Bunna Bank

Samuel Aynalem

ቡና ባንክ እና የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት (ATI) የግብርና ፋይናንስ ዘርፉን ለማሳደግ የሚያስችል ስትራቴጂካዊ የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ

በሀገራችን የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመንና የፋይናንስ ተደራሽነትን ለማስፋፋት በማለም፤ ቡና ባንክ እና የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት (ATI) ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. (July 15, 2026) የአጋርነት ስምምነት ሰነድ (MoU) ተፈራርመዋል። ይህ ስምምነት በኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽንን፣ የህብረት ሥራ ማህበራትን ልማት እና ሁሉን አቀፍ የግብርና ፋይናንስን ለመደገፍ የሚያስችል የተቀናጀ ስትራቴጂካዊ ማዕቀፍ ይፈጥራል ተብሎ ታምኖበታል። ይህ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶችን ከግብርና ሥራዎች ጋር በማቀናጀት በገጠሩ የሀገሪቱ ክፍሎች ያለውን የፋይናንስ ክፍተት በዋነኝነት ለመሙላት ያለመ ነው። ስምምነቱ በአምስት ዋና ዋና ምሰሶዎች ላይ የተዋቀረ ሲሆን፤ እነሱም የግብርና እና የህብረት ሥራ ማህበራት ልማት፣ የግብርና ስራ ፈጠራ (Agri-Entrepreneurship)፣ የእሴት ሰንሰለት ፋይናንስ፣ ዲጂታል ግብርና እና ተቋማዊ የባንክ አገልግሎቶችን ያጠቃልላል። በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የቡና ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሙሉጌታ ዓለማየሁ ስምምነቱ ከባንኩ ዘላቂ ግብ ጋር ያለውን ፍፁም መጣጣም ሲያብራሩ፡-“በእሴት ላይ የተመሰረተ አጋርነት እና ዘላቂ እድገትን ማረጋገጥ ከባንካችን ስትራቴጂካዊ ምሰሶዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው። በመሆኑም ይህ አጋርነት ዘላቂ እድገት እና ማህበረሰባዊ ተፅዕኖ ለመፍጠር ሰፊ ዕድል ያለውን የህብረተሰብ ክፍል ለመድረስ ስትራቴጂካዊ ባህሪ ያለው ስምምነት ነው”* ብለዋል። ይህ ለማህበረሰቡ ዕድገት በአጋርነት የመቆም ቁርጠኝነት በተግባር በመተርጎም ረገድ፣ ስምምነቱ አማራጭ የባንክ አገልግሎቶችን እና ልዩ የዲጂታል ብድር ምርቶችን ተደራሽ የማድረግ ኃላፊነትን አስቀምጧል። በዚህም ባንኩ እንደ “አቦል ዲጂታል ፋይናንሻል ሰርቪስ” (Abol DFS) ያሉ የራሱን የቴክኖሎጂ መድረኮች በመጠቀም፤ በክላስተር ለተደራጁ አርሶ አደሮች፣ ለግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ሰጪዎች እንዲሁም ለወጣቶችና ሴት ስራ ፈጣሪዎች ተስማሚ የሆኑ የፋይናንስ መፍትሄዎችን ያቀርባል። የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት (ATI) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ማንደፍሮ ንጉሴ በበኩላቸው፤ ይህ ትብብር አዳዲስ ግብርና-ነክ ስራ ፈጣሪዎች በተለይም የብድር ዋስትና (ኮላተራል) ማቅረብ የማይችሉ ወጣቶች የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ያለውን ሚና ሲጠቅሱ፡-“ይህ ስምምነት ብድር ለመውሰድ ዋስትና ማቅረብ ለማይችሉ እና የገንዘብ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው በርካታ ወጣት አርሶ አደሮች በኩል ያለውን የፋይናንስ ክፍተት፣ ሊፈጠር ከሚችለው የብድር ስጋት ጋር በማመጣጠን ለመሙላት ትልቅ ዕድል የሚፈጥር ነው፤ ይህም በአንጻሩ ለባንኩም ሆነ ለሀገሪቱ ትልቅ አስተዋፅዖ ይኖረዋል” ብለዋል። ያለዋስትና ከሚሰጥ ብድር ጋር ተያይዞ የሚመጣውን ስጋት ለመቀነስ እንዲረዳ፣ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት (ATI) ወሳኝ የሆኑ የግብርና መረጃዎችን፣ የንግድ እቅድ ድጋፎችን እና የራሱን የተደራጀ የአርሶ አደሮች መረጃ ቋት (Farmer Profiling System) ከባንኩ ጋር ያገናኛል። ይህ የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት ቡና ባንክ በሰው ሰራሽ ኢንተለጀንስ (AI) ላይ የተመሰረቱ የብድር መመዘኛ መተግበሪያዎችን እና የጋራ ዋስትና (co-guarantee) የፋይናንስ ሞዴሎችን በመጠቀም ከዚህ ቀደም የባንክ አገልግሎት ባልደረሰባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ዘንድ ፈጣንና ቀልጣፋ የብድር አቅርቦት እንዲኖር ያስችላል። ይህ ስምምነት ከተጠቀሰው አብይ የትብብር ማዕቀፍ ባሻገር በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር ሲሆን፤ በዚህም ቡና ባንክ ለኢንስቲትዩቱ እና ለሰራተኞቹ አጠቃላይ የባንክ አገልግሎቶችን ማቅረብን ያካትታል። የመግባቢያ ሰነዱ ዛሬ በይፋ መፈረሙን ተከትሎ፤ ሁለቱም ተቋማት የተነደፉትን ስትራቴጂካዊ ምሰሶዎች ወደ ተግባር ለመለወጥና በኢትዮጵያ የግብርና ምህዳር ውስጥ ዘላቂ የኢኮኖሚ አቅምን ለመገንባት የበኩላቸውን ለማበርከት በጋራ መስራት ይጀምራሉ።   Bunna Bank and Ethiopian Agricultural Transformation Institute Forge Strategic Partnership to Drive Agri-Finance and Sector Transformation ADDIS ABABA — In a major step toward expanding financial inclusion and accelerating Ethiopia’s agricultural sector, Bunna Bank and the Ethiopian Agricultural Transformation Institute (ATI), on July 15, 2026, signed a landmark Memorandum of Understanding (MoU). The agreement establishes a comprehensive and unified framework to support agricultural transformation, cooperative development, and inclusive agri-finance across the nation. The strategic partnership directly targets critical gaps in rural finance by integrating digital banking solutions with agricultural operations. Structured around five core pillars, the collaboration encompasses agriculture and cooperative sector transformation, agri-entrepreneurship, value chain financing, digital agriculture, and institutional banking services. During the signing ceremony, CEO of Bunna Bank, Ato Mulugeta Alemayehu emphasized how the agreement aligns perfectly with the bank’s overarching objectives. “Value-based partnership and sustainable growth are among our bank’s strategic pillars,” he stated. “Therefore, this partnership is strategic in its nature to reach out to the masses where there is an opportunity for sustainable growth and community impact.” This commitment to community impact is practically operationalized through the MoU’s mandate to deploy alternative banking channels and specialized digital loan products. [7/16/2026 8:31 AM] Sami AD: By utilizing platforms such as Bunna Bank’s Abol DFS, the bank will deliver tailored financial solutions to cluster-based farmer productions, mechanization service providers, and youth and women-owned enterprises. Dr. Mandefro Nigussie, Director General of the ATI, highlighted the economic vitalization this collaboration will bring to emerging agricultural entrepreneurs, particularly in navigating traditional borrowing hurdles. “It is a big opportunity to fill the finance gap for many youth farmers who are in need of financing, balancing with the risk of uncollateralized credit, thereby contributing for the bank and the country too,” Dr. Mandefro remarked. To actively mitigate the risks associated with uncollateralized lending, the ATI will supply crucial agronomic data, business planning support, and integration with its granular Farmer Profiling System. This data-sharing framework will empower Bunna Bank to utilize AI-based credit scoring tools and co-guarantee financing models, ensuring accurate and efficient loan approvals for underserved client segments. Beyond this, the agreement also strengthens the institutional relationship between the two entities, with Bunna Bank set to provide comprehensive banking services and dedicated relationship management for the ATI and its staff. With the official execution of the MoU today, both institutions will immediately move to operationalize the strategic pillars through jointly developed implementation frameworks, setting the stage for sustainable economic empowerment within Ethiopia’s agricultural landscape.

ቡና ባንክ እና የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት (ATI) የግብርና ፋይናንስ ዘርፉን ለማሳደግ የሚያስችል ስትራቴጂካዊ የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ Read More »

የተከበራችሁ ውድ ደንበኞቻችን፣

ቡና ባንክ ዓመታዊ የሒሳብ መዝጊያ ሥራዎችን ለመሥራት እና የቀጣዩን የበጀት ዓመት ስራ ለማስጀመር ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ብቻ በሁሉም ቅርንጫፎችቻችን ላይ በጊዜያዊነት ተግባራዊ የሚሆን የሥራ ሰዓት ማሻሻያ አድርጓል። በመሆኑም፤ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ሁሉም ቅርንጫፎች እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ለደንበኞች አገልግሎት ክፍት ሆነው ይቆያሉ። የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቶች (አቦል ሞባይል ባንኪንግ፣ አቦል ዲጂታል ብድር አገልግሎት ፣ የኤቲኤም አገልግሎት፣ ፖስ አገልግሎት፣ ኢንተርኔት ባንኪንግ) አይቋረጡም፡፡ ውድ ደንበኛችን! ሁሉም የባንካችን አገልግሎቶች ረቡዕ ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ መደበኛ ሥራቸውን እንደሚቀጥሉ በአክብሮት እንገልጻልን። ቡና ባንክ የባለራዕዮች ባንክ!

የተከበራችሁ ውድ ደንበኞቻችን፣ Read More »

የጥንቃቄ መልዕክት⚠️⚠️

ዉድ ደንበኞቻችን በማኅበራዊ ሚዲያ በዋትስአፕ ፣ ቴሌግራም፣ ፌስቡክ፣ በአጭር ፅሁፍ መልዕክት ወይም ካልታወቁ አካላት የስልክ ጥሪዎች በኩል የሚመጡ የገንዘብ ማስተላለፍ ጥያቄዎችን አይቀበሉ፡፡ደንበኞች ማንኛውንም የገንዘብ ዝውውር ከመፈጸማቸው በፊት፣ ጥያቄውን የላከውን አካል ትክክለኛ ማንነት በቀጥታ በድምፅ ግንኙነት ወይም ላኪ ተብሎ በሚታሰበው አካል ይፋዊ የግንኙነት መስመሮች በኩል ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል። ማንኛዉም የማጭበርበር ሙከራ ካጋጠምዎ በአቅራቢያዎት ወደሚገኝ የቡና ባንክ ቅርንጫፍ ይሒዱ ወይም ወደ ጥሪ ማዕከላችን 8501 ይደዉሉ፡፡ ቡና ባንክ- የባለራዕዮች ባንክ #BunnaBank #SecurityAlert #StaySafeOnline #DigitalSecurity #CyberSecurity #OnlineSafety #ProtectYourAccount #SecureBanking #BankingSecurity #FraudAlert #ScamAlert

የጥንቃቄ መልዕክት⚠️⚠️ Read More »

ቡና ባንክ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሳለጥ የሚያስችል ለደንበኞች ምቹ የሆነ የዲጂታል ኦንቦርዲንግ ስርዓት ይፋ አደረገ፡፡

ቡና ባንክ በርካታ የባንክ አገልግሎቶችን በዲጂታል መንገድ ለማከናወን የሚያስችለውን የዲጂታል ደንበኞች ምዝገባ ስርዓት (Digital Customer Onboarding System) ዛሬ በይፋ ወደ ስራ ማስገባቱን አስታውቋል።  ይህ በድረ-ገጽ (Web-based) ላይ የተመሰረተ የአሰራር ስርዓት ደንበኞች በአካል ወደ ቅርንጫፍ መሄድ ሳያስፈልጋቸው ጊዜያቸውንና ጉልበታቸውን ቆጥበው ባሉበት ሆነው የባንክ ሂሳብ እንዲከፍቱ እና የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ የሚያስችል ነው። ይህ ዘመናዊ ትግበራ የባንኩ የ “Vision 2030” ስትራቴጂክ እቅድ አካል ሲሆን፣ ባንኩን በቅርንጫፍ ላይ ከተመሰረተ አሰራር ወደ ተማከለ እና ዲጂታል-መር የፕላትፎርም (Platform) ስርዓት ለማሸጋገር የሚረዳ ጭምር ነው። ዋና ዋና ቴክኒካዊ ፋይዳዎች፡ የርቀት ምዝገባ (Remote Onboarding) ፡ ደንበኞች ደህንነቱ በተጠበቀ የድረ-ገጽ መተግበሪያ (https://onboardingportal.bunnabanksc.com/ ) አማካኝነት ሙሉ የባንክ ሂሳብ የመክፈት ሂደትን ከጅምሩ እስከመጨረሻው (End to End) ማከናወን ይችላሉ። የአገልግሎት አውቶሜሽን (Service Automation) ፡ ከሂሳብ መክፈት ባሻገር የዚህ አገልግሎት ትልቁ ፋይዳ ተጠቃሚዎች የኤቲኤም ካርድ ለማዘዝ፣ የሞባይል ባንኪንግ ለማስጀመር እና ከባንኩ ባለሙያዎች ጋር ቀጠሮ ለመያዝ በዲጂታል መንገድ ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ። አቅጣጫ ጠቋሚ (Geolocation Tools) ፡ ቅርንጫፎችን፣ ኤቲኤምና (ATM) አይቲኤሞችን (ITM)እንዲሁም የባንኩ የክፍያ አማራጭ ያለባቸውን የንግድ ቦታዎች ለማግኘት የሚያስችል የካርታ (Map) ትስስርን ያካተተ ነው። የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ትስስር (Fayda ID Integration) ፡ ከብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ስርዓት ጋር በቅጽበት በመገናኘት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎችን (NBE directives) በጠበቀ መልኩ የደንበኞችን ማንነት ማረጋገጥ (KYC) ያስችላል። የቡና ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙሉጌታ ዓለማየሁ በጉዳዩ ላይ እንደገለጹት፤ የቡና ባንክ  ዲጂታል ስትራቴጂ ከአገር-አቀፉ የዲጂታል ኢኮኖሚ ጋር የተናበበ መሆኑን ተናግረው በዚህ የዲጂታል ኦንቦርዲንግ አገልግሎት የባንክ አገልግሎትን ለማግኘት እንቅፋት የሆኑትን ጂኦግራፊያዊ እና ሎጂስቲካዊ ገደቦችን ማስቀረት መቻሉን ተናግረዋል። “ይህ አማራጭ የአሰራር መጓተትን በከፍተኛ ደረጃ ከመቀነሱም በላይ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘውን ሀገራዊ የፋይናንስ አካታችነት (Financial Inclusion) ግብ የሚደግፍና እንደ ፋይዳ ካሉ ሀገራዊ የዲጂታል መሰረተ ልማቶች ጋር ለማስተሳሰር፣ የደንበኞችን ማንነት በቅጽበት ማረጋገጥ እና መመዝገብ የሚያስችልም ጭምር ነው” ብለዋል፡፡ የአገልግሎት ስርዓቱ ለህዝብ ክፍት ከመደረጉ በፊት የቅርንጫፍ ሰራተኞች የተሟላ ስልጠና የወሰዱ ሲሆን፣ የመረጃ ታማኝነትን እና ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ጠንካራ የሳይበር ደህንነት (Cybersecurity) ማዕቀፍ ተዘርግቷል። ስርዓቱ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የደንበኞች ፍሰት ለማስተናገድ እና ጥብቅ የሆነ የመረጃ ግላዊነት ስታንዳርዶችን ለመጠበቅ በሚያስችል መንገድ ታስቦ የተነደፈ ነው። ይህ የዲጂታል ደንበኞች ምዝገባ ስርዓት ከሰኞ ሚያዝያ 26፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለህዝብ ክፍት ሆኖ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። # # # ስለ ቡና ባንክ፡- በ2001 ዓ.ም የተመሰረተው ቡና ባንክ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ግንባር ቀደም የግል የንግድ ባንኮች አንዱ ነው። ባንኩ 449 ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን፣ አሁን ላይ የ “Vision 2030” ስትራቴጂውን በመተግበር በዲጂታል ፈጠራ እና በእሴት ፍሰት (Value Stream) ላይ በተመሰረተ አሰራር በዘርፉ ቀዳሚ የፋይናንስ ተቋም ለመሆን እየሰራ ይገኛል። ለተጨማሪ መረጃ፡- ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽንስ ዳይሬክቶሬት ቡና ባንክ- የባለራዕዮች ባንክ ስልክ ቁጥር፡-251911403884

ቡና ባንክ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሳለጥ የሚያስችል ለደንበኞች ምቹ የሆነ የዲጂታል ኦንቦርዲንግ ስርዓት ይፋ አደረገ፡፡ Read More »

This will close in 0 seconds

Open Your Bank Account Today!

አካውንት ይክፈቱ የክፍያ ካርድዎን ያዝዙ ፣ ፈጣን አገልግሎት ማግኘት ይጀምሩ! ዛሬውኑ ይቀላቀሉን!

Open Bunna Account

You cannot copy content of this page