Bunna Bank

Uncategorized

የተከበራችሁ ውድ ደንበኞቻችን፣

ቡና ባንክ ዓመታዊ የሒሳብ መዝጊያ ሥራዎችን ለመሥራት እና የቀጣዩን የበጀት ዓመት ስራ ለማስጀመር ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ብቻ በሁሉም ቅርንጫፎችቻችን ላይ በጊዜያዊነት ተግባራዊ የሚሆን የሥራ ሰዓት ማሻሻያ አድርጓል። በመሆኑም፤ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ሁሉም ቅርንጫፎች እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ለደንበኞች አገልግሎት ክፍት ሆነው ይቆያሉ። የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቶች (አቦል ሞባይል ባንኪንግ፣ አቦል ዲጂታል ብድር አገልግሎት ፣ የኤቲኤም አገልግሎት፣ ፖስ አገልግሎት፣ ኢንተርኔት ባንኪንግ) አይቋረጡም፡፡ ውድ ደንበኛችን! ሁሉም የባንካችን አገልግሎቶች ረቡዕ ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ መደበኛ ሥራቸውን እንደሚቀጥሉ በአክብሮት እንገልጻልን። ቡና ባንክ የባለራዕዮች ባንክ!

የተከበራችሁ ውድ ደንበኞቻችን፣ Read More »

ቡና ባንክ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን (ECMA) የሰነደ ሙአለነዋይ ምዝገባውን በተሳካ ሁኔታ አጠናቀቀ

(አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17 ቀን፣ 2018 ዓ.ም.) ቡና ባንክ አ.ማ. የሰነደ ሙአለነዋይ ምዝገባን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን (ECMA) ፈቃድ ማግኘቱን በደስታ ይገልጻል። ይፋዊ ምዝገባው ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ይህም ስኬታማ ምዝገባ በባንኩ የኮርፖሬት እድገት እና እየተስፋፋ ባለው የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ውስጥ ትልቅ ታሪካዊ ምዕራፍ ነው። በዚህ ኦፊሴላዊ ምዝገባ መሰረት የቡና ባንክ አ.ማ. 61,895,598 ነባር መደበኛ አክሲዮኖች፣ እንዲሁም ለነባር ባለአክሲዮኖች የሚቀርቡ 2,587,002 አዳዲስ መደበኛ አክሲዮኖች በባለስልጣኑ ጸድቀዋል፡፡ ይህ ስኬት ቡና ባንክ በኢትዮጵያ የሰነደ ሙአለነዋይ ገበያ (ESX) ውስጥ በቀጣይ ለመሳተፍ ላስቀመጠው እቅድ ወሳኝ እርምጃ ነው። ባንኩ ለግልጽነት፣ ለጠንካራ የኮርፖሬት ገቨርናንስ እና ለባለአክሲዮኖቹ ዘላቂ እሴት ለመፍጠር ያለውን ጠንካራ ቁርጠኝነት ያጎላ ተግባር ነው። የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሙሉጌታ ዓለማየሁ በሰጡት መግለጫ”የሰነደ ሙአለነዋያችንን በካፒታል ገበያ ባለስልጣን (ECMA) በተሳካ ሁኔታ ማስመዝገባችን ለቡና ባንክ የሚያኮራ ታሪካዊ ምዕራፍ ነው። ይህ ስኬታማ ክንውን የባንካችንን የወደፊት ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ የሚያንጸባርቅ፣ የገቨርናንስ ደረጃችንን የሚያሳድግ እና የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ እያደገ ሲመጣ ለባለአክሲዮኖቻችን አዳዲስ እድሎችን የሚከፍት ነው። በዚህ ረገድ ባለአክሲዮኖቻችን እና ባለድርሻ አካላት ላሳዩን ቀጣይነት ያለው እምነት እና ድጋፍ ጥልቅ ምስጋናችንን እናቀርባለን።” ባንኩ እንዳስታወቀው ከዚህ የአክሲዮን ጉዳይ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ መረጃዎችና ማብራሪያዎች በሂደት በይፋ የሚገለጹ ይሆናል። በዚህ አጋጣሚ ቡና ባንክ ለኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን፣ ለክቡራን ባለአክሲዮኖቹ፣ ለደንበኞቹ እና ለሁሉም አጋሮቹ ላደረጉት የማያቋርጥ ድጋፍ የከበረ ምስጋናውን ያቀርባል። ይፋዊ የአክሲየን ማህበሩን መግለጫ ሰነድ (Prospectus) ከዚህ በታች የሚገኘው ማስፈንጠሪያ በመጫን አውርደው ማንበብ ይችላሉ፡፡ 📄 መግለጫውን ያውርዱ (PDF) ለተጨማሪ መረጃ፣ እባክዎ ያነጋግሩን፦ ስልክ፦ 8501 Bunna Bank Successfully Completes Securities Registration with the Ethiopian Capital Market Authority (ECMA) (Addis Ababa, June 24, 2026) Bunna Bank S.C. is delighted to announce that it has received approval from the Ethiopian Capital Market Authority (ECMA) to register its securities. The formal registration was completed on June 23, 2026, marking a significant milestone in the Bank’s corporate development and Ethiopia’s evolving capital market. Under this registration, 61,895,598 existing ordinary shares, and the issuance of up to 2,587,002 new ordinary shares to be offered to existing shareholders, have been approved. This achievement represents an important step toward Bunna Bank’s planned participation in the Ethiopian Securities Exchange (ESX). It underscores the Bank’s strong commitment to transparency, robust corporate governance, and the creation of long-term value for its shareholders. Chief Executive Officer of Bunna Bank S.C., Ato Mulugeta Alemayehu, in his statement, stated: “The successful registration of our securities with the ECMA is a proud milestone for Bunna Bank. It reflects our forward-looking strategy, enhances our governance standards, and opens new opportunities for our shareholders as Ethiopia’s capital market matures. We remain deeply grateful to our shareholders and stakeholders for their continued trust and support.” Download the Prospectus using the link below: 📄 Download the Prospectus (PDF) Further information regarding the share management and related issues will be communicated officially in due course. At this juncture in time, Bunna Bank would like to express its sincere appreciation to the Ethiopian Capital Market Authority, its valued shareholders, customers, and all partners for their unwavering support. For more information, please contact: Telephone: 8501

ቡና ባንክ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን (ECMA) የሰነደ ሙአለነዋይ ምዝገባውን በተሳካ ሁኔታ አጠናቀቀ Read More »

የጥንቃቄ መልዕክት⚠️⚠️

ዉድ ደንበኞቻችን በማኅበራዊ ሚዲያ በዋትስአፕ ፣ ቴሌግራም፣ ፌስቡክ፣ በአጭር ፅሁፍ መልዕክት ወይም ካልታወቁ አካላት የስልክ ጥሪዎች በኩል የሚመጡ የገንዘብ ማስተላለፍ ጥያቄዎችን አይቀበሉ፡፡ደንበኞች ማንኛውንም የገንዘብ ዝውውር ከመፈጸማቸው በፊት፣ ጥያቄውን የላከውን አካል ትክክለኛ ማንነት በቀጥታ በድምፅ ግንኙነት ወይም ላኪ ተብሎ በሚታሰበው አካል ይፋዊ የግንኙነት መስመሮች በኩል ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል። ማንኛዉም የማጭበርበር ሙከራ ካጋጠምዎ በአቅራቢያዎት ወደሚገኝ የቡና ባንክ ቅርንጫፍ ይሒዱ ወይም ወደ ጥሪ ማዕከላችን 8501 ይደዉሉ፡፡ ቡና ባንክ- የባለራዕዮች ባንክ #BunnaBank #SecurityAlert #StaySafeOnline #DigitalSecurity #CyberSecurity #OnlineSafety #ProtectYourAccount #SecureBanking #BankingSecurity #FraudAlert #ScamAlert

የጥንቃቄ መልዕክት⚠️⚠️ Read More »

ቡና ባንክ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሳለጥ የሚያስችል ለደንበኞች ምቹ የሆነ የዲጂታል ኦንቦርዲንግ ስርዓት ይፋ አደረገ፡፡

ቡና ባንክ በርካታ የባንክ አገልግሎቶችን በዲጂታል መንገድ ለማከናወን የሚያስችለውን የዲጂታል ደንበኞች ምዝገባ ስርዓት (Digital Customer Onboarding System) ዛሬ በይፋ ወደ ስራ ማስገባቱን አስታውቋል።  ይህ በድረ-ገጽ (Web-based) ላይ የተመሰረተ የአሰራር ስርዓት ደንበኞች በአካል ወደ ቅርንጫፍ መሄድ ሳያስፈልጋቸው ጊዜያቸውንና ጉልበታቸውን ቆጥበው ባሉበት ሆነው የባንክ ሂሳብ እንዲከፍቱ እና የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ የሚያስችል ነው። ይህ ዘመናዊ ትግበራ የባንኩ የ “Vision 2030” ስትራቴጂክ እቅድ አካል ሲሆን፣ ባንኩን በቅርንጫፍ ላይ ከተመሰረተ አሰራር ወደ ተማከለ እና ዲጂታል-መር የፕላትፎርም (Platform) ስርዓት ለማሸጋገር የሚረዳ ጭምር ነው። ዋና ዋና ቴክኒካዊ ፋይዳዎች፡ የርቀት ምዝገባ (Remote Onboarding) ፡ ደንበኞች ደህንነቱ በተጠበቀ የድረ-ገጽ መተግበሪያ (https://onboardingportal.bunnabanksc.com/ ) አማካኝነት ሙሉ የባንክ ሂሳብ የመክፈት ሂደትን ከጅምሩ እስከመጨረሻው (End to End) ማከናወን ይችላሉ። የአገልግሎት አውቶሜሽን (Service Automation) ፡ ከሂሳብ መክፈት ባሻገር የዚህ አገልግሎት ትልቁ ፋይዳ ተጠቃሚዎች የኤቲኤም ካርድ ለማዘዝ፣ የሞባይል ባንኪንግ ለማስጀመር እና ከባንኩ ባለሙያዎች ጋር ቀጠሮ ለመያዝ በዲጂታል መንገድ ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ። አቅጣጫ ጠቋሚ (Geolocation Tools) ፡ ቅርንጫፎችን፣ ኤቲኤምና (ATM) አይቲኤሞችን (ITM)እንዲሁም የባንኩ የክፍያ አማራጭ ያለባቸውን የንግድ ቦታዎች ለማግኘት የሚያስችል የካርታ (Map) ትስስርን ያካተተ ነው። የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ትስስር (Fayda ID Integration) ፡ ከብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ስርዓት ጋር በቅጽበት በመገናኘት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎችን (NBE directives) በጠበቀ መልኩ የደንበኞችን ማንነት ማረጋገጥ (KYC) ያስችላል። የቡና ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙሉጌታ ዓለማየሁ በጉዳዩ ላይ እንደገለጹት፤ የቡና ባንክ  ዲጂታል ስትራቴጂ ከአገር-አቀፉ የዲጂታል ኢኮኖሚ ጋር የተናበበ መሆኑን ተናግረው በዚህ የዲጂታል ኦንቦርዲንግ አገልግሎት የባንክ አገልግሎትን ለማግኘት እንቅፋት የሆኑትን ጂኦግራፊያዊ እና ሎጂስቲካዊ ገደቦችን ማስቀረት መቻሉን ተናግረዋል። “ይህ አማራጭ የአሰራር መጓተትን በከፍተኛ ደረጃ ከመቀነሱም በላይ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘውን ሀገራዊ የፋይናንስ አካታችነት (Financial Inclusion) ግብ የሚደግፍና እንደ ፋይዳ ካሉ ሀገራዊ የዲጂታል መሰረተ ልማቶች ጋር ለማስተሳሰር፣ የደንበኞችን ማንነት በቅጽበት ማረጋገጥ እና መመዝገብ የሚያስችልም ጭምር ነው” ብለዋል፡፡ የአገልግሎት ስርዓቱ ለህዝብ ክፍት ከመደረጉ በፊት የቅርንጫፍ ሰራተኞች የተሟላ ስልጠና የወሰዱ ሲሆን፣ የመረጃ ታማኝነትን እና ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ጠንካራ የሳይበር ደህንነት (Cybersecurity) ማዕቀፍ ተዘርግቷል። ስርዓቱ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የደንበኞች ፍሰት ለማስተናገድ እና ጥብቅ የሆነ የመረጃ ግላዊነት ስታንዳርዶችን ለመጠበቅ በሚያስችል መንገድ ታስቦ የተነደፈ ነው። ይህ የዲጂታል ደንበኞች ምዝገባ ስርዓት ከሰኞ ሚያዝያ 26፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለህዝብ ክፍት ሆኖ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። # # # ስለ ቡና ባንክ፡- በ2001 ዓ.ም የተመሰረተው ቡና ባንክ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ግንባር ቀደም የግል የንግድ ባንኮች አንዱ ነው። ባንኩ 449 ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን፣ አሁን ላይ የ “Vision 2030” ስትራቴጂውን በመተግበር በዲጂታል ፈጠራ እና በእሴት ፍሰት (Value Stream) ላይ በተመሰረተ አሰራር በዘርፉ ቀዳሚ የፋይናንስ ተቋም ለመሆን እየሰራ ይገኛል። ለተጨማሪ መረጃ፡- ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽንስ ዳይሬክቶሬት ቡና ባንክ- የባለራዕዮች ባንክ ስልክ ቁጥር፡-251911403884

ቡና ባንክ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሳለጥ የሚያስችል ለደንበኞች ምቹ የሆነ የዲጂታል ኦንቦርዲንግ ስርዓት ይፋ አደረገ፡፡ Read More »

ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለፀሎተ ሀሙስ በሰላም አደረሳችሁ፡፡

ለበዓል ከዉጪ ሀገር የተላከሎትን ገንዘብ በባንካችን ይመንዝሩ፤ ጠቀም ያለ ጉርሻ ያግኙ!! ቡና ባንክ- የባለራዕዮች ባንክ BunnaBank #Chrstianity #Orthodox #Holiday #Foryou #Forex #Bonus

ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለፀሎተ ሀሙስ በሰላም አደረሳችሁ፡፡ Read More »

እየመጣን ነው 🚀

የላቀ የዲጂታል ተሞክሮን ከቀልጣፋ አገልግሎት ጋር አጣምረን ይዘንልዎ እየመጣን ነው። በጣትዎ ጫፍ የሚዘወር፣ የባንክ አገልግሎትን መልክ የሚቀይር፤ አዲስ ብስራት፣ ልዩ ነገር… ይዘን ከች ልንል ከደጃፍዎ ደርሰናል! ዝግጁ ነዎት? በቅርብ ቀን ይጠብቁን! ቡና ባንክ- የባለራዕዮች ባንክ #Bunnabank #ComingSoon #StayTuned #SomethingNew #BigUpdate  #SmartBanking #DigitalBanking

እየመጣን ነው 🚀 Read More »

This will close in 0 seconds

Open Your Bank Account Today!

አካውንት ይክፈቱ የክፍያ ካርድዎን ያዝዙ ፣ ፈጣን አገልግሎት ማግኘት ይጀምሩ! ዛሬውኑ ይቀላቀሉን!

Open Bunna Account

You cannot copy content of this page