የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የባለአክሲዮኖች መረጃ ወደ ማዕከላዊ የሠነዶች መዋዕለንዋዮች ግምጃ ቤት በኤሌክትሮኒክ ዘዴ ለመተካት እና የባለአክሲዮኖችን መረጃ ማሟላት አስፈላጊ በመሆኑ መረጃውን እስከአሁን ያላሟላችሁ የቡና ባንክ ባለአክሲዮኖች የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ካርድ ኮፒ፣ ወይም የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ቁጥር( FAN-16-Digit)፣ እና ባለአክሲዮኑ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ድርጅት ከሆነ የታክስ መለያ ቁጥር (TIN) እና የወኪሉ ሰው ሙሉ መረጃ በዋናው መ/ቤት 4ኛ ፎቅ አክሲዮን አስተዳደር ክፍል ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ የቡና ባንክ ቅርንጫፍ እስከ ሃምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም. በመቅረብ እንዲያሳውቁን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
እባክዎ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን የኦንላይን ፎርም ይሙሉ
https://forms.gle/Qv5UzYKjfs38MzuLA
ቡና ባንክ
የባለራዕዮች ባንክ