New to site?


Login

Lost password? (X)

Already have an account?


Signup

(X)
Farooq

News

ቡና ባንክ ለኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ (ኮቪድ-19) ለመከላከል የሁለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ ለደንበኞቹም የተለያዩ የአገልግሎት ማሻሻያዎችን አቅርቧል

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ በዓለም አቀፍ ብሎም በአገራችን ደረጃ ከፍተኛ ስጋትን ያንዣበበውን የኮሮና ቫይረስ (ኮቢድ19) ወረርሽኝ ለመከላከል ለብሄራዊ የሃብት አሰባሳቢ ኮሚቴ የሁለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡

ቡና ባንክ በትናንትናው ዕለት በሰላም ሚኒስቴር አዳራሽ ብሄራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው ሰብሳቢ አምባሳደር ምስጋናው አረጋ ያስረከበ ሲሆን ፤ከአስከፊ በሽታው መስፋፋት ጋር በተያያዘ በአገራችን የሚያርሰውን ጉዳት ለመከላከል በሚደረገው ጥረት አጋርነቱን ለማሳዬትና የመንግስትን ጥሪ ተከትሎ ምልሽ ለመስጠት የተደረገ ድጋፍ መሆኑን ተገልጾአል፡፡

አምባሳደር ምስጋናው አረጋ የእርዳታ ድጋፉን ከተቀበሉ በኋላ ባደረጉት ንግግር የኮቪድ 19 በሽታ በአገራችን የሚያደርሰውን ጉዳት ለመከላከል ባንኮችን ጨምሮ የተለያዩ የማህበሰብ ክፍሎች የተጠናከረ ድጋፍ ማድረጋቸው የሚያስመሰግናቸው መሆኑን በመግለጽ በዚህ መልኩ ትብብሩ የሚጠናከር ከሆነ በአጭር ጊዜ ውስጥ የጉዳት መጠኑን በመቀነስ መከላከል ይቻላል ብለዋል፡፡

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ በተጨማሪም ለደንበኞቹ ኮሮና ቫይረስ (ኮቢድ19) ወረርሽኝ እያስከተላቸው የሚገኙ ተጽዕኖዎችን ለመቋቋም የሚያስችሉ የተለያዩ የአገልግሎት ማሻሻያዎችንና የጥንቃቄ ርምጃዎችን በመውሰድ ላይ እንደሚገኝ በቅርቡ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ቡና ባንክ ከአስከፊ በሽታው መስፋፋት ጋር በተያያዘ በዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ የተፈጠረውን ቀውስ ግምት ውስጥ በማስገባት ባንኩ ማሻሻያ ካደረገባቸው የባንኩ አገልግሎቶች መካከል የባንኩ ተበዳሪዎች የብድር ማራዘሚያ ክፍያ ኮሚሽን ይገኝበታል፡፡

በዚሁ መሰረት የባንኩ ተበዳሪ የሆኑ ደንበኞች ከዚህ ቀደም ይጠየቁ የነበረውን የብድር ማራዘሚያ ክፍያ ኮሚሽን ( የአገልግሎት ክፍያ) ከማርች 31 ቀን 2020 ጀምሮ ለቀጣይ ሁለት ወራት ሙሉ በሙሉ በማንሳት ለደንበኞቹ አጋርነቱን ገልጾአል፡፡

ባንኩ ተበዳሪዎች በኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ሳቢያ ሊያጋጥማቸው የሚችለውን ብድር የመክፈል አቅም ውስንነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የአገልግሎት ክፍያ በማስቀረቱ ወረርሽኝ ምክንያት የሚደርሰውን የኢኮኖሚ ተጽዕኖ ለመቀነስ ለሚደረገው ጥረት የበኩሉን ሚና መጫወቱን ያመለክታል፡፡

ቡና ባንክ የአገልግሎት ፈላጊዎች መተፋፋግ ለማስቀረትና አካላዊ ርቀትን ተጠብቆ አገልግሎት እንዲሰጥ ከማድረጉ ባሻገር በሞባይል ባንክ  እስከ 30 ሺ ብር ድረስ፤በኢንተርኔት እንደ ደንበኞች ጥያቄና ፍላጎትን መሰረት ባደረግ መልኩ የገንዘብ መጠኑ የሚስተናገድ ሲሆን ፤ በቡና ኤቴኤም አገልግሎት በአንድ ጊዜ ሲሰጥ የነበረውን የገንዘብ መጠን እስከ አስር ሺ ብር ድረስ በማሳደግ እንዲያስተላልፉና እንዲገበያዬ ምቹ በማድረግ ደንበኞቹ ወደ ቅርንጫፎች መምጣት ሳያስፈልጋቸው በሞባይል፤በኤቴኤምና በፖስ የመክፈያ ማሽን እንዲጠቀሙ ማመቻቸቱን ይታወቃል፡፡

ለኮረና ቫይረስ የመከላከል ዘመቻ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ለሚፈልግ ብሄራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚያካሂደው በሽታውን የመከላለል ዘመቻው ገንዘብ ለማሰባሰብ በቡና ኢንተርናሽናል ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1019601001853 የከፈተ በመሆኑ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በአገር አቀፍ ደረጃ በሽታውን ለመከላከል ለሚካሄደው ዘመቻ የበኩሉን ድጋፍ በማድረግ አጋርነቱን ማሳዬት ይችላል፡፡

/ News

wash your hands!

/ News

ቡና ባንክ ከኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ (ከኮቪድ-19 )ጋር በተያያዘ የአገልግሎት ማሻሻያዎችን አደረገ

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ለደንበኞቹ ኮሮና ቫይረስ(ኮቢድ19) ወረርሽኝ እያስከተላቸው የሚገኙ ተጽዕኖዎችን ለመቋቋም የሚያስችሉ የተለያዩ የአገልግሎት ማሻሻያዎችንና የጥንቃቄ ርምጃዎችን በመውሰድ ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡

ቡና ባንክ ከአስከፊ በሽታው መስፋፋት ጋር በተያያዘ በዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ የተፈጠረውን ቀውስ ግምት ውስጥ በማስገባት ባንኩ ማሻሻያ ካደረገባቸው የባንኩ አገልግሎቶች መካከል የባንኩ ተበዳሪዎች የብድር ማራዘሚያ ክፍያ ኮሚሽን ይገኝበታል፡፡

በዚሁ መሰረት የባንኩ ተበዳሪ የሆኑ ደንበኞች ከዚህ ቀደም ይጠየቁ የነበረውን የብድር ማራዘሚያ ክፍያ ኮሚሽን ( የአገልግሎት ክፍያ) ከማርች 31 ቀን 2020 ጀምሮ ለቀጣይ ሁለት ወራት ሙሉ በሙሉ በማንሳት ለደንበኞቹ አጋርነቱን ገልጾአል፡፡

ባንኩ ተበዳሪዎች በኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ሳቢያ ሊያጋጥማቸው የሚችለውን ብድር የመክፈል አቅም ውስንነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የአገልግሎት ክፍያ በማሰቀረቱ ወረርሽኝ ምክንያት የሚደርሰውን የኢኮኖሚ ተጽዕኖ ለመቀነስ ለሚደረገው ጥረት የበኩሉን ሚና መጫወቱን ያመለክታል፡፡

ቡና ባንክ የአገልግሎት ፈላጊዎች መተፋፋግ ለማስቀረትና አካላዊ ርቀትን ተጠብቆ አገልግሎት እንዲሰጥ ከማድረጉ ባሻገር በሞባይል ባንክ ፤በኢንተርኔት እና በቡና ኤቴኤም አገልግሎት በአንድ ጊዜ ሲሰጥ የነበረውን የገንዘብ መጠን እስከ አስር ሺ ብር ድረስ በማሳደግ እንዲያስተላልፉና እንዲገበያዬ ምቹ በማድረግ ደንበኞቹ ወደ ቅርንጫፎች መምጣት ሳያስፈልጋቸው በሞባይል፤በኤቴኤምና በፖስ የመክፈያ ማሽን እንዲጠቀሙ ማመቻቸቱን አስታውቋል፡፡

ባንኩ በተጨማሪም ቫይረሱን ስርጭቱን ለመግታት የሚያስችሉ ከደንበኞች አገልግሎት ጋር የተያያዙ ሰራተኞች የአፍ መሸፈኛ(ማስክ)፤የእጅ ጓንት እና ሳኒታይዘሮችን በማሰራጨት ርቀታቸውን ጠብቀው በጥንቃቄ አገልግሎቱን እንዲሰጡ እየተደረገ መሆኑን አስረድቷል፡፡

በሌላ በኩል ባንኩ ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችሉ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ ሲሆን፤ነፍሰ ጡሮችንና እድሜያቸው ከ55 ዓመት በላይ የሆኑ እንዲሁም የታወቀ የጤና ችግር ያለባቸው ሰራተኞች ሆኖ ከአፕሪል 1 ጀምሮ ለ14 ቀናት በቤታቸው እንዲቆዩ ወስኗል፡፡

/ News

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ከታክስ በፊት 625 ሚሊዮን ብር አተረፈ

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ በተጠናቀቀው የ2011 የበጀት ዓመት ከታክስ በፊት 625 ሚሊዮን ብር ማትረፉን የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢና ዋና ስራ አስፈጻሚ አስታወቁ፡፡

የቦርድ ሰብሳቢው ዶ/ር ሰውአለ አባተ እና ዋና ስራአስፈጻሚው አቶ ሙሉጌታ ዓለማየሁ ህዳር 28 ቀን 2012 ዓ.ም. በሚሊኒየም አዳራሽ ለባለአክሲዮኖች አስረኛ ጠቅላላ ጉባኤ ባቀረቡት ሪፖርት እንዳስታወቁት፤ባንኩ ያገኘው የትርፍ መጠን ከካቻምናው በ198 ሚሊዮን ብር ወይም በ46.4 በመቶ ጭማሬ አስመዝግቧል፡፡

የባንኩ ውጤታማነት የተመዘገበው ባንኩ ሊቀነሱ የሚችሉ ወጪዎችን በጥንቃቄ በማስተዳደርና ያለውን ውስን ሃብት በአግባቡ ጥቅም ላይ በማዋል በተደረገው ጥረት መሆኑን የባንኩ ከፍተኛ ሃላፊዎች አስታውቀዋል፡፡

በዚሁ መሰረት ባንኩ በበርካታ መስፈርቶች ከፍተኛ እድገት እንዳስመዘገበ ገልጸው፤የባንኩን ቀጣይ እድገት የሚያስቀጥሉና ተደራሽነቱን የሚያሰፉ 34 አዳዲስ ቅርንጫፎችን በመክፈት እንዲሁም አዳዲስ አገልግሎቶችን የሞባይል፤የኢንተርኔት፤የወኪል እንዲሁም ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎትን በማስፋፋትና በማጠናከር በኩል ሰፊ ስራዎችን እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡

በሌላ በኩል ባንኩ ቋሚ ሃብትን ለማፍራት ባደረገው ጥረትም በአዲስ አበባ እና በባህርዳር ከተሞች የራሱን ህንጻ በግዥ ባለቤት መሆን እንደቻለ የገለጹት የባንኩ ከፍተኛ ሃላፊዎች፤ የባንኩን የተከፈለ ካፒታሉን ወደ ብር 1.8 ቢሊየን ብር፤አጠቃላይ ሃብቱንም ወደ 14 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ እንደተቻለ አብራርተዋል፡፡

ባንኩ በአስር ዓመት ውስጥ ካስመዘገበው ውጤት የላቀ ውጤት በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ለማስመዝገብ የሚያስችል የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ መነደፉን የገለጹ ሲሆን፤በተያዘው የበጀት ዓመት ወደ ትግበራ በመገባቱ በቀጣይ ዓመታት ዘርፍ ብዙ እመርታዎች እንደሚጠበቁ ከባንኩ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡ 

/ News
Loading...

Bunna Bank