Bunna Bank

Kalkidan Debela

የቡና ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 17ኛ መደበኛ እና 8ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔዎች ጥሪ የስብሰባ ቀን ማስተካከያ

የቡና ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 17ኛ መደበኛ እና 8ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔዎች ጥሪ የስብሰባ ቀን ማስተካከያ የተከበራችሁ የቡና ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ አንቀፅ 366/1/፣ 367/1/፣ 370፣ እና በባንኩ መመስረቻ ፅሑፍ አንቀፅ 21 እና 22 መሰረት የቡና ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 17ኛ መደበኛ እና 8ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ህዳር 12 ቀን 2019 ዓ.ም እንደሚከናወን ማሳወቃችን ይታወሳል፡፡ ነገር ግን ከባንኩ አቅም በላይ በሆነ ምክንያት  የስብሰባ ቀኑ ወደ ህዳር 20 ቀን 2019 ዓ.ም መዘዋወሩን ከይቅርታ ጋር እናሳውቃለን፡፡ በዚህ መሰረት ጉባኤው ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ፣ ሲኤምሲ አደባባይ  አካባቢ በሚገኘው፣ በአዲስ ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል ስለሚያካሂድ፤ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ተወካዮች በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ በጉባዔው ላይ እንድትገኙ የማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ የአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡ አክሲዮን ማህበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች፣ የአክሲዮን ማህበሩ ስም፡- ቡና ባንክ አክሲዮን ማህበር፣ የአክሲዮን ማህበሩ ዓይነት፡- የባንክ ሥራ ላይ የተሰማራ አክሲዮን ማህበር፣ የአክሲዮን ማህበሩ የተፈረመና የተከፈለ ዋና ገንዘብ /ካፒታል/፡- 6,189,559,800 ብር፣ የአክሲዮን ማህበሩ የምዝገባ ቁጥር፡-AR/AA/3/0003357/2006፣ የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መ/ቤት አድራሻ፡-አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የቤት ቁጥር አዲስ፣ ድረ ገጽ፡ http://www.bunnabanksc.com/ የ17ኛው ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፣ በባንኩ ውስጥ የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማጽደቅ፤ እ.ኤ.አ የ2025/26 የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥና መወሰን፤ እ.ኤ.አ የ2025/26 የውጭ ኦዲተሮችን ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርት ማዳመጥና ማጽደቅ፤ ባንኩን ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የሚያገለግሉ የውጭ ኦዲተሮችን ሹመት ማጽደቅና አበላቸውን መወሰን፣ እ.ኤ.አ የ2026/27 ሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ አበልና እ.ኤ.አ የ2025/26 ሒሳብ ዓመት ዓመታዊ ክፍያ መወሰን፤ እ.ኤ.አ በ2025/26 ሒሳብ ዓመት የተጣራ ትርፍ ድልድልና ክፍፍል ላይ ተወያይቶ መወሰን፣ የጉባዔውን ቃለጉባዔ ማጽደቅ፣ የሚሉት ናቸው፡፡ የ8ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፣ የጉርሻ አክሲዮንን / Bonus Share / በተመለከተ ተወያይቶ መወሰን፤ የባንኩን መመስረቻ ጽሁፍ ማሻሻል፤ የጉባዔውን ቃለጉባዔ ማጽደቅ፣ የሚሉት ናቸው፡፡ ማሳሰቢያ በጉባዔው ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ስልጣን ባለው አካል የተሰጠ የውክልና ሰነድ ወይም በንግድ ህግ አንቀጽ 377 መሰረት ጉባዔው ከመካሄዱ ሦስት ቀን በፊት በባንኩ ዋና መ/ቤት አክሲዮን አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ በባንኩ የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ በመሙላትና በመፈረም ተወካይ መሾምና ተወካዩም የውክልና ማስረጃውን በመያዝ የጉባዔው ተካፋይ ለመሆንና ድምጽ ለመስጠት የሚችል መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡ ሆኖም አንድ ባለአክሲዮን በማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ በማንኛውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ሰው ብቻ መሆኑን እናሳስባለን፡፡ የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን የሚያሳይ የብሔራዊ መታወቂያ / ፋይዳ/ እና የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ዋናውንና ኮፒ በመያዝ በጉባዔው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የሆኑ የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈበት መታወቂያ /ቢጫ ካርድ/ ይዘው እንዲቀርቡ እናሳውቃለን፡፡ የድርጅትና የማህበር ተወካዮች ድርጅቱን/ማህበሩን ወክለው በስብሰባው እንዲገኙና ድምፅ እንዲሰጡ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዘው መቅረብ ያለባቸው መሆኑን በአክብሮት እናስታውቃለን፡፡ የሚወከሉ ባለአክሲዮኖች የሚቀበሉት የውክልና መጠን የራሳቸውን አክሲዮን ጨምሮ ከባንኩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ ከአስር በመቶ /10% / መብለጥ የለበትም፡፡ ባለአክሲዮኖች በስራ ላይ ያሉ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትና ሰራተኞች በባለአክሲዮኖች ጉባዔ ላይ እንዲሳተፉና ድምጽ እንዲሰጡ መወከል አይችሉም፡፡ የጉባዔው ቦታ ከሲኤምሲ ቤቶች በተቃራኒ ከፀሐይ ሪል ስቴት አጠገብ ወደወሰን መሄጃ በስተግራ በኩል የሚገኘው አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል መሆኑን ያስታውሱ፡፡ የቡና ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ Call Us 8501 የባለራዕዮች ባንክ! Bank of the visionaries!   www.bunnabanksc.com    

የቡና ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 17ኛ መደበኛ እና 8ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔዎች ጥሪ የስብሰባ ቀን ማስተካከያ Read More »

የቡና ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 17ኛ መደበኛ እና 8ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔዎች ጥሪ

የተከበራችሁ የቡና ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ አንቀፅ 366/1/፣ 367/1/፣ 370፣ እና በባንኩ መመስረቻ ፅሑፍ አንቀፅ 21 እና 22 መሰረት የቡና ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 17ኛ መደበኛ እና 8ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ህዳር 12 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ፣ ሲኤምሲ አደባባይ  አካባቢ በሚገኘው፣ በአዲስ ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል ስለሚያካሂድ፤ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ተወካዮች በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ በጉባዔው ላይ እንድትገኙ የማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ የአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡ አክሲዮን ማህበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች፣ የአክሲዮን ማህበሩ ስም፡- ቡና ባንክ አክሲዮን ማህበር፣ የአክሲዮን ማህበሩ ዓይነት፡- የባንክ ሥራ ላይ የተሰማራ አክሲዮን ማህበር፣ የአክሲዮን ማህበሩ የተፈረመና የተከፈለ ዋና ገንዘብ /ካፒታል/፡- 6,189,559,800 ብር፣ የአክሲዮን ማህበሩ የምዝገባ ቁጥር፡-AR/AA/3/0003357/2006፣ የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መ/ቤት አድራሻ፡-አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የቤት ቁጥር አዲስ፣ ድረ ገጽ፡ http://www.bunnabanksc.com/ የ17ኛው ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፣ በባንኩ ውስጥ የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማጽደቅ፤ እ.ኤ.አ የ2025/26 የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥና መወሰን፤ እ.ኤ.አ የ2025/26 የውጭ ኦዲተሮችን ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርት ማዳመጥና ማጽደቅ፤ ባንኩን ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የሚያገለግሉ የውጭ ኦዲተሮችን ሹመት ማጽደቅና አበላቸውን መወሰን፣ እ.ኤ.አ የ2026/27 ሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ አበልና እ.ኤ.አ የ2025/26 ሒሳብ ዓመት ዓመታዊ ክፍያ መወሰን፤ እ.ኤ.አ በ2025/26 ሒሳብ ዓመት የተጣራ ትርፍ ድልድልና ክፍፍል ላይ ተወያይቶ መወሰን፣ የጉባዔውን ቃለጉባዔ ማጽደቅ፣ የሚሉት ናቸው፡፡ የ8ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፣ የጉርሻ አክሲዮንን / Bonus Share / በተመለከተ ተወያይቶ መወሰን፤ የባንኩን መመስረቻ ጽሁፍ ማሻሻል፤ የጉባዔውን ቃለጉባዔ ማጽደቅ፣ የሚሉት ናቸው፡፡ ማሳሰቢያ በጉባዔው ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ስልጣን ባለው አካል የተሰጠ የውክልና ሰነድ ወይም በንግድ ህግ አንቀጽ 377 መሰረት ጉባዔው ከመካሄዱ ሦስት ቀን በፊት በባንኩ ዋና መ/ቤት አክሲዮን አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ በባንኩ የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ በመሙላትና በመፈረም ተወካይ መሾምና ተወካዩም የውክልና ማስረጃውን በመያዝ የጉባዔው ተካፋይ ለመሆንና ድምጽ ለመስጠት የሚችል መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡ ሆኖም አንድ ባለአክሲዮን በማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ በማንኛውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ሰው ብቻ መሆኑን እናሳስባለን፡፡ የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን የሚያሳይ የብሔራዊ መታወቂያ / ፋይዳ/ እና የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ዋናውንና ኮፒ በመያዝ በጉባዔው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የሆኑ የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈበት መታወቂያ /ቢጫ ካርድ/ ይዘው እንዲቀርቡ እናሳውቃለን፡፡ የድርጅትና የማህበር ተወካዮች ድርጅቱን/ማህበሩን ወክለው በስብሰባው እንዲገኙና ድምፅ እንዲሰጡ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዘው መቅረብ ያለባቸው መሆኑን በአክብሮት እናስታውቃለን፡፡ የሚወከሉ ባለአክሲዮኖች የሚቀበሉት የውክልና መጠን የራሳቸውን አክሲዮን ጨምሮ ከባንኩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ ከአስር በመቶ /10% / መብለጥ የለበትም፡፡ ባለአክሲዮኖች በስራ ላይ ያሉ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትና ሰራተኞች በባለአክሲዮኖች ጉባዔ ላይ እንዲሳተፉና ድምጽ እንዲሰጡ መወከል አይችሉም፡፡ የጉባዔው ቦታ ከሲኤምሲ ቤቶች በተቃራኒ ከፀሐይ ሪል ስቴት አጠገብ ወደወሰን መሄጃ በስተግራ በኩል የሚገኘው አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል መሆኑን ያስታውሱ፡፡ የቡና ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ Call Us 8501 የባለራዕዮች ባንክ! Bank of the visionaries!           www.bunnabanksc.com

የቡና ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 17ኛ መደበኛ እና 8ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔዎች ጥሪ Read More »

ለቡና ባንክ አ.ማ. ባለክሲዮኖች የቀረበ የአክሲዮን ሽያጭ ጥሪ ማስታወቂያ

ለቡና ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች የቀረበ የአክሲዮን ሽያጭ ጥሪ ማስታወቂያ ቡና ባንክ አ.ማ የኢትዮጵያ ካፒታል ገብያ ባለስልጣን ባፀደቀዉ ደንበኛ ሳቢ መግለጫ እና በተሰጠ ፍቃድ መሰረት ከነሀሴ 08 ቀን 2018 ዓ.ም  እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ 2,587,002 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሰማንያ ሰባት  ሺህ  ሁለት) መደበኛ አክሲዮኖችን በአንድ አክሲዮን ዋጋ ብር 120 (አንድ መቶ ሃያ ብር)  ሽያጭ የሚያከናዉን  መሆኑን በደስታ ይገልፃል፡፡ በቡና ባንክ ደንበኛ ሳቢ መግለጫ ላይ እንደተመለከተዉ ነባር ባለአክሲዮኞች ባላቸው አክሲዮኖች መጠን ልክ አዲስ አክሲዮኖችን እንዲገዙ የተደለደለ ሲሆን በነባር ባለአክሲዮኖች ያልተገዙ አክሲዮኖች በተመለከተ ለመግዛት ፍላጎታችሁን ለምትገልጹ ነባር ባለአክሲዮኖች የሚደለደል ይሆናል፡፡ በመሆኑም የተደለደለላችሁን አዲስ አክሲዮኖችም ይሁን በነባር ባለአክሲዮኖች ያልተገዙት አክሲዮኖች ለመግዛት ፍላጎት ያላችሁ ነባር ባለአክሲዮኖች አክሲዮኖችን ለመግዛት ትችሉ ዘንድ በኢትዮጲያ የካፒታል ገቢያ ባለስልጣን እዉቅና ከተሰጣቸው የሰነድ ሙዓለንዋይ አገበያዮች (ደላሎች) የግብይት ሂሳብ (Trading Account) በመክፈት የአክሲዮን ገዥዉን እንድትፈፅሙ ባንኩ ጥሪዉን ያቀርባል፡፡ ባለአክሲዮኖች አክሲዮኖችን ለመግዛት የሚከተሉትን አስፈላጊ ሰነዶች ይዘዉ ሊቀርቡ ይገባል ፡፡ የፋይዳ መታወቂያ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የኢሜይል አድራሻ በተወካይ አማካኝነት የሚፈፀም ከሆነ የውክልና ማስረጃ፡፡ ማሳሰብያ፡   በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የጸደቀው የደንበኛ ሳቢ መግለጫ እና ተያያዥ ሰነዶች በባንኩ ድህረ-ገጽ ላይ የሚገኝ ሲሆን ባለአክሲዮኖች ደንበኛ ሳቢ መግለጫዉን በሙሉ እንዲያነቡ ይበረታታሉ፤ ለዉሳኔ የተቸገሩ ከሆነ  በኢትዮጲያ የካፒታል ገቢያ ባለስልጣን ፍቃድ ከተሰጣቸዉ ገለልተኛ የኢንቨስትመንት አማካሪዎች ምክር ይጠይቁ፡፡ የደንበኛ ሳቢ መግለጫዉ መፅደቅ ሰነድሙዓለ ንዋዮችን ባለሃብቶች እንዲገዙ የተሰጠ ምክር ወይም ድጋፍ ተደርጎ አይወሰድም፡፡ ይህ ማስታወቂያ በኢትዮጵያ ካፒታል ገብያ ባለስልጣን ፍቃድ አግኝቷል፡፡ ለበለጠ መረጃ፡ ቡና ባንክ አክሲዮን ማህበር ዋና መስሪያ ቤት ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አፍሪካ ጎዳና በአካል ቀርቦ ማናገር ወይም በስልክ ቁጥር +25111580880 ሞባይል +251911006396/+251931795160/+251910636306 ቡና ባንክ የባለራዕዮች ባንክ!

ለቡና ባንክ አ.ማ. ባለክሲዮኖች የቀረበ የአክሲዮን ሽያጭ ጥሪ ማስታወቂያ Read More »

This will close in 0 seconds

Open Your Bank Account Today!

አካውንት ይክፈቱ የክፍያ ካርድዎን ያዝዙ ፣ ፈጣን አገልግሎት ማግኘት ይጀምሩ! ዛሬውኑ ይቀላቀሉን!

Open Bunna Account

You cannot copy content of this page