ግንቦት 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ለሶስት ወራት የሚቆየው የይቆጥቡ ይሸለሙ መርሀ-ግብር ሲጠናቀቅ በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ድርጅት አማካኝነት አሸናፊዎችን የመለየት ስራ የሚሰራ ሲሆን በዚህም መሰረት የተዘጋጁት ሽልማቶች ለቁጠባ መርሀ-ግብሩ አሸናፊዎች ይበረከታሉ፡፡
ቡና ባንክ የሀገርና የትውልድ ባለውለታ የሆኑትን መምህራንና የጤና ባለሙያዎችን ለማክበርና ለማበረታታት ባዘጋጀው በዚህ የቁጠባና ሽልማት መርሀ-ግብር ተሳታፊ የሚሆኑ ነባርም ሆነ አዲስ ደንበኞች በአቅራቢያቸው በሚገኝ የቡና ባንክ ቅርንጫፍ በአካል በመገኘት ቁጠባ በመጀመር የሽልማት መርሃ-ግብሩ ተሳታፊ መሆን የሚችሉ መሆኑን እያሳወቀ በመርሀ-ግብሩ ላይ ለሚኖራቸው ማንኛውም ጥያቄም ከቅርንጫፎች መረጃ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን ይገልጻል፡፡ ለመርሀ-ግብሩ ተሳታፊዎችም መልካም ዕድል ይመኛል፡፡
ቡና ባንክ አ.ማ. ከ13 ዓመታት በፊት የተቋቋመና ከ455 በላይ በደረሱ ቅርንጫፎቹ በመላዉ ኢትዮጵያ በሚገኙ ሁሉም ክልሎች አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ባንክ ሲሆን በውጭ አገርና በአገር ውስጥ የሚገኙ በርካታ ደንበኞችን በማገልገል ይገኛል፡፡