Bunna Bank

Solomon mekbib

ቡና ባንክ በታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋይነት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆነ

6ኛ ዙር የታማኝ ግብር ከፋዮች የምስጋናና የዕውቅና ሽልማት መርሐ ግብር ትናንት መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም በአንድነት ፓርክ ተካሂዷል። በዚህ መርሃ ግብር ላይም ቡና ባንክ በ2016 የበጀት ዓመት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ግብር በመክፈል የበጀት አመቱ ታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋይ የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆኗል። የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትርን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሃገሪቱ ባለስልጣናት በተገኙበትና በአዲስ ፓርክ (ብሄራዊ ቤተመንግስት) ግብር አዳራሽ በተካሄደው በዚሁ ስነስርዓት በተለያዩ መስፈርቶች የተመረጡ 550 ተቋማት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። ከነዚህ መካከልም 66 ኩባንያዎች በፕላቲኒየም፣ 165 ኩባንያዎች በወርቅ እንዲሁም 319 ኩባንያዎች በብር ደረጃ ተሸላሚ ሆነዋል። ቡና ባንክ አምና በ2015 ዓ.ም በተካሄደው ተመሳሳይ መርሃ ግብር በታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋይነት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ እንደነበር ይታወሳል።

ቡና ባንክ በታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋይነት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆነ Read More »

15th Years of Anniversary

Dear Valued Shareholders and Customers, We congratulate you on Bunna Bank’s 15th years of anniversary. As we celebrate the 15th anniversary of Bunna Bank, we want to take this opportunity to express my sincere gratitude for your support and trust over the years. This milestone reflects not only our growth and achievements but also the strong relationships we have built with you.#Bunna_Bank #Bank_of_the_Visionaries #15_years_anniversary

15th Years of Anniversary Read More »

መልካም የመስቀል በዓል!

  ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ የቡና ቤተሰቦች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ። ቡና ባንክ ለሁላችሁም መልካም የመስቀል ደመራ በዓል ይመኛል! 🔥🔥 ቡና ባንክ የባለራዕዮች ባንክ! #CrossDay #BunnaBank #EthiopianBanks

መልካም የመስቀል በዓል! Read More »

መልካም በዓል!

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ የቡና ቤተሰቦች እንኳን ለደብረ ታቦር ( ቡሄ ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ! የቡና ባንክ ዲጂታል ባንኪንግን በመጠቀም ህይወትዎን ያቅልሉ። መልካም በዓል! ቡና ባንክ የባለራዕዮች ባንክ! #BunnaBank #Ethiopian_Banks #Ethiopia #ኢትዮጵያ #Buhe #ቡሄ

መልካም በዓል! Read More »

ዜና እረፍት

የቡና ባንክ ደ/ማርቆስ ዙሪያ አካባቢ፣ ራስ ቢትወድድ ቅርንጫፍ ባልደረባ የነበሩት አቶ ገላጋይ ታደለ ባደረባቸው ህመም ምክንያት ነሐሴ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የቡና ባንክ የስራ አመራር አካላትና መላው ሰራተኞች በአጠቃላይ የቡና ቤተሰቦች በባልደረባቸው ህልፈት የተሰማቸውን ከፍተኛ ሃዘን ይገልጻሉ። ለሟች እረፍተነፍስን፣ ለቤተሰቦቹ፣ ለቅርብ የስራ ባልደረቦቹና  በአጠቃላይ ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን ይመኛሉ።

ዜና እረፍት Read More »

የተሻሻለውን የቡና መተግበሪያ ሞክረውታል?

አዲሱን የቡና ባንክ የሞባይል መተግበሪያ አውርደዋል? 🚀✨ ውድ የቡና ቤተሰቦች የተሻሻለውን መተግበሪያችንን ዛሬውኑ አውርደው በእንከን የለሽ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ቀላልና ፈጣን የባንክ አገልግሎታችን እፎይ ብለው ደስታዎን ያጣጥሙ። 📱💰 Play Store (https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bunnabanksc.bunnamobile) App Store (https://apps.apple.com/se/app/bunna-bank-abol-mobile-banking/id6502711479?l=en-GB) #BunnaBank #MobileBanking #UpgradeNow

የተሻሻለውን የቡና መተግበሪያ ሞክረውታል? Read More »

[ivory-search id="5747" title="Custom Search Form"]

This will close in 0 seconds

error: