New to site?


Login

Lost password? (X)

Already have an account?


Signup

(X)
Farooq

Tender

HomeAboutTender

አክሲዮኖችን በጨረታ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ቡና ባንክ አ.ማ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በወጣው መመሪያ ቁጥር FIS/01/2016 መሰረት የውጭ አገር ዜግነት ካላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለአክሲዮኖች የተረከባቸውን በቁጥር  2,295 የሆኑ አክሲዮኖች ፤ የአንዱ አክሲዮን ዋጋ ብር 100 ሆኖ፤ ጠቅላላ ዋጋቸው ብር 229,500.00 የሚያወጡ አክሲዮኖችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም የአንድ አክሲዮን የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 100.00 ሲሆን ፤ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመሳተፍ የምትል መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 1. ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው ግለሰብ ወይም ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ባላቸው ባለአክሲዮኖች የተያዙ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፤
 2. ተጫራቶች ማንነታቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፤ የታደሰ መንጃ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ፤ ወይም ተጫራቾች ድርጅቶች ከሆኑ ድርጅቱ በሰነዶች ማ/ም/ጽ/ቤት የጸደቀ የመመስረቻ ጽሁፍ እና የመተዳደሪያ ደንብ ወይም ሌላ ተቀባይነት ያለው ማስረጃ ኮፒ ከዋናው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
 3. ተጫራቾች አንዱን አክሲዮን የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለፅ መግዛት የሚፈልጉትን ጠቅላላ የአክሲዮን ዋጋ ¼ኛ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
 4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሳይያያዝ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፤
 5. ተጫራቾች መግዛት የሚችሉት አነስተኛ የአክሲዮን ብዛት በቁጥር 500 እና የገንዘብ መጠኑ ደግሞ ብር 50,000/ሀምሳ ሺህ/ ሲሆን ፤ ከዚህ በታች የሆኑ አክሲዮኖችን ለመግዛት የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፤
 6. አክሲዮኖች የሚሸጡት በተጫራቾች የሚሰጠውን ዋጋ በማወዳደር ሲሆን ፤ የተሻለ ዋጋ የሚሰጡ ተጫራቾች ለመግዛት በገለጹት ዋጋ እና የተጠየቁትን አክሲዮኖች ብዛት ልክ በቅደም ተከተል ቅድሚያ ይሰጣል፡፡ ተጫራቾች ተወዳድረው የጨረታው አሸናፊ መሆናቸው በባንኩ ሲገለጽላቸው የተሻለ ዋጋ ለሰጡ ተወዳዳሪዎች ቅድሚያ በመሰጠቱ ምክንያት ሊገዙት ከጠየቁት የአክሲዮኖች ብዛት የቀነሰ ቢሆንም በቀጣይ የተሻለ ዋጋ የሰጠ ተወዳዳሪ የተረፉ አክሲዮኖችን ባቀረበው ዋጋ  የመግዛት ግዴታ አለባቸው፤
 7. ከአንድ በላይ ተጫራቾች ተመሳሳይ ዋጋ ቢሰጡ እና ተራፊ አክሲዮኖች ሁለቱ ተጫራቾች ከጠየቁት የአክስዮን ብዛት ቢያንሱ ቀሪዎቹ አክሲዮኖች ተመሳሳይ ዋጋ ለሰጡ ተጫራቾች እኩል ይከፋፈላል፤
 8. ተጫራቾች ሌሎች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፤
 9. የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ የጨረታው አሸናፊ መሆናቸው በተገለፀላቸው በ15 ቀን /በአስራ አምስት ቀናት/ ጊዜ ውስጥ ለባንኩ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው አሸናፊ በዚህ ጊዜ ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ለባንኩ ገቢ ካላደረጉ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፤
 10. ለጨረታ የቀረቡት አክሲዮኖች በሙሉ በአሸናፊዎች ከተገዙ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፤
 11. ከላይ የተገለጹትን የሚያሟላ ተጫራች ለጨረታው የተዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ እስከ ነሃሴ 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4 ሰዓት ድረስ በስራ ሰዓት ቦሌ ሩዋንዳ መዞሪያ በሚገኘው የባንኩ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቀርበው በመውሰድ እና በመሙላት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ አሽገው ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤
 12. ጨረታው ነሃሴ 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በእለቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም የሚመለከታቸው ታዛቢዎች በተገኙበት ቦሌ ሩዋንዳ መዞሪያ በሚገኘው የባንኩ ህንፃ 5ኛ ፎቅ ላይ ባለው አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፤
 13. የጨረታው አሸናፊዎች የጨረታው አሸናፊ መሆናቸው እንደተገለጸላቸው ዋናው /ኦርጅናሉ/ ሰነድ ለባንኩ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
 14. በሌሎች ህጎችና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መመሪያዎች የተደነገጉ ደንቦች በዚህ ጨረታ ላይ ተፈፃሚነት አላቸው፤
 15. ባንኩ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥሮች

+251 111 58-08-80 ወይም

+251 111 26-28-22 መደወል ይችላሉ

ቡና ባንክ አ.ማ.

አዲስ አበባ

ቀን 15/08/2011 ዓ.ም

 

 

 

 

 

       ቡና ባንክ .

      BUNNA BANK S.C

ለቡና ባንክ አ.ማ ባለአክስዮኖች በሙሉ

ዕጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ ለመቀበል ተሻሽሎ የወጣ ማስታወቂያ

የቡና ባንክ አ.ማ የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ታህሳስ 11 ቀን 2013 ዓ.ም ባካሄደው 11ኛ መደበኛ ስብሰባው ያቋቋመው “የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማና አስመራጭ ኮሚቴ” ከሐምሌ 01 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የዕጩ ጥቆማዎችን በመቀበል ላይ የሚገኝ ሲሆን የቦርድ አባላትን ለመጠቆም የሚያስችለውን የጥቆማ መሙያ ቅጽ ከቡና ባንክ አ.ማ ድረ-ገጽ https://www.bunnabanksc.com ወይም አዲስ አበባ ቦሌ መንገድ ሩዋንዳ መታጠፊያ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 8ኛ ፎቅ ከሚገኘው የኮሚቴው ጽ/ቤት ወይም ከባንኩ ቅርንጫፎች ማግኘት ይቻላል፡፡

ስለሆነም ባለአክስዮኖች ለዳይሬክተሮች የቦርድ አባልነት ብቁ የሆኑትን ፤ ለባንኩ ሁለንተናዊ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከት የሚችሉትን እና ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉትን ዕጩዎች በቅፁ ላይ በጥንቃቄ በመሙላት እስከ ጥቅምት 01 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ብቻ ከላይ በተገለፀው የኮሚቴው ጽ/ቤት በአካል በማቅረብ ወይም አድራሻውን ለቡና ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማና አስመራጭ ኮሚቴ በማለት በባንኩ የፓ.ሣ.ቁጥር 1743 ኮድ 1110 በአደራ ደብዳቤ በመላክ ወይም የተሞላውን ቅጽ ስካን በማድረግ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው በባንኩ ኢሜይል bibnomination@bunnabanksc.com አያይዛችሁ በመላክ ለባንኩ ዕድገት የበኩላችሁን አስተዋፅኦ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ተጠቋሚ ዕጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡-

 1. በዜግነት ኢትዮጵያዊ/ት ወይም የውጭ ሀገር ዜግነት ካለው/ላት በትውልድ ኢትዮጵያዊ/ት የሆነ/ች፤
 2. ዕድሜው/ዋ 30 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የሆነ/ች፤
 3. የዳይሬክተሮች የቦርድ አባል ሆኖ ቢመረጥ /ሆና ብትመረጥ ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ/ች፤
 4. ከታወቀ የከፍተኛ የትምህርት ተቋም ቢያንስ በመጀመሪያ ዲግሪ ወይም በአቻ የትምህርት ደረጃ የተመረቀ/ች፤
 5. የዳይሬክተሮች የቦርድ አባላት ስብስብ በባንክ ስራ፣ በፋይናንስ፣ በአካውንቲንግ፣ በማኔጅመንት፣ በኢኮኖሚክስ፣ በሕግ፣ በቢዝነስ አስተዳደር ፣ በኦዲቲንግ ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ወይም በኢንቨስትመንት ማኔጅመንት መሠረታዊ ክህሎትን /ችሎታን ያካተተ እና የፆታ ስብጥርን ያገናዘበ ቢሆን ይመረጣል፤
 6. የፋይናንስ ድርጅት የቦርድ ዳይሬክተር ያልሆነ/ች ወይም ዳይሬክተሩ/ሯ 10% ወይም ከዚያ በላይ የባለቤትነት ድርሻ ያልያዘበት/ችበት የንግድ ድርጅት፤
 7. የማንኛውም ባንክ ተቀጣሪ ሠራተኛ ያልሆነ/ች፤
 8. የቡና ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥቆማና አስመራጭ ኮሚቴ አባል ያልሆነ/ች፤
 9. በግሉ/ሏ ወይም ሌላ ባለአክስዮንን በመወከል በቡና ባንክ አ.ማ ውስጥ ለተከታታይ ስድስት ዓመታት በቦርድ አባልነት አገልግሎ/ላ ከሆነ/ች ከለቀቀበት/ችበት ጊዜ ጀምሮ ስድስት ዓመታት ያለፈው/ፋት፤
 10. በብሔራዊ ባንክ እምነት መሰረት ታማኝ ፣ ሐቀኛ፣ ጠንቃቃ እና መልካም ዝና ያለው/ላት፤
 11. መልካም የፋይናንስ ታሪክና አቋም ያለው/ያላት ፤ የንግድ ሥራን ከመተግበር ወይም ድርጅትን ከመምራት አኳያ በፍርድ ቤት የመክሰር ውሳኔ ያልተላለፈበት/ባት፣ ከታክስ እና ከባንክ ክፍያዎች ጋር በተያያዘ ግዴታዎቹን/ቿን በአግባቡ የተወጣ/ች፤
 12. መልካም ስነምግባር ያለው/ላት፣ከዚህ በፊት በንግድ ማህበር አደራጅነት፣ ዳይሬክተርነት፣ ስራ አስኪያጅነት፣ተቆጣጣሪነት፣ኦዲተርነት ወይም በሌሎች የአመራር ኃላፊነቶች ላይ ተመድቦ/ባ ሲሰራ/ስትሰራ ከኃላፊነቱ/ቷ ጋር በተያያዘ ወይም በማናቸውም ሌላ ሁኔታ በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ በእምነት ማጉደል፣ በስርቆት ፣ በማጭበርበር፣ በውንብድና ወይም በሌላ ለቦርድ አባልነት ብቁ በማያደርግ ተመሳሳይ ወንጀል በፍ/ቤት ተከሶ/ሳ የጥፋተኝነት ውሳኔ ያልተሰጠበት/ባት፤
 13. ከመንግስት ባለስልጣናት መረጃን በመደበቅ፣ የተሳሳቱ የሂሳብ ወይም ሌሎች ሰነዶችን በመስጠት፣ የተቆጣጣሪ አካላትን ማረጋገጫዎች ባለመቀበል፣ መስፈርቶችን ባለማሟላት ፣ የእርምት ወይም የማስተካከያ እርምጃዎችን ባለመውሰድ ሪከርድ የሌለበት/ባት፤
 14. በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በውጭ ሃገር በሚገኝ በማናቸውም በፈረሰ ባንክ ውስጥ ዳይሬክተር የነበረ/ች ከሆነ በቅድሚያ ከብሔራዊ ባንክ የጽሁፍ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል/ ምትችል፤
 15. ዕጩ ተጠቋሚው በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው ድርጅት ከሆነ፤ ድርጅቱን ወክሎ የሚያገለግል ቋሚ ተወካይ (የተፈጥሮ ሰው) መመደብ ያለበት ሲሆን ይህ ተወካይ ሁሉንም መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅበታል፤
 16. መስፈርቱን የሚያሟሉ ሴት ዕጩዎች ይበረታታሉ፤

 

ለበለጠ መረጃ ባለአክስዮኖች በስልክ ቁጥር 011-8-722845/011-1-264357 ደውለው ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

ማሳሰቢያ፤

ኮሚቴው ከጥቅምት 01 ቀን 2014 . በኋላ የሚቀርቡ ጥቆማዎችን የማይቀበል መሆኑን ከወዲሁ ያሳስባል!!!

NameDownloads
እጩ መጠቆሚያ ቅጽ

የቡና ባንክ አ.ማ

የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት አስመራጭ ኮሚቴ

Bunna Bank