Bunna Bank

የቡና ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 14ኛ መደበኛ ጉባዔ ጥሪ

በኢትዮጵያ ንግድ አንቀፅ 366፡367፡370፡371፡372 እና 394 እንዲሁም በባንክ መመስረቻ ፅሁፍ አንቀፅ 21 መሰረት የቡና አ.ማ የባለአክሲዮኖች 14ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ሕዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል። ስለሆነም የባንኩ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም በሕጋዊ ተወካዮቻችሁ አማካኝነት በተጠቀሰው ቀን፡ ሰዓትና ቦታ በጉባዔው ላይ እንድትገኙ ባንኩ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል።

የ14ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች፤

  1. ረቂቅ አጀንዳዎችን ማፅደቅ፤
  2. በባንኩ ውስጥ የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን እና የአዲስ አክሲዮኖችን ሽያጭ ማፅደቅ፤
  3. እ.ኤ.አ የ2022/23 የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥና ተወያይቶ ማፅደቅ፤
  4. እ.ኤ.ኢ የ2022/23 የውጭ ኦዲተሮችን ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርት ማዳመጥና ተወያይቶ ማፅደቅ፤
  5. በዘመኑ የተጣራ ትርፍ አደላደል እና አከፋፈል ላይ የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ተወያይቶ ማፅደቅ፤
  6. ባንኩን ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የሚያገለግሉ የውጭ ኦዲተሮችን ሹመት ማፅደቅና አባላቸውን መወሰን፤
  7. እ.ኤ.አ የ2023/24 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ አበልና እ.ኤ.አ የ2022/23 በጀት
    ዓመት ዓመታዊ ክፍያ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
  8. የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ አባላትን መምረጥ እና አባላቸውን መወሰን፤
  9. የጉባዔውን ቃለ-ጉባዔ ማፅደቅ፤ የሚሉት ናቸው፡፡
    ማሳሰቢያ
  10. በጉባኤው ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው አካል በስብሰባው
    ላይ ለመገኘትና ድምፅ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ሰነድ ወይም ከስብሰባው ሦስት ቀን ቀደም ብሎ ቦሌ
    መንገድ ከወሎ ሰፈር አደባባይ ቀጥሎ ሩዋንዳ መታጠፊያ ከመድረሱ በፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት
    4ኛ ፎቅ የባንኩ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ የውክልና ቅፅ በመሙላት፤ የውክልና ቅፁን ዋናውንና
    አንድ ቅጂ እና የራሳቸውንም ሆነ የወካዮቻቸውን ኢትዮጵያዊ ዜግነት ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ አገር
    ዜግነት የሚያሳይ ሕጋዊ የታደሰ መታወቂያ /ፓስፖርት/ መንጃፈቃድ ዋናውን እና ቅጂውን ይዘው በመምጣት
    በጉባዔው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
  11. በተጨማሪም የድርጅትና የማህበር ተወካዮች ድርጅቱን/ማህበሩን ወክለው በስብሰባው እንዲገኙና ድምፅ
    እንዲሰጡ የሚያረጋግጥ የተመዘገበ ቃለ ጉባዔ ወይም ስልጣን ባለው አካል የተሰጠ ውክልና ዋናውንና
    ቅጂውን ይዘው መቅረብ ያለባቸው መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  12. ለተጨማሪ መረጃ ቦሌ መንገድ ከወሎ ሰፈር አደባባይ ቀጥሎ ሩዋንዳ መታጠፊያ ከመድረሱ በፊት በሚገኘው
    የባንኩ ዋና መ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0111580880/262822/262810
    በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የዳይሬክተሮች ቦርድ
ቡና ባንክ አ.ማ
የባለራዕዮች ባንክ

[ivory-search id="5747" title="Custom Search Form"]

This will close in 0 seconds

error: