New to site?


Login

Lost password? (X)

Already have an account?


Signup

(X)
Farooq

News

ፋና ዜና

ቡና ባንክ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ዕጣ የወጣላቸውን ደንበኞቹን ሸለመ https://www.facebook.com/fanabroadcasting/posts/4066702100087165

/ News

የቡና ባንክ ቺፍ ስትራቴጂ ኦፊሰር አቶ መንክር ሃይሉ በስምንተኛው ዙር “የውጭ ምንዛሬ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ ይሸለሙ” ፕሮግራም እና የአምስተኛው ዙር የታክሲና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪ ሹፌሮችና ባለንብረቶች “ይቆጥቡ ይሸለሙ” መርሃ ግብር ላይ ያደረጉት ንግግር

(ግንቦት 18 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ) ክቡራን የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ደንበኞችና እድለኞችቡና ኢንተርናሽናል ባንክ የስምንተኛውን ዙር “የውጭ ምንዛሬ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ ይሸለሙ” ፕሮግራም እና የአምስተኛውን ዙር የታክሲና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪ ሹፌሮችና ባለንብረቶች “ይቆጥቡ ይሸለሙ” መርሃ ግብር ፕሮግራሞች መጠናቀቃቸውን አስመልክቶ በዕጣ የወጣላችሁን ሽልማት ለመረከብ በመብቃታችሁ ሁላችሁንም እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ።

በባንክ አገልግሎት ዘርፍ 11 ዓመታት ያስቆጠረው ቡና ባንክ የሃገራችንን የቁጠባ ባህል ለማሳደግ እና ዘመናዊ የባንክ አገልግሎቶችን ለመስጠት በአዲስ አበባና በሁሉም የሃገራችን አካባቢዎች 284 ቅርንጫፎችን ከፍቶ አገልግሎቱን ተደራሽ በማድረግ ላይ ይገኛል።ቡና ባንክ የማበረታቻ ሽልማቶችን በማዘጋጀት ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ ባደረገው የታክሲና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪ ሹፌሮችና ባለንብረቶች የቁጠባ መርሃ ግብር እስካሁን ድረስ 49 ሺህ 37 የታክሲና ሜትር ታክሲ አሽከርካሪና ባለንብረቶች እንዲሁም 31 ሺህ 498 የባለሶስት እግር አሽከርካሪና ባለንብረቶች በድምሩ 80 ሺህ 535 አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች በየቀኑ የሚያገኙትን ገቢ በመቆጠብ የቁጠባ ባህላቸውን እንዲያዳብሩና ለተሻለ ህይወት እንዲጥሩ መሰረት ሆኗቸዋል።

ከነዚህ መካከልም የአሁኑን ጨምሮ በአምስት ዙሮች የይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃ ግብሩ ላይ ተካፋይ ሆነው ዕጣ ለወጣላቸው ዕድለኞች ዘመናዊ አውቶሞቢሎችንና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ በርካታ ሽልማቶችን በመስጠት ህይወታቸው እንዲሻሻል የበኩሉን አስተዋዕዖ አበርክቷል።

በሌላ በኩል የቡና ባንክ ደንበኞች ከውጭ የሚላክላቸውን የውጭ ምንዛሪ በባንኩ በኩል ሲቀበሉ የውጭ ምንዛሪ መቀበልም ሆነ መመንዘር ህጋዊ የባንክ ስርዓትን እንዲከተል በማድረግ የጥቁር ገበያን ተጽዕኖ ለመቀነስ ላበረከቱት አስተዋዕዖ “ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ.፣ ይሸለሙ” በሚል መሪ ቃል የማበረታቻ ሽልማቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ አሰራር ዘርግቶ ተግባራዊ ሲያደርግ ቆይቷል።በዚህም በስምንት ዙሮች በርካታ እድለኞች የዘመናዊ አውቶሞቢሎችና የግል እና የቤት ውስጥ መገልገያ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ተሸላሚ ለመሆን በቅተዋል።

ዛሬም እንደቀደሙት ጊዜያት ሁሉ ባንካችን ከላይ በጠቀስኳቸው ሁለቱ ፕሮግራሞች ተሳትፈው ዕድለኞች ለሆኑና እጣ ለወጣላቸው ደንበኞች ያዘጋጃቸውን የ2020 ሱዙኪ የቤት አውቶሞቢሎች፣ የባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች፣ የዘመናዊ ሶፋ፣ የፍላት ስክሪን ቴሌቪዠኖች፣ የውሃ ማጣሪያዎች፣ እና ዘመናዊ የስልክ ቀፎ ሽልማቶችን ያስረክባል።

ላለፉት 5 ዙሮች ለታክሲዎችና ባለሶስት እግር አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች ሲካሄድ የቆየው የቁጠባ ፕሮግራም በቀጣይ የመካከለኛና ከፍተኛ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ባለንብረቶችንና ሹፌሮችን አካትቶ በአዲስ መልክ ከአጓጊ ሽልማቶች ጋር የሚቀጥል ይሆናል። ዘጠነኛው ዙር የውጭ ምንዛሪ ይቀበሉ ይመንዝሩ ይሸለሙ ፕሮግራምም ተጀምሮ ተግባራዊ በመሆን ላይ ይገኛል።

ቡና ባንክ ዛሬ እዚህ ዋና መስሪያ ቤቱ ድረስ የተገኛችሁና የሁለቱም አገልግሎቶች ተጠቃሚ በመሆን የሽልማቶቹ እድለኛ የሆናችሁትን ደንበኞቹን በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ይወዳል።ወደፊትም ባንካችን የባለራዕዮች ባንክ ነውና ለጋራ ራዕያችን መሳካት ከባንኩ ጋር ያላችሁን ደንበኝነት በማጠናከር የአገልግሎቶቹ ተጠቃሚ አንድትሆኑ፣ ከወዳጅ ዘመዶቻችሁ ጋር በጋራ በመሆን በቡና ባንክ ቤተሰብነታችሁም እንድትቀጥሉ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

ሁላችሁም እንኳን ደስ አላችሁ !!!

አመሰግናለሁ

/ News

ቡና ባንክ ደንበኞቹን ሸለመ

ከ80 ሺህ በላይ የታክሲና ባጃጅ አሽከርካሪና ባለንብረቶችን ደንበኛ ማድረግ ችሏ

 (ግንቦት 18 ቀን 2013 . አዲስ አበባ

ቡና  ባንክ ላለፉት ወራት ሲያካሂድ የቆየውን የስምንተኛውን ዙር “የውጭ ምንዛሬ ይቀበሉ ፣ይመንዝሩ ይሸለሙ” እና የአምስተኛውን ዙር “የታክሲና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪ ሹፌሮችና ባለንብረቶች ቁጠባ” መርሃ ግብሮች ማጠናቀቂያ ምክንያት በማድረግ ዕጣ ለወጣላቸው ደንበኞቹ ያዘጋጃቸውን ሽልማቶች በዛሬው ዕለት አስረክቧል።

ባንኩ ግንቦት 18 ቀን 2013 ዓ.ም በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ባካሄደው በዚሁ የሽልማት አሰጣጥ ስነስርዓት ላይ በሁለቱም ፕሮግራሞች የዕጣ አሸናፊዎች ለሆኑት ባለዕድሎች የአውቶሞቢሎች፣ የባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ፣ የዘመናዊ ሶፋዎች፣ የስማርት ስልኮች ፣ የፍላት ስክሪን ቴሌቪዠኖች እና የውሃ ማጣሪያዎች በሽልማት አበርክቷል።

ደንበኞች ከውጭ የሚላክላቸውን የውጭ ምንዛሪ በቡና ባንክ ቅርንጫፎች በኩል ሲቀበሉና ሲመነዝሩ የሽልማት ተጠቃሚ የሚሆኑባቸውን የዕጣ ኩፖኖች የሚቀበሉበት አሰራር የዘረጋው ቡና ባንክ ባለፉት ወራት ባካሄዳቸው ስምንት ዙሮች የዕጣ ኩፖኖችን በማዘጋጀት በባንኩ በኩል የውጭ ምንዛሪ የሚቀበሉና የሚመነዝሩ ደንበኞቹን ሲሸልም ቆይቷል።

የዛሬው ሽልማት የ8ኛው ዙር የይቀበሉ ፣ ይመንዝሩ ፣ ይሸለሙ መርሃ ግብር ማጠናቀቂያ ሲሆን  የዕጣ ባለእድል ለሆኑት ደንበኞቹም  ለአንደኛ ዕጣ ዘመናዊ የ2020 ሱዙኪ ዲዛየር የቤት አውቶሞቢል ፣ለሁለተኛ ዕጣ አምስት የውሃ ማጣሪያዎች ሶስተኛ ዕጣ አምስት ፍላት ስክሪን ቴሌቪዠኖች እና አራተኛ ዕጣ አስር ስማርት ሞባይል ቀፎዎችን ለባለዕድሎች አዘጋጅቶ አስረክቧል።

የባንኩ ቺፍ ስትራተጂ ኦፊሰር አቶ መንክር ሃይሉ ለባለዕድሎች ሽልማት በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት “የውጭ ምንዛሪ ይቀበሉ ይሸለሙ መርሃ ግብር በህጋዊ መንገድ የሚካሄድ የውጭ ምንዛሪ ለውጥን በማበረታታት ሃገሪቱ ልታገኝ የምትችለውን ጥቅም በማረጋገጥ ረገድ አይነተኛ ድርሻ እንዳለው ቡና ባንክ ያምናል” ብልዋል።

በተመሳሳይም ቡና ባንክ የታክሲና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ባለንብረቶችና ሹፌሮች የቁጠባ ሂሳብ በመክፈት የየዕለት ቁጠባ ልምዳቸውን እንዲያዳብሩና ነገ ያሰቡበት ራዕይ ላይ እንዲደርሱ የተመቻቸ የቁጠባ አገልግሎት በማዘጋጀት ብዙዎችን ተጠቃሚ አድርጓል።

ባንኩ በቋሚነት በሚሰጠው በዚህ አገልግሎት በሃገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የዕለት ገቢ ያላቸውን የታክሲና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ባለንብረቶችና ሹፌሮች  የቁጠባ ባህል ለማሳደግ ለአምስት  ተከታታይ ዙሮች ተጠቃሚዎችን በስፋት ለማካተት የሚያስችሉ ተግባራት አከናውኗል።

እንደአቶ መንክር ሃይሉ ገለጻ ይህ የቁጠባ መርሃ ግብር ባንኩ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበበት አገልግሎት ነው። “ይህ የታክሲና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ሹፌሮችና ባለንብረቶች የቁጠባ መርሃ ግብር  ቡና ባንክ የማበረታቻ ሽልማቶችን በማዘጋጀት ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ ያደረገው የቁጠባ አገልግሎት ነው። እስካሁን በተካሄዱት አምስት ዙሮች 49 ሺህ 37 የታክሲና ሜትር ታክሲ አሽከርካሪና ባለንብረቶች እንዲሁም 31 ሺህ 498 የባለሶስት እግር አሽከርካሪና ባለንብረቶች በድምሩ  80 ሺህ 535 አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች በየቀኑ የሚያገኙትን ገቢ በመቆጠብ የቁጠባ ባህላቸውን እንዲያዳብሩና ለተሻለ ህይወት እንዲጥሩ ባንኩ መሰረት ጥሎላቸዋል። ከነዚህ መካከልም የአሁኑን ጨምሮ በአምስት ዙሮች የይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃ ግብሩ ላይ ተካፋይ ሆነው ዕጣ ለወጣላቸው ዕድለኞች   ዘመናዊ አውቶሞቢሎችንና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ ቴሌቪዠኖችን፣ ስማርት ስልኮችንና በርካታ ሽልማቶችን በመስጠት ቁጠባን ባህላቸው እንዲያደርጉ የበኩሉን አስተዋዕዖ አበርክቷል” ብለዋል።

የ9ኛው ዙር የውጭ ምንዛሪ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ መርሃ ግብር በቅርቡ ተጀምሮ በሂደት ላይ ሲሆን 6ኛው ዙር የታክሲና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ሹፌሮችና  ባለንብረቶች የቁጠባ መርሃ ግብር ደግሞ መካከለኛና ከፍተኛ የትራንስፖርት ተሽከርካሪ ባለቤቶችና አሽከርካሪዎችን አካትቶ በቅርቡ እንደሚጀመርም ቺፍ ስትራተጂ ኦፊሰሩ አቶ መንክር ሃይሉ አስታውቀዋል።

“ደንበኞች የአገልግሎቱም የማበረታቻ ሽልማቱም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ቡና ባንክ  በዚህ አጋጣሚ ይጋብዛል” ነው ያሉት አቶ መንክር።

ከተመሰረተ 11 ዓመታት ያስቆጠረው ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ በአዲስ አበባና በመላው ኢትዮጵያ በከፈታቸው 284 ቅርንጫፎቹ ለህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ የግል ባንክ ነው።

/ News

284 ኛው ቅርንጫፍ ተከፈተ

ቡና ባንክ 284ኛ ቅርንጫፉን ለደንበኞቹ ክፍት አድርጓል፡፡

ባንኩ ፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ “ፈረንሳይ ለጋሲዮን” ቅርንጫፉን ከፍቶ ለደንበኞቹ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

/ News

ባንኩ የቅርንጫፍ ቁጥሮቹን ወደ 283 ከፍ አደረገ

ቡና ባንክ የቅርንጫፍ ቁጥሮቹን በመላው ኢትዮጵያ በማስፋት ይበልጥ ወደደንበኞቹ እየቀረበ ነው፡፡ በቅርቡ 282ኛ ቅርንጫፉን በይርጋጨፌ ከተማ ለደንበኞቹ ክፍት ያደረገ ሲሆን በትላንትናው እለት በመዲናችን አዲስ አበባ ቦሌ አራብሳ 283ኛ ቅርንጫፉን ከፍቷል፡፡

/ News

Bunna Bank