New to site?


Login

Lost password? (X)

Already have an account?


Signup

(X)
Farooq

News

ድሬ ቲዩብ ዜና

ቡና ባንክ የ 5ኛ ዙር “የታክሲና ባጃጅ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች ይቆጥቡ ይሸለሙ” መርሃ ግብር አሸናፊዎችን ይፋ አደረገ DireTube | Facebook

/ News

ናሁ ዜና

ጉዞ ጎ እና ቡና ባንክ ስምምነት ፊርማ ጉዞ ጎ እና ቡና ባንክ ስምምነት ፊርማ Nahoo News – YouTube

/ News

ኢዜአ ዜና

ቡና ባንክና ጉዞ ጎ ስምምነት Ethiopian News Agency | Facebook

/ News

ባንኩ የቅርንጫፍ ቁጥሮቹን ወደ 281 ከፍ አደረገ

ቡና ባንክ የአገልግሎት አድማሱን በሁሉም የሃገሪቱ ክልሎች በማስፋት ለደንበኞቹ ቀልጣፋና ምቹ አገልግሎትን ለመስጠት የያዘውን ዕቅድ ለማሳካት እየገሰገሰ ነው።

በአንድ ሳምንት ብቻ አምስት አዳዲስ ቅርንጫፎችን ከፍቶ አገልግሎት አስጀምሯል።

“ቴፒ ቅርንጫፍ” 277ኛው የቡና ባንክ ቅርንጫፍ ሆኖ በደቡብ ክልል ሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ውስጥ ተከፍቶ አገልግሎት ጀምሯል።

“መቱ ቅርንጫፍ” 278ኛው የቡና ባንክ ቅርንጫፍ ሆኖ በኦሮሚያ ክልል ኢሉአባቦራ ዞን መቱ ከተማ ውስጥ ተከፍቶ አገልግሎት ጀምሯል።

በሴቶች ብቻ የሚመራው “ኮከበጽባህ ልዩ ቅርንጫፍ” 279ኛው የቡና ባንክ ቅርንጫፍ ሆኖ በአዲስ አበባ ከተማ ተከፍቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

“ግንደወይን ቅርንጫፍ” 280ኛው የቡና ባንክ ቅርንጫፍ ሆኖ በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ግንደወይን ከተማ ተከፍቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

“ዱርቤቴ ቅርንጫፍ” 281ኛው የቡና ባንክ ቅርንጫፍ ሆኖ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ዱርቤቴ ከተማ ተከፍቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

ባንኩ በሁሉም ስፍራ ተገኝቶ ለሁሉም ተደራሽ የሚሆን አገልግሎቱን በጥራትና በፍጥነት በመስጠት ወደራዕዩ ለመድረስ የሚያደርገውን ግስጋሴ ቀጥሏል።

/ News

የጋራ ስምምነት መግባቢያ ሰነድ ተፈረመ

ቡና ባንክ እና የኢትዮጲያ ኢንደስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

ስምምነቱ ሁለቱንም ተቋማት ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ተብሏል።

በኢትዮጲያ ስካይላይት ሆቴል በተካሄደው የስምምነት ፊርማ ስነስርዓት ላይ የተገኙት የንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር የኢንደስትሪ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታና የኢግልድ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተካ ገብረየስ ድርጅቱ ለባንክ አገልግሎት ፍላጎቶቹ ቡና ባንክን መምረጡ የተሻለ ተጠቃሚ ያደርገዋል የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል።

በጋራ መስራት ለውጥ ያመጣል ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው በሁለቱም ድርጅቶች መካከል የተፈረመው ስምምነት ዘላቂ እንዲሆንና ሁለቱንም ተቋማት እኩል ተጠቃሚ እንዲያደርግ የተባበረ ጥረት ያስፈልጋል ብለዋል።

የቡና ባንክ ቺፍ ባንኪንግ ሰርቪስ ኦፊሰር አቶ ለውጤ ጥሩሰው በበኩላቸው ባንኩ ከዚህ ቀደምም ከተለያዩ ተቋማት ጋር መሰል ስምምነቶችን በመፈጸም ለሰራተኞች እና ለተቋሙ የባንክ ፍላጎቶች አፋጣኝ እና አጥጋቢ ምላሽ ሲሰጥ መቆየቱን ጠቅሰዋል።

ይህ የዛሬው ስምምነትም የዚሁ ሂደት አንድ አካል መሆኑን የገለጹት አቶ ለውጤ ሁለቱ ተቋማት ለዚህ ስምምነት እንዲበቁ በሂደቱ አስተዋጽዖ ያበረከቱትን አካላት አመስግነዋል።

በቀድሞ ስሙ ጅንአድ ተብሎ ይጠራ የነበረው የኢንደስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ የሺመቤት ነጋሽ እና የቡና ባንክ ዲፖዚት ሞቢላይዜሽን ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ጥላሁን በየበኩላቸው ባደረጉት ንግግር ይህ ስምምነት የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ እንደማይሆን ገልጸው ለተቋማቱ ዘላቂ ጥቅም በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል።

ስምምነቱ ቡና ባንክ ለኢንደስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅ ሰራተኞች ብድር እና የመሳሰሉ ፋይናንስ አገልግሎቶችን እንዲሰጥ፣ የኢንደስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅትም የፋይናንስ አገልግሎቱን በቡና ባንክ በኩል እንዲያደርግ የሚያስችል መሆኑም በፊርማ ስነስርዓቱ ወቅት ተገልጿል።

/ News

Bunna Bank