Bunna Bank

በአዲሱ ዓመት ለደንበኞቻችን አዳዲስ እሴቶችን በመፍጠር መጪውን ጊዜ በጋራ እንገነባለን – ቡና ባንክ!

ክቡራን የባንካችን ደንበኞች፣

የተከበራችሁ ባለአክሲዮኖች፣

ባለድርሻ አካላት እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፤

በቅድሚያ፣ እንኳን ለአዲሱ የ2019 ዓ.ም ዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። “የባለራዕዮች ባንክ” በሆነው ባንካችን በየዕለቱ ታላላቅ አላማዎችን ለማሳካት ስንጓዝ፣ በባንካችን ላይ ላላችሁ ጽኑ እምነት እና በተግባር ላሳያችሁን ታማኝ አጋርነት በዚህ አጋጣሚ ከልብ እናመሰግናለን።

የእድገት ጉዟችን እውነተኛ ማዕከል ሁልጊዜም ደንበኞቻችን እና ባለአክሲዮኖቻችን ናቸው። ባንካችንን ይበልጥ ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ እና ለነገው የፋይናንስ ገበያ ጠንካራ ውድድር ዝግጁና ለደንበኞቻችን ምቹ ለማድረግ በርካታ የለውጥ እርምጃዎችን ወስደናል፦

የዲጂታል ባንኪንግና የብድር አገልግሎቶቻችንን በማስፋፋት ደንበኞቻችን እንከን የለሽ፣ ፈጣን እና የላቀ የባንክ አገልግሎት እንዲያገኙ አድርገናል። በአዲሱ ዓመትም ይህ ተነሳሽነት ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተግተን እንሰራለን።

የባንካችን ቀጣይነት ያለው ስኬት የሚመነጨው ከባለአክሲዮኖቻችን የማያቋርጥ ድጋፍ መሆኑ እሙን ነው። በአዲሱ ዓመትም የባለአክሲዮኖቻችንን እሴት ከፍ የሚያደርጉ ውጤታማ ስራዎችን ለመስራት ተዘጋጅተናል።

በሀገራችን አዲስ የተጀመረውን የሰነደ-መዋዕለ-ነዋይ ገበያን ጨምሮ ሌሎች የባንካችንን ዋና ቢዝነስ የሚደግፉ የገበያ ዕድሎችን በብቃት አሟጦ በመጠቀም፣ ጠንካራ የሪስክ አስተዳደር በመዘርጋትና የውስጥ አቅምን አሟጦ በመጠቀም የጋራ እድገታችንን እናረጋግጣለን።

የቡና ባንክ እውነተኛ ስኬት የሚለካው ከናንተ – ከውድ ደንበኞቻችን እና ባለአክሲዮኖች – ጋር ባለው የጠበቀ ውጤታማ ግንኙነት ነው። በመሆኑም በ2019 ዓ.ም በአላማና በአንድነት በመቆም፣ አዳዲስ እሴቶችን በጋራ በመፍጠር እና የአገልግሎት ጥራታችንን ከፍ በማድረግ መጪውን ጊዜ በአንድነት እንገነባለን።

አዲሱ ዓመት ለደንበኞቻችን፣ ለባለአክሲዮኖች እና ለሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ የሰላም፣ የደስታ እና የጋራ ብልጽግና እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ።

 

መልካም አዲስ ዓመት!

ሙሉጌታ አለማየሁ

ዋና ሥራ አስፈፃሚ፣

ቡና ባንክ – የባለራዕዮች ባንክ!

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This will close in 0 seconds

Open Your Bank Account Today!

አካውንት ይክፈቱ የክፍያ ካርድዎን ያዝዙ ፣ ፈጣን አገልግሎት ማግኘት ይጀምሩ! ዛሬውኑ ይቀላቀሉን!

Open Bunna Account

You cannot copy content of this page