የቡና ባንክ 7ኛ ዙር የህዝብና የጭነት ማመላለሻ ትራንስፖርት ዘርፍ ይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃ ግብር
የቡና ባንክ 7ኛ ዙር የህዝብና የጭነት ማመላለሻ ትራንስፖርት ዘርፍ ይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃ ግብር 1ኛ እጣ ቁጥር 4160417 የቤት አውቶ ለጃክሮስ አደባባይ ቅርንጫፍ ደንበኛ ፣ 2 ኛ እጣ ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ የዕጣ ቁጥር 2187063 ፣ ለሃና ማርያም ቅርንጫፍ ደንበኛ ወጥቷል።
ደንበኞቻችን እንኳን ደስ ያላችሁ ::
ቡና ባንክ
የባለ ራዕዮች ባንክ
የቡና ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ እና 6ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ
በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ አንቀፅ 366፣367፣ 370፣ 371፣ 372፣ 394 እና 400 እንዲሁም በባንኩ መመስረቻ ፅሑፍ አንቀፅ 9.4 እና በመተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ 6.3 መሰረት የቡና ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ እና 6ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ሕዳር 25 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ ስለሆም የባንኩ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም በሕጋዊ ተወካዮቻችሁ አማካኝነት በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ በጉባዔው ላይ እንድትገኙ ባንኩ በአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡
የአክሲዮን ማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ፡ 3,314,741,000 ብር፣
የአክሲዮን ማህበሩ የምዝገባ ቁጥር፡ AR/AA/3/0003357/2006፣
የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መ/ቤት የሚገኝበት ቦታ፡ አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የቤት ቁጥር፣ አዲስ፣
የ13ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፣
- ረቂቅ አጀንዳዎችን ማፅደቅ፣
- በባንኩ ውስጥ የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን እና የአዲስ አክሲዮኖችን ሽያጭ ማፅደቅ፤
- እ.ኤ.አ የ2021/22 የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፤
- እ.ኤ.አ የ2021/22 የውጭ ኦዲተሮችን ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርት ማዳመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፤
- እ.ኤ.አ የ2022/23 በጀት ዓመት የውጭ ኦዲተሮችን አበል መወሰን፤
- እ.ኤ.አ የ2022/23 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ አበልና እ.ኤ.አ የ2021/22 በጀት ዓመት ዓመታዊ ክፍያ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
- በዘመኑ የተጣራ ትርፍ አደላደል እና አከፋፈል ላይ የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ተወያይቶ ማጽደቅ፤
- የጉባዔውን ቃለ-ጉባዔ ማፅደቅ፣ የሚሉት ናቸው፡፡
የ6ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፣
- ረቂቅ አጀንዳዎችን ማጽደቅ፣
- የባንኩን የመመስረቻ ጽሁፍ ማሻሻያ ተወያይቶ ማጽደቅ፣
- የጉባዔውን ቃለጉባዔ ማጽደቅ፣ የሚሉት ናቸው፡፡
ማሳሰቢያ
- በጉባዔው ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው አካል በስብሰባው ላይ ለመገኘትና ድምፅ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ሰነድ ወይም ከስብሰባው ሦስት ቀን ቀደም ብሎ ቦሌ መንገድ ከወሎ ሰፈር አደባባይ ቀጥሎ ሩዋንዳ መታጠፊያ ከመደረሱ በፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 4ኛ ፎቅ የባንኩ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድረስ በመቅረብ የውክልና ቅጽ በመሙላት፣ የውክልና ቅፁን ዋናውንና አንድ ቅጂ እና የራሳቸውንም ሆነ የወካዮቻቸውን ኢትዮጵያዊ ዜግነት ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ አገር ዜግነት የሚያሳይ ሕጋዊ የታደሰ መታወቂያ/ፓስፖርት/ መንጃፈቃድ ዋናውን እና ቅጂውን ይዘው በመምጣት በጉባዔው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እናስታውቃለን፡፡
- በተጨማሪም የድርጅትና የማህበር ተወካዮች ድርጅቱን/ማህበሩን ወክለው በስብሰባው እንዲገኙና ድምፅ እንዲሰጡ የሚያረጋግጥ የተመዘገበ ቃለ ጉባዔ ወይም ስልጣን ባለው አካል የተሰጠ ውክልና ዋናውንና ቅጂውን ይዘው መቅረብ ያለባቸው መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
- የባንኩ መመስረቻ ጽሁፍ ማሻሻያ ሰነድ ከባንኩ ድረ-ገጽ ላይ በማውረድ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ ቦሌ መንገድ ከወሎ ሰፈር አደባባይ ቀጥሎ ሩዋንዳ መታጠፊያ ከመደረሱ በፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0111 580880/262822/262810 በመደወል ማግኘት ይችላሉ::
የዳይሬክተሮች ቦርድ
ቡና ባንክ አ.ማ
የባለራዕዮች ባንክ
አክሲዮኖችን በጨረታ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ቡና ባንክ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በወጣው መመሪያ ቁጥር FIS/01/2016 መሰረት የውጭ አገር ዜግነት ካላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለአክሲዮኖች የተረከባቸውን በቁጥር 7,611 የሆኑ አክሲዮኖች ፤ የአንዱ አክሲዮን ዋጋ ብር 100 ሆኖ፤ ጠቅላላ ዋጋቸው ብር 761,100.00 የሚያወጡ አክሲዮኖችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም የአንድ አክሲዮን የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 100.00 ሲሆን ፤ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው ግለሰብ ወይም ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ባላቸው ባለአክሲዮኖች የተያዙ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፤
- ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፤ የታደሰ መንጃ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ፤ ወይም ተጫራቾች ድርጅቶች ከሆኑ ድርጅቱ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የጸደቀ የመመስረቻ ጽሁፍ እና የመተዳደሪያ ደንብ ወይም ሌላ ተቀባይነት ያለው ማስረጃ ዋናውን እና ኮፒ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
- ተጫራቾች አንዱን አክሲዮን የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለፅ መግዛት የሚፈልጉትን ጠቅላላ የአክሲዮን ዋጋ ¼ኛ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሳይያያዝ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፤
- ተጫራቾች መግዛት የሚችሉት አነስተኛ የአክሲዮን ብዛት በቁጥር 500 እና የገንዘብ መጠኑ ደግሞ ብር 50,000/ሀምሳ ሺህ/ ሲሆን ፤ ከዚህ በታች የሆኑ አክሲዮኖችን ለመግዛት የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፤
- አክሲዮኖች የሚሸጡት በተጫራቾች የሚሰጠውን ዋጋ በማወዳደር ሲሆን ፤ የተሻለ ዋጋ የሚሰጡ ተጫራቾች ለመግዛት በገለጹት ዋጋ እና የተጠየቁትን አክሲዮኖች ብዛት ልክ በቅደም ተከተል ቅድሚያ ይሰጣል፡፡ ተጫራቾች ተወዳድረው የጨረታው አሸናፊ መሆናቸው በባንኩ ሲገለጽላቸው የተሻለ ዋጋ ለሰጡ ተወዳዳሪዎች ቅድሚያ በመሰጠቱ ምክንያት ሊገዙት ከጠየቁት የአክሲዮኖች ብዛት የቀነሰ ቢሆንም በቀጣይ የተሻለ ዋጋ የሰጠ ተወዳዳሪ የተረፉ አክሲዮኖችን ባቀረበው ዋጋ የመግዛት ግዴታ አለባቸው፤
- ከአንድ በላይ ተጫራቾች ተመሳሳይ ዋጋ ቢሰጡ እና ተራፊ አክሲዮኖች ሁለቱ ተጫራቾች ከጠየቁት የአክስዮን ብዛት ቢያንሱ ቀሪዎቹ አክሲዮኖች ተመሳሳይ ዋጋ ለሰጡ ተጫራቾች እኩል ይከፋፈላል፤
- ተጫራቾች ሌሎች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተመስርተው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፤
- የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ የጨረታው አሸናፊ መሆናቸው በተገለፀላቸው በ15 ቀን /በአስራ አምስት ቀናት/ ጊዜ ውስጥ ለባንኩ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው አሸናፊ በዚህ ጊዜ ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ለባንኩ ገቢ ካላደረጉ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፤
- ለጨረታ የቀረቡት አክሲዮኖች በሙሉ በአሸናፊዎች ከተገዙ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፤
- ከላይ የተገለጹትን የሚያሟላ ተጫራች ለጨረታው የተዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ እስከ ጥቅምት 09 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4 ሰዓት ድረስ በስራ ሰዓት ቦሌ ሩዋንዳ መዞሪያ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ 4ኛ ፎቅ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቀርበው በመውሰድ እና በመሙላት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ አሽገው ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤
- ጨረታው ጥቅምት 09 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በእለቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም የሚመለከታቸው ታዛቢዎች በተገኙበት ቦሌ ሩዋንዳ መዞሪያ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ 4ተኛ ፎቅ ላይ ይከፈታል፤
- በሌሎች ህጎችና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መመሪያዎች የተደነገጉ ደንቦች በዚህ ጨረታ ላይ ተፈፃሚነት አላቸው፤
- ባንኩ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥሮች +251 111 58-08-80 ወይም +251 111 26-28-22 መደወል ይችላሉ ቡና ባንክ አዲስ አበባ |
ተሸከርካሪ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር BB/PFMD/03/2022
ቡና ባንክ ከዚህ ቀደም ይጠቀምባቸው የነበሩ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ተሸከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ
የሰሌዳ ቁጥር
የተሸከርካሪው አይነት
የምርት ዘመን
የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር (ከተ.እ.ታ በፊት)
1
03-A60896
ሃዩንዳይ ክሬኤታ
2015
2,173,914.00
2
03-A69203
ሃዩንዳይ ክሬኤታ
2018
2,304,348.00
3
3-A70090
ሃዩንዳይ ክሬኤታ
2019
2,434,783.00
4
3-A70096
ሃዩንዳይ ክሬኤታ
2019
2,434,783.00
5
3-A70075
ሃዩንዳይ ክሬኤታ
2019
2,434,783.00
6
3-A70055
ሃዩንዳይ ክሬኤታ
2019
2,434,783.00
7
03- B04470
ሃዩንዳይ ክሬኤታ
2020
2,434,783.00
8
03- B08412
ሃዩንዳይ ክሬኤታ
2020
2,608,696.00
9
03- B08502
ሃዩንዳይ ክሬኤታ
2020
2,608,696.00
10
03- B11715
ሃዩንዳይ ክሬኤታ
2019
2,434,783.00
11
03- B11775
ሃዩንዳይ ክሬኤታ
2019
2,434,783.00
12
3-B21564
ሃዩንዳይ ክሬኤታ
2020
2,608,696.00
የጨረታ መመሪያዎች
- ተሸከርካሪዎችን መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ቡና ባንክ አራት ኪሎ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ህንፃ አንደኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የባንኩ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሃሴ 15 ቀን 2014 ዓ.ም ዘውትር በስራ ሰዓት በማንኛውም የባንኩ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 1019601000609 ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ገቢ በማድረግና ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ በማቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በመሙላት እስከ ነሃሴ 16 ቀን 2014 ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡ ጨረታው ነሃሴ 17 ቀን 2014 ዓ.ም ጠዋት 4፡20 ሰዓት የጨረታ ሰነድ በገዙበት ቦታ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ተሸከርካሪ የጨረታ የመነሻውን አስር በመቶ(10%) በቡና ባንክ አ.ማ ወይም “Bunna Bank S.C” ስም በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ከጨረታ ሰነዳቸውን ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ንብረቶቹን መመልከት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው አድራሻ መመልከት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ/ዎች ያሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)15 ይከፍላል፤ እንዲሁም ተጫራቾች ባሸነፉበት ዋጋ እና መንገድ ትራንስፖርት በሚገምተው የተሸከርካሪዎቹ ዋጋ ልዩነት ምክንያት የሚኖር ተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያ ገዥ ይከፍላል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ውስጥ ክፍያ ፈጽሞ ንብረቶቹን መረከብ ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ቡና ባንክ አ.ማ
የባለራዕዮች ባንክ!!
0111580879/0111261901
የአክሲዮን ሽያጭ ማስታወቂያ
- ታህሳስ 03 ቀን 2014 ዓ.ም በተደረገው የባንኩ ባለአክሲዮኖች 5ተኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የባንኩ ካፒታል ወደ ብር 6.5 ቢሊየን እንዲያድግ በሙሉ ድምጽ መወሰኑ ይታወሳል፡፡
- በመሆኑም የባለአክሲዮኖች 5ተኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ለዳይሬክተሮች ቦርድ በሰጠው ስልጣን መሰረት አዲስ አክሲዮኖችን በባንኩ የመተዳደርያ ደንብና አግባብነት ባላቸው የንግድ ህጉ ድንጋጌዎች መሰረት ለነባር ባለአክሲዮኖች እ.ኤ.አ. ግንቦት 31 ቀን 2022 ዓ.ም በባንኩ ባላቸው አክሲዮን መጠን ልክ እንዲደለደል ስለወሰነ ነባር ባለአክሲዮኖች የተደለደለላችሁን አክሲዮን ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 3 ላይ በተገለጸው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ማዞሪያ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 4ተኛ ፎቅ የባንኩ አክሲዮን አስተዳደር ዋና ክፍል ወይም በአቅራቢያችሁ በሚገኙ የባንኩ ቅርንጫፎች አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎችን ይዞ በአካል በመቅረብ የተደለደለላችሁን አክሲዮን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
- ስለሆነም ባለአስዮኖች የተደለደለላችሁን የአክሲዮን ድርሻ እ.ኤ.አ. ከሰኔ 15 ቀን 2022 እስከ ሐምሌ 15 ቀን 2022 ድረስ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ወይም በየአካባቢያችሁ ባሉ የባንኩ ቅርንጫፎች ቀርባችሁ መግዛት የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡ በተጨማሪም ከተደለደለላችሁ አክሲዮን በላይ ተጨማሪ አክሲዮን መግዛት የምትፈልጉ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ውስጥ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ እንገልጻለን፡፡
- ከላይ በተራ ቁጥር 3 በተጠቀሰው የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ቀርቦ አክሲዮኖቹን ያልገዛ ባለአክሲዮን የመግዛት የቅድሚያ መብቱን በፈቃዱ እንደተወ ስለሚቆጠር የአክሲዮን ድልድል ድርሻውን ባንኩ ለሌሎች ተጨማሪ አክሲዮን ለሚፈልጉ ነባር ባለአክሲዮኖች ወይም ለሌሎች አዲስ አክሲዮን ገዢዎች ለሽያጭ የሚያቀርብ መሆኑን አስቀድመን እናስታውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡
- ከላይ በተገለፀው መልኩ የተደለደለላችሁን አክሲዮኖች ለመግዛት በግምባር የምትቀርቡ ባለአክሲዮኖች የኢትዮጵያ ዜጋ መሆናችሁን የሚያረጋግጥ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ /ፖስፖርት/ መንጃ ፈቃድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ይዛችሁ መቅረብ የሚጠበቅባችሁ ሲሆን፤ በግምባር መቅረብ የማትችሉ ባለአክሲዮኖች አግባብነት ባለው አካል ተረጋግጦ የተመዘገበና የተሰጠ የውክልና ስልጣን ይዘው በሚቀርቡ ወኪሎቻችሁ በኩል የተደለደለላችሁን አክሲዮን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የባለአክሲዮን ወኪሎች የራሳቸውን ሕጋዊ መታወቂያና የውክልና ስልጣን ማስረጃ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ወካይ ባለአሲዮኖች የኢትዮጵያ ዜጋ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ /ፖስፖርት/ መንጃ ፈቃድ ፎቶ-ኮፒ ይዘው መቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን፤ ተወካዩ የወካይ ባለአክሲዮን ዜግነት ለማረጋገጥ ከላይ በተገለፀው መልኩ ስለሚያቀርቡት ሰነድ ትክክለኛነት ባንኩ በሚያዘጋጀው ፎርም ላይ በመፈረም ማረጋገጥ የሚጠበቅባቸው መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ የባንኩን አክሲዮን አስተዳደር በ0111-580880 ደውላችሁ ማነጋገር የምትችሉ መሆኑን አንገልፃለን፡፡
የዳይሬክተሮች ቦርድ
ለተከበራችሁ ደንበኞቻችን
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቁጥር FIS/04/2021 ባወጣው መመሪያ ሁሉም የገንዘብ ተቋማት የደንበኞቻቸውን ዝርዝር መረጃ በአግባቡ በማጣራት እና በማደራጀት በመረጃ ቋት ውስጥ መዝግበው መያዝ እንዳለባቸው ደንግጓል፡፡ በዚህም መሠረት የቅርብ ጊዜና ማንነትዎን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በአቅራቢያዎት በሚገኝ ቡና ባንክ ቅርንጫፍ በአካል ተገኝተው እስከ የካቲት 20 ቀን 2014 ዓ.ም አስፈላጊውን መረጃ እንድትሰጡ/እንድታሟሉ በድጋሚ እየጠየቅን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ መረጃ የማያሟሉ ደንበኞች ሂሳብ ወደ ማይንቀሳቀስ ሂሳብ መደብ /Deactivated Account Category/የሚለወጥ በመሆኑ በአካልም ሆነ በሌሎች ኤሌትሮኒክ አገልግሎት መስጫ መንገዶች/አማራጮች/ አገልግሎት ክልከላ የሚጣል መሆኑን በድጋሚ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
ቡና ባንክ
የባለራዕዮች ባንክ!
- Tenders
- Shareholders information

Invitation to Local Competitive Bid –no. - BIB/022/2021
Bunna International Bank S.C. (BIB) invites all interested and eligible bidders to
participate on the bid for the supply of the under listed items..Click here to download the result.

Invitation to Local Competitive Bid –no. - BIB/022/2021
Bunna International Bank S.C. (BIB) invites all interested and eligible bidders to participate on the bid for the supply of the under listed items..Click here to download the result

ቡና ባንክ ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ቡና ባንክ አ.ማን በዳይሬክተርነት ለመምራት የተመረጡ የቦርድ አባላት ዝርዝር
ቡና ባንክ ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ቡና ባንክ አ.ማን በዳይሬክተርነት ለመምራት የተመረጡ የቦርድ አባላት ዝርዝር .Click here to download the result.