New to site?


Login

Lost password? (X)

Already have an account?


Signup

(X)
Farooq

Archive by Category "News"

HomeArchive by Category "News"
 • Author
  Genet Fekade
 • Comments
  0 Comments
 • Category

የባለራዕዮቹ ቡና ባንክ “እስቴ ቅርንጫፍ” ብሎ የሰየመውን 261ኛውን ቅርንጫፉን ከፍቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። ቅርንጫፉ በአማራ ክልላዊ መንግስት ደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ መካነየሱስ ከተማ ይገኛል።

 • Author
  Genet Fekade
 • Comments
  0 Comments
 • Category

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ 260ኛውን “ሃሙሲት” ቅርንጫፉን በሃሙሲት ከተማ ከፍቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። ቅርንጫፉ የኢትዮጵያን ሌላኛው ስም ቡናን ከሙሉ የባንክ አገልግሎት ጋር ይዞ ለደንበኞቹ ክፍት ሆኗል፡፡

 • Author
  Genet Fekade
 • Comments
  0 Comments
 • Category

የባለራዕዮች ባንክ የሆነው ቡና ባንክ ለገሀር ቅርንጫፉን በገና ዋዜማ ለደንበኞቹ ክፍት በማድረግ የቅርንጫፍ ቁጥሮቹን ወደ 259 አሳድጓል፡፡ አዲሱ ቅርንጫፍ በመዲናችን አዲስ አበባ ለገሀር አካባቢ ነው አገልግሎቱን መስጠት የጀመረው፡፡

 • Author
  Genet Fekade
 • Comments
  0 Comments
 • Category

ለዚህ ቀን በጤና ከደረስን በረከታችን ከዚህ ይጀምራል። ለመላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታችን ከባንካችን ይድረሳችሁ! መልካም የገና በአል ይሁንላችሁ!

ቡና ባንክ የቅርንጫፍ ቁጥሮቹን በመጨመር ደብረብርሃን ስላሴ እና ቻግኒ ቅርንጫፎቹን ከፍቶ ስራ አስጀምሯል፡፡ ባንኩ ተገልጋዮቹ ከአካባቢያቸው ሳይርቁ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ደንበኞቹ ወዳሉበት መምጣቱን በመቀጠል በዛሬው ዕለት 257 ኛ እና 258 ኛ ቅርንጫፎቹን በደብረብርሃን እና ቻግኒ ከፍቷል፡፡

እባክዎ ከ8ኛው ደቂቃ ጀምሮ ይከታተሉ https://l.facebook.com/l.php?u=https%3A%2F%2Fwww.youtube.com%2Fwatch%3Fv%3DrYLYBxKJ4Cc%26feature%3Dyoutu.be%26fbclid%3DIwAR2cA7fiZeaA_Mjbz4jNdOOSBfvA_Dz5TQT2aE9sAvpmUWZEOzjyr2nZiOU&h=AT1jK4rI5kvMJhAb14oSTaw4Wsdhx64yTR2puodfxqUDjskBjkjtG-lR62VFvE2rSE_YsCYVuFDo_nPckXT-cqQ3btZLQnQBHtWuiguBLLLPyLZiWdYm_-bZBN_ytMIExgNy&__tn__=-UK-R&c[0]=AT1YIpnZxSbn7M_JuVcpZffpptKR4SmwkvpxVQh3BDwAv7AZXT6E7ZZLj6U4qiO5I4V-bznIRzwlns7-YsfcWPu1AwfRePIP78p5Soxuhg-3DNfSItXSB4kz9fmFMzoVgRSTjaENwjcgHdi2tz-fKEsPqNXjtnzA8g7Axa05IdxXKNWGtzGQ5G9JQzUkF7_Wgi7UP9-2asvSbc_0FUgFeHYqRQ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንዳስታወቀው በክልሉ ተቋርጦ የነበረው ከ1ዐዐ ሺህ ብር በታች የአሮጌ ብር ኖት ቅያሬ በድጋሚ ተጀምሯል።መንግስት በክልሉ በወሰደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ምክንያት የአሮጌ ብር ኖት ቅያሬው ተቋርጦ እንደነበር አስታውሶ አሁን ላይ በተወሰኑ የክልሉ ከተሞች የመብራትና የኢንተርኔት አገልግሎት በመጀመሩ በእነዚሁ አካባቢዎች ባንኮች ሥራ እንዲጀምሩ እየተደረገ ይገኛል ብሏል። በዚህ መሰረት ተቋርጦ የነበረውን የአሮጌ ብር ኖት ቅያሬ […]

 • Author
  Genet Fekade
 • Comments
  0 Comments
 • Category

ቡና ባንክ የቅርንጫፍ ቁጥሮቹን ወደ 256 አሳድጓል በዚህም ይበልጠ ወደደንበኞቹ እየቀረበ ይገኛል፡፡   የባለራዕዮቹ ባንክ ውጤታማ ጉዞውን በመቀጠል በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ቅርንጫፎችን ከፍቷል፡፡ በአማራ ክልል ጂጋ፣ ጃዊ፣ ይፋት፣ ደነባ እና እነዋሪ አዳዲስ የተከፈቱት ቅርንጫፎች በቅርቡ ለደንበኞች አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል። በአዲስ አበባ እንቁላል ፋብሪካና ብስራተ ገብርኤል ደግሞ ሁለት አዳዲስ ቅርንጫፎች ተከፍተው አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል። ባንኩ በቀጣይም […]

hghttps://www.facebook.com/174917042577946/videos/498728114437399/?__cft__[0]=AZU809lUFA_T8JkWJpI9LzAD2LOCiQTzFaPmr-Ln4Nkahr9JzEHP1QvSn80TgDbVn4uhxy46lms3L6cka8HcPp6OINqA67Dug00jv7OYpvDwbNV_JyXqkerJVQpLwkiyQiYCLjCsP7vgUvFN8WLyCT_X2kGYO0Ld_2wr6IF2ZXGgdpl-gePnmD_S0-iP4XD5OKqC7TIC6gYtYoI8W0n5PSw4fqu1cjvqWZ3Xda2p1ee1d_oT5iesMQkesB2FKvmLGV4hNJUlx8bCQHQ7KSdvy0iZ&__tn__=-UK-R

በብስራት ስፖርት https://t.me/bunnabanksc/228 በቅኝት በኳስ ሜዳ https://l.facebook.com/l.php?u=https%3A%2F%2Ft.me%2Fkegnitbekuasmeda%2F381%3Ffbclid%3DIwAR3IYu8UgqDsnCjinecKEYiUBhpl3S1gafYuNe1VMxgmPo0uUI4F5FPuBoU&h=AT3zmtOvGbg_u9neFOz8w0ndUNqUoGlf5bwEvaIgxJtCMh0pWPSWZKfuZSUI2HWbvYc7ZFN6InuYNS8MpkJSRv51d5z2lia2Nhk-RvQy-IVr4nmLNPZIQvweGVU91kYno4N6&__tn__=-UK-R&c[0]=AT0UKXEL8RDBYZD23-UrnSN0AtvzOihJe1HXUkZjaPgpb0A2-NM9nZimPD3SNkXfoJ88ww3Z0wLWJbai7JCBRioJUrCjamakeuuRmEyhLNl0bvuv6IvHqyS9dZ1aFGM1p_Ql5SSrqk90_waTkyQgF4_kcmVl15w6JFM2ssh3k72DZB7wE8N86Kz3iD4pXnnhlltOxr89Lm-tjvnYGiQhLActkQቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ የ11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 4ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ


በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ አንቀጽ 418፣ 419 እና 423 እንዲሁም በባንኩ መመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 11.3.7 እና በመተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 6.3 መሠረት የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 4ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ ታህሳስ 11 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ ጦርሃይሎች አካባቢ በሚገኘው ጎልፍ ክለብ ውስጥ ይካሄዳል፡፡

ስለሆነም የባንኩ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም በሕጋዊ ተወካዮቻችሁ አማካኝነት በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ ጉባኤው ላይ እንድትገኙ ባንኩ በአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የ4ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

1) ረቂቅ አጀንዳዎችን ማጽደቅ፣

2) በባንኩ የመመስረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ

3) የጉባኤውን ቃለ-ጉባኤ ማጽደቅ

የ11ኛ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

1) ረቂቅ አጀንዳዎችን ማጽደቅ፣

2) በባንኩ ውስጥ የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን እና የአዲስ አክሲዮኖችን ሽያጭ መርምሮ ማጽደቅ፣

3) እ.ኤ.አ የ2019/20 የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ፣

4) እ.ኤ.አ የ2019/20 የውጭ ኦዲተሮች ቦርድ ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርትን ማዳመጥ፣

5) በተራ ቁጥር 3 እና 4 የቀረቡትን ሪፖርቶች ተወያይቶ ማጽደቅ፣

6) የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማ እና ምርጫ አፈፃፀም የአሰራር ደንብ ማሻሻያን መርምሮ ማጸደቅና የአስመራጭ ኮሚቴ አባላት አበልን መወሰን፣

7) የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴን መምረጥ፣

8) እ.ኤ.አ የ2020/21 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ አበልና ዓመታዊ ክፍያ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣

9) እ.ኤ.አ የ2020/21 በጀት ዓመት የውጭ ኦዲተሮችን ሹመት ማጽደቅና አበል መወሰን፣

10) በዘመኑ የተጣራ ትርፍ አደላደል እና አከፋፈል ላይ የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ መወሰን፣

11) የጉባኤውን ቃለ-ጉባኤ ማጽደቅ፣ የሚሉት ናቸው፡፡

ማሳሰቢያ

1. በጉባኤው ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች አግባብነት ካለውና ሕጋዊ ውክልና መስጠት ከሚችል የመንግሥት አካል የተሰጠ’ በስብሰባው ላይ ለመገኘትና ድምጽ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ሰነድ ወይም ከስብሰባው ሶስት ቀን ቀደም ብሎ ቦሌ መንገድ ከወሎ ሰፈር አደባባይ ቀጥሎ ርዋንዳ መታጠፊያ ከመድረሱ በፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 4ኛ ፎቅ የባንኩ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድርስ በመቅረብ የውክልና ፎርም (ቅጽ) በመሙላት፣ ሌላ ሰው በመወከል የውክልና ሰነዱን ወይም ቅጹን ዋናውንና አንድ ቅጂ ይዘው በመምጣት በጉባዔው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እናስታውቃለን፡፡

2. ባለአክስዮኖችም ሆኑ ህጋዊ ወኪሎቻቸው ወደ ስብሰባው ቦታ ሲመጡ የራሳቸውንም ሆነ የተወካዮቻቸውን ሕጋዊ የታደሰ መታወቂያ ካርድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን መያዝ አለባቸው፡፡

3. ባንኩ የባለአክሲዮኖችን የመለያ ቁጥር ባስመዘገባችሁት ተንቀሳቃሽ ስልክ የሚልክ ሲሆን& ይህንኑ ቁጥር በስብሰባው ዕለት ይዛችሁ እንድትመጡ በአጽንኦት እንጠይቃለን፡፡

4. ከላይ በተ.ቁ. 2 ላይ የተገለፀውን የወካዩን ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሚያረጋግጥ ሕጋዊና የታደሰ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ኮፒ ይዘው የማይመጡ ተወካዮች በጉባኤው ላይ መሳተፍ የማይችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡ በተጨማሪም የድርጅት ተወካዮች ድርጅቱን ወክለው በስብሰባው እንዲገኙና ድምጽ እንዲሰጡ መወከላቸውን የሚያረጋግጥ የተመዘገበ ቃለ-ጉባዔ ወይም በውል አዋዋይ ፊት የተሰጠ ውክልና ዋናውን እና ኮፒውን ይዘው መቅረብ ያለባቸው መሆኑን እናስታውቃለን፣፡

5. የብሄራዊ ባንክ ያስቀመጠውን የውክልና አሰጣጥ መጠን ገደብ ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ለጊዜው ያነሳ በመሆኑ ወረርሽኙን ለመከላከል ሲባል ባለአክሲዮኖች በጉባዔው በውክልና እንዲሳተፉ ይበረታታሉ፡፡

6. ተጨማሪ መረጃ ቦሌ መንገድ ከወሎ ሰፈር አደባባይ ቀጥሎ ወደሩዋንዳ መታጠፊያ ከመድረሱ በፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ 0111580880 / 262822 / 262810 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ

የዳይሬክተሮች ቦርድ

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ

የባለራዕዮች ባንክ!!!

Bunna Bank