ለቡና ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች የቀረበ የአክሲዮን ሽያጭ ጥሪ ማስታወቂያ
ቡና ባንክ አ.ማ የኢትዮጵያ ካፒታል ገብያ ባለስልጣን ባፀደቀዉ ደንበኛ ሳቢ መግለጫ እና በተሰጠ ፍቃድ መሰረት ከነሀሴ 08 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ 2,587,002 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሰማንያ ሰባት ሺህ ሁለት) መደበኛ አክሲዮኖችን በአንድ አክሲዮን ዋጋ ብር 120 (አንድ መቶ ሃያ ብር) ሽያጭ የሚያከናዉን መሆኑን በደስታ ይገልፃል፡፡
በቡና ባንክ ደንበኛ ሳቢ መግለጫ ላይ እንደተመለከተዉ ነባር ባለአክሲዮኞች ባላቸው አክሲዮኖች መጠን ልክ አዲስ አክሲዮኖችን እንዲገዙ የተደለደለ ሲሆን በነባር ባለአክሲዮኖች ያልተገዙ አክሲዮኖች በተመለከተ ለመግዛት ፍላጎታችሁን ለምትገልጹ ነባር ባለአክሲዮኖች የሚደለደል ይሆናል፡፡
በመሆኑም የተደለደለላችሁን አዲስ አክሲዮኖችም ይሁን በነባር ባለአክሲዮኖች ያልተገዙት አክሲዮኖች ለመግዛት ፍላጎት ያላችሁ ነባር ባለአክሲዮኖች አክሲዮኖችን ለመግዛት ትችሉ ዘንድ በኢትዮጲያ የካፒታል ገቢያ ባለስልጣን እዉቅና ከተሰጣቸው የሰነድ ሙዓለንዋይ አገበያዮች (ደላሎች) የግብይት ሂሳብ (Trading Account) በመክፈት የአክሲዮን ገዥዉን እንድትፈፅሙ ባንኩ ጥሪዉን ያቀርባል፡፡
ባለአክሲዮኖች አክሲዮኖችን ለመግዛት የሚከተሉትን አስፈላጊ ሰነዶች ይዘዉ ሊቀርቡ ይገባል ፡፡
- የፋይዳ መታወቂያ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)
- የኢሜይል አድራሻ
- በተወካይ አማካኝነት የሚፈፀም ከሆነ የውክልና ማስረጃ፡፡
ማሳሰብያ፡ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የጸደቀው የደንበኛ ሳቢ መግለጫ እና ተያያዥ ሰነዶች በባንኩ ድህረ-ገጽ ላይ የሚገኝ ሲሆን ባለአክሲዮኖች ደንበኛ ሳቢ መግለጫዉን በሙሉ እንዲያነቡ ይበረታታሉ፤ ለዉሳኔ የተቸገሩ ከሆነ በኢትዮጲያ የካፒታል ገቢያ ባለስልጣን ፍቃድ ከተሰጣቸዉ ገለልተኛ የኢንቨስትመንት አማካሪዎች ምክር ይጠይቁ፡፡
የደንበኛ ሳቢ መግለጫዉ መፅደቅ ሰነድሙዓለ ንዋዮችን ባለሃብቶች እንዲገዙ የተሰጠ ምክር ወይም ድጋፍ ተደርጎ አይወሰድም፡፡
ይህ ማስታወቂያ በኢትዮጵያ ካፒታል ገብያ ባለስልጣን ፍቃድ አግኝቷል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡ ቡና ባንክ አክሲዮን ማህበር ዋና መስሪያ ቤት ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አፍሪካ ጎዳና በአካል ቀርቦ ማናገር ወይም በስልክ ቁጥር +25111580880 ሞባይል +251911006396/+251931795160/+251910636306
ቡና ባንክ የባለራዕዮች ባንክ!
