New to site?


Login

Lost password? (X)

Already have an account?


Signup

(X)
Farooq

Pay your Bill at no extra cost! Apply Now Bunna Bank ATM, Debit or Prepaid card are Faster, safer and more convenient than cash ReadMore Bank wherever, whenever from the convenience of your phone. Mobile Banking Readmore ቡና የወጣቶች ተቀማጭ ሒሳብ የዚህ ተቀማጭ ሒሳብ አገልግሎት ዓብይ አላማዎች የወጣቱን የቁጠባ ፍላጎት እና ባሕል እንዲዳብር ማበረታታት ነው፡፡ በተጨማሪም የሕፃናት የማያቋርጥ ተቀማጭ ሒሳብ ደንበኛ ሆነው በሕጉ መሠረት ...፤ Readmore EASY TRANSFER THE PERFECT SOLUTION በቡና ካርድ በቡና ካርድ የትም ይመቸኛል!! EASY TRANSFER THE PERFECT SOLUTION USSD BANKING Feature ->Deposit / Credit Transaction Alert
->Withdrawal / Debit Transaction Alert
->Account Balance Alert
->Due credit payment
->Debit card transaction and payment due date
EASY TRANSFER THE PERFECT SOLUTION There's a card for you -> 24/7 ATM cash
-> Shop at merchants
-> Directly debit fund in Ethiopian Birr from your bank Account
-> Daily limit 4999 ETB at local ATMs
-> Accepted at all Ethswitch ATM network accross Ethiopia
-> And More ..
USSD BANKING Bank on the go with our new USSD code at no data cost ReadMore Slide EASY TRANSFER THE PERFECT SOLUTION በቡና ካርድ በቡና ካርድ የትም ይመቸኛል!!
WELCOME TO BUNNA BANK

UNLIMITED SERVICES

We appreciate the opportunity to provide you
Want a pre-paid or Debit card that suits your lifestyle?
A Bunna Bank ATM, Debit Card allow you the flexible to shop
committed to innovativeness and high quality.

RECEIVE YOUR MONEY

 ጥቅምት 1 ቀን 2014 ዓ.ም

 

የአክሲዮን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቁጥር ፋኢስ/ባሱዳ/458/19 ሚያዚያ 29 ቀን 2011 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ የተለያየ ዋጋ ያላቸው አክሲዮኖች በጨረታ መሸጥ እንዳለባቸው አሳውቆናል፡፡ ስለሆነም የአንዱ አክሲዮን ዋጋ ብር 100.00 (አንድ መቶ) ሆኖ  277,700 አክሲዮኖችን ለመግዛት ፈቃደኛ የሆነ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘትን መስፈርቶች በማሟላት እና እንዲቀርቡ የተጠየቁትን ማስረጃዎች በማቅረብ መወዳደር ይችላል፡-

 1. ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው ግለሰብ ወይም ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ባላቸው ባለአክሲዮኖች የተያዙ ድርጅቶች፤
 2. ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ለመውሰድ ሲመጡ የተጫራቹን ማንነት የሚያረጋግጥ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፤ የታደሰ መንጃ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ፎቶ ኮፒ፤ ወይም ተጫራቹ ድርጅት ከሆነ ድርጅቱ በሰነዶች ማ/ም/ ኤጀንሲ የጸደቀ የመመስረቻ ጽሁፍ እና የመተዳደሪያ ደንብ ወይም ሌላ ተቀባይነት ያለው ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 3. ተጫራቾች አንዱን አክሲዮን የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለፅ መግዛት የሚፈልጉትን ጠቅላላ የአክሲዮን ዋጋ ¼ኛ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው:: የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሳይያያዝ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም::
 4. ተጫራቾች መግዛት የሚችሉት አነስተኛ የአክሲዮን ብዛት በቁጥር 500 እና የገንዘብ መጠኑ ደግሞ ብር 50,000 /ሀምሳ ሺህ/ ሲሆን፤ ከዚህ በታች የሆኑ አክሲዮኖችን ለመግዛት የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፤
 5. አክሲዮኖች የሚሸጡት በተጫራቾች የሚሰጠውን ዋጋ በማወዳደር ሲሆን፤ የተሻለ ዋጋ የሚሰጡ ተጫራቾች ለመግዛት በገለጹት ዋጋ እና የተጠየቁትን አክሲዮኖች ብዛት ልክ በቅደም ተከተል ቅድሚያ ይሰጣል፡፡
 6. ተጫራቾች ተወዳድረው የጨረታው አሸናፊ መሆናቸው በባንኩ ሲገለጽላቸው የተሻለ ዋጋ ለሰጡ ተወዳዳሪዎች ቅድሚያ በመሰጠቱ ምክንያት ሊገዙት ከጠየቁት የአክሲዮኖች ብዛት የቀነሰ ቢሆንም በቀጣይ የተሻለ ዋጋ የሰጠ ተወዳዳሪ የተረፉ አክሲዮኖችን ባቀረበው ዋጋ የመግዛት ግዴታ አለባቸው፤
 7. ከአንድ በላይ ተጫራቾች ተመሳሳይ ዋጋ ቢሰጡ እና ተራፊ አክሲዮኖች እነዚህ ተጫራቾች ከጠየቁት የአክስዮን ብዛት ቢያንሱ ቀሪዎቹ አክሲዮኖች ተመሳሳይ ዋጋ ለሰጡ ተጫራቾች እኩል ይከፋፈላል፤
 8. ተጫራቾች ሌሎች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፤
 9. የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ የጨረታው አሸናፊ መሆናቸው በተገለፀላቸው በ5 ቀን /በአምስት ቀናት/ ጊዜ ውስጥ ለባንኩ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው አሸናፊ በዚህ ጊዜ ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ለባንኩ ገቢ ካላደረጉ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፤
 10. ለጨረታ የቀረቡት አክሲዮኖች በሙሉ በአሸናፊዎች ከተገዙ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፤
 11. ከላይ የተገለጹትን የሚያሟላ ተጫራች ለጨረታው የተዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ እስከ ጥቅምት 15 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በስራ ሰዓት ቦሌ ሩዋንዳ መዞሪያ በሚገኘው የባንኩ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቀርበው በመውሰድ እና በመሙላት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ አሽገው ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤
 12. ጨረታው ጥቅምት 15 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በእለቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም የሚመለከታቸው ታዛቢዎች በተገኙበት ቦሌ ሩዋንዳ መዞሪያ በሚገኘው ህንፃ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፤
 13. የጨረታው አሸናፊዎች የጨረታው አሸናፊ መሆናቸው እንደተገለጸላቸው በተ.ቁ. 2 የተጠቀሱትን ሰነዶች ዋና ቅጂ /ኦርጅናል ኮፒ/ ለባንኩ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
 14. በሌሎች ህጎችና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መመሪያዎች የተደነገጉ ደንቦች በዚህ ጨረታ ላይ ተፈፃሚነት አላቸው፤
 15. ባንኩ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥሮች

+251 111 58-08-80 ወይም

+251 111 26-28-22 መደወል ይችላሉ

ቡና ባንክ አ.ማ.

አዲስ አበባ

 

 

ለቡና ባንክ አ.ማ. ባለአክስዮኖች

የቡና ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር SBB/79/2021 / SBB/71/2019 እና በዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምልመላ እና ምርጫ ማስፈጸሚያ የአሰራር ደንብ መሠረት እጩ የቦርድ አባላትን አወዳድሮ አጠናቋል፡፡

በዚህ መሠረት ለእጩ የቦርድ አባላት ከተጠቆሙት መካከል ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘረው ተወዳዳሪዎች ባገኙት ድምጽ መሠረት የቀረቡ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

ተፅእኖ ፈጣሪ ባልሆኑ ባለአክስዮኖች የተጠቆሙ ዕጩ ተወዳዳሪዎች፡-

 1. አምባሳደር አለማየሁ ሰዋገኝ
 2. ሹምዬ ሲሳይ ገብሩ
 3. ይግረም ክንዴ ተገኝ
 4. ገደፋው መሐሪ መላኩ
 5. ሞላልኝ መለሰ መንግስቱ
 6. ዶ/ር ክንዴ ተስፋዬ ፋንታዬ

ተፅእኖ ፈጣሪ በሆኑና ተፅእኖ ፈጣሪ ባልሆኑ ባለአክስዮኖች የተጠቆሙ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ፡-                

 1. እሱባለው እጅጉ ጌታሁን
 2. ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ (አበባየሁ አበበ ውንድሙ)
 3. ዶ/ር ስለሺ ደምሴ ያለው
 4. ደረጄ መኮንን ዘውዱ
 5. ኤልሳቤጥ ጉልማ አዋጅ
 6. ዮናስ ጌትነት አለሙ
 7. ኃይለየሱስ ዳኜ ምትኩ
 8. ዶ/ር ሰውአለ አባተ አያሌው
 9. ዋሲሁን አባተ አበበ
 10. አብርሃም ስዩም ንጋቱ
 11. ላቀው ብርሃኑ ወልዴ
 12. ዘውዱ በለጠ ገደፋው

 

ተጠባባቂዎች

 1. ማንደፍሮት በላይ ፈንታ
 2. አዳም መላኩ ተረፈ
 3. ሰሎሞን ደምሴ ገ/ማርያም
 4. አልማው አዲስ አድገህ
 5. ተስፋዬ ኪዳኔ ያለም
 6. አያሌው ክንፈ ወ/ሰማይት
 7. አስቻለው ካሳ ዘውዴ
 8. ሙሉጌታ አባተ መኮንን
 9. ዶ/ር መኮንን አይችልሁም ቢሻው

 

የቡና ባንክ አ.ማ

የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ

Bunna Bank