Bunna Bank

የኢ.አር.ፒ እና አቦል ዲጂታል ባንኪንግ ውጤታማ ትግበራን ተከትሎ ዕውቅናና ሽልማት ተሰጠ

  • በፕሮጀክቶቹ ከ 5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማዳን ተችሏል!

ቡና ባንክ ኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ ፕሮጀክትና አቦል ዲጂታል ባንኪንግ መተግበሪያን ሙሉ በሙሉ ወደስራ ማስገባቱን ተከትሎ እነዚህ ሁለት ፕሮጀክቶች በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቁ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የባንኩ ሰራተኞች ዕውቅናና ሽልማት ሰጠ፡፡

ሐምሌ 29 ቀን 2016 ዓ.ም. የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ እና የኤክስኪዩቲቭ ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት በተካሄደው የሽልማት ፕሮግራም ለ70 ባለሙያዎች ምስጋናና ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡

የቡና ባንክ አቦል ዲጂታል ባንኪንግ መተግበሪያ በባንኩ ቺፍ ኢንፎርሜሽን ዘርፍ በተቋቋመው ቡድን በባንኩ ባለሙያዎች የራስ አቅም እንደአዲስ የተዘጋጀ መተግበሪያ ሲሆን አሁን ላይ በስኬታማነት አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተነግሯል፡፡ መተግበሪያው በራስ አቅም መልማቱ የባንኩ ሰራተኞች ልምድ እንዲያካብቱ ከማድረጉም በላይ ባንኩ 1.2 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ከወጪ እንዲያድን ማድረጉ ተነግሯል፡፡

ይህንን መተግበሪያም ሆነ የኢአርፒ ስርዓትን ወደትግበራ ለማስገባት በነበረው ጥረት የባንኩ ኤክስኪዩቲቭ ማኔጅመንት የቅርብ ክትትልና ዕገዛ በማድረግ እንዲሁም ተገቢውን አቅጣጫ በወቅቱ በመስጠት የማይተካ ሚና ተጫውቷል ተብሏል። አሁን የተተገበረው የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ ሲይስተም በዉጭ ምንዛሬ ሊያሶጣ የሚችለዉን ከ 4 ሚሊዮን ዶላር  በላይ ገንዘብ ማዳን ተችሏል።

ይህ የዕውቅናና ምስጋና ፕሮግራም መዘጋጀቱ ለፕሮጀክቱ ስኬታማነት አስተዋጽኦ ያበረከቱትን ከማመስገን ባለፈ ሌሎች የባንኩ ሰራተኞችና ባለሙያዎችን ለበለጠ ስራ ለማነሳሳትና ለማትጋት የሚረዳ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በተያያዘም ባንኩ ኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግን በተቋም ደረጃ በውጤታማት የተተገበረ ሲሆን ይህንን ፕሮጀክት ስኬታማ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱና ክትትል ሲያደርጉ ለነበሩ የሚመለከታቸው የባንኩ የስራ ክፍሎችና ባለሙያዎች ዕውቅና ተሰጥቷል፡፡

በዕለቱ የዕውቅና ፕሮግራም ላይ የተገኙት የባንንኩ ዋና ሰራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ ባስተላለፉት መልዕክት የሁለቱ ፕሮጀክቶች በዚህ መልክ መጠናቀቅ ለወደፊቱ መሰል የባንካችን የሥራ ከፍሎችና ባለሙያዎች አርዓያ ከመሆኑ በተጨማሪ  ውጤታማ ፕሮጀክቶችን ዕውን ለማድረግ የሚያነሳሳ ምሳሌ የሆነ ስራ በመሆኑ ሊበረታታ የሚገባው ተግባር ነው ብልዋል። በፕሮጀክቶቹ ትግበራ ላይ ከተካፈሉ ባለሙያዎችም ምስጋና አቅርበዋል። ፡

ዋና ስራ አስፈጻሚው የሲስተሞቹን ውጤታማ ዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚመለከታቸው የባንኩ የሥራ ክፍሎች ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተገቢውን ክትትል ማድረግ እንደሚገባቸውም አጽንኦት ሰጥተው አሳስበዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

[ivory-search id="5747" title="Custom Search Form"]

This will close in 0 seconds

error: