Bunna Bank

Uncategorized

ቡና ባንክ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሳለጥ የሚያስችል ለደንበኞች ምቹ የሆነ የዲጂታል ኦንቦርዲንግ ስርዓት ይፋ አደረገ፡፡

ቡና ባንክ በርካታ የባንክ አገልግሎቶችን በዲጂታል መንገድ ለማከናወን የሚያስችለውን የዲጂታል ደንበኞች ምዝገባ ስርዓት (Digital Customer Onboarding System) ዛሬ በይፋ ወደ ስራ ማስገባቱን አስታውቋል።  ይህ በድረ-ገጽ (Web-based) ላይ የተመሰረተ የአሰራር ስርዓት ደንበኞች በአካል ወደ ቅርንጫፍ መሄድ ሳያስፈልጋቸው ጊዜያቸውንና ጉልበታቸውን ቆጥበው ባሉበት ሆነው የባንክ ሂሳብ እንዲከፍቱ እና የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ የሚያስችል ነው። ይህ ዘመናዊ ትግበራ የባንኩ የ “Vision 2030” ስትራቴጂክ እቅድ አካል ሲሆን፣ ባንኩን በቅርንጫፍ ላይ ከተመሰረተ አሰራር ወደ ተማከለ እና ዲጂታል-መር የፕላትፎርም (Platform) ስርዓት ለማሸጋገር የሚረዳ ጭምር ነው። ዋና ዋና ቴክኒካዊ ፋይዳዎች፡ የርቀት ምዝገባ (Remote Onboarding) ፡ ደንበኞች ደህንነቱ በተጠበቀ የድረ-ገጽ መተግበሪያ (https://onboardingportal.bunnabanksc.com/ ) አማካኝነት ሙሉ የባንክ ሂሳብ የመክፈት ሂደትን ከጅምሩ እስከመጨረሻው (End to End) ማከናወን ይችላሉ። የአገልግሎት አውቶሜሽን (Service Automation) ፡ ከሂሳብ መክፈት ባሻገር የዚህ አገልግሎት ትልቁ ፋይዳ ተጠቃሚዎች የኤቲኤም ካርድ ለማዘዝ፣ የሞባይል ባንኪንግ ለማስጀመር እና ከባንኩ ባለሙያዎች ጋር ቀጠሮ ለመያዝ በዲጂታል መንገድ ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ። አቅጣጫ ጠቋሚ (Geolocation Tools) ፡ ቅርንጫፎችን፣ ኤቲኤምና (ATM) አይቲኤሞችን (ITM)እንዲሁም የባንኩ የክፍያ አማራጭ ያለባቸውን የንግድ ቦታዎች ለማግኘት የሚያስችል የካርታ (Map) ትስስርን ያካተተ ነው። የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ትስስር (Fayda ID Integration) ፡ ከብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ስርዓት ጋር በቅጽበት በመገናኘት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎችን (NBE directives) በጠበቀ መልኩ የደንበኞችን ማንነት ማረጋገጥ (KYC) ያስችላል። የቡና ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙሉጌታ ዓለማየሁ በጉዳዩ ላይ እንደገለጹት፤ የቡና ባንክ  ዲጂታል ስትራቴጂ ከአገር-አቀፉ የዲጂታል ኢኮኖሚ ጋር የተናበበ መሆኑን ተናግረው በዚህ የዲጂታል ኦንቦርዲንግ አገልግሎት የባንክ አገልግሎትን ለማግኘት እንቅፋት የሆኑትን ጂኦግራፊያዊ እና ሎጂስቲካዊ ገደቦችን ማስቀረት መቻሉን ተናግረዋል። “ይህ አማራጭ የአሰራር መጓተትን በከፍተኛ ደረጃ ከመቀነሱም በላይ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘውን ሀገራዊ የፋይናንስ አካታችነት (Financial Inclusion) ግብ የሚደግፍና እንደ ፋይዳ ካሉ ሀገራዊ የዲጂታል መሰረተ ልማቶች ጋር ለማስተሳሰር፣ የደንበኞችን ማንነት በቅጽበት ማረጋገጥ እና መመዝገብ የሚያስችልም ጭምር ነው” ብለዋል፡፡ የአገልግሎት ስርዓቱ ለህዝብ ክፍት ከመደረጉ በፊት የቅርንጫፍ ሰራተኞች የተሟላ ስልጠና የወሰዱ ሲሆን፣ የመረጃ ታማኝነትን እና ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ጠንካራ የሳይበር ደህንነት (Cybersecurity) ማዕቀፍ ተዘርግቷል። ስርዓቱ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የደንበኞች ፍሰት ለማስተናገድ እና ጥብቅ የሆነ የመረጃ ግላዊነት ስታንዳርዶችን ለመጠበቅ በሚያስችል መንገድ ታስቦ የተነደፈ ነው። ይህ የዲጂታል ደንበኞች ምዝገባ ስርዓት ከሰኞ ሚያዝያ 26፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለህዝብ ክፍት ሆኖ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። # # # ስለ ቡና ባንክ፡- በ2001 ዓ.ም የተመሰረተው ቡና ባንክ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ግንባር ቀደም የግል የንግድ ባንኮች አንዱ ነው። ባንኩ 449 ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን፣ አሁን ላይ የ “Vision 2030” ስትራቴጂውን በመተግበር በዲጂታል ፈጠራ እና በእሴት ፍሰት (Value Stream) ላይ በተመሰረተ አሰራር በዘርፉ ቀዳሚ የፋይናንስ ተቋም ለመሆን እየሰራ ይገኛል። ለተጨማሪ መረጃ፡- ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽንስ ዳይሬክቶሬት ቡና ባንክ- የባለራዕዮች ባንክ ስልክ ቁጥር፡-251911403884

ቡና ባንክ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሳለጥ የሚያስችል ለደንበኞች ምቹ የሆነ የዲጂታል ኦንቦርዲንግ ስርዓት ይፋ አደረገ፡፡ Read More »

ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለፀሎተ ሀሙስ በሰላም አደረሳችሁ፡፡

ለበዓል ከዉጪ ሀገር የተላከሎትን ገንዘብ በባንካችን ይመንዝሩ፤ ጠቀም ያለ ጉርሻ ያግኙ!! ቡና ባንክ- የባለራዕዮች ባንክ BunnaBank #Chrstianity #Orthodox #Holiday #Foryou #Forex #Bonus

ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለፀሎተ ሀሙስ በሰላም አደረሳችሁ፡፡ Read More »

እየመጣን ነው 🚀

የላቀ የዲጂታል ተሞክሮን ከቀልጣፋ አገልግሎት ጋር አጣምረን ይዘንልዎ እየመጣን ነው። በጣትዎ ጫፍ የሚዘወር፣ የባንክ አገልግሎትን መልክ የሚቀይር፤ አዲስ ብስራት፣ ልዩ ነገር… ይዘን ከች ልንል ከደጃፍዎ ደርሰናል! ዝግጁ ነዎት? በቅርብ ቀን ይጠብቁን! ቡና ባንክ- የባለራዕዮች ባንክ #Bunnabank #ComingSoon #StayTuned #SomethingNew #BigUpdate  #SmartBanking #DigitalBanking

እየመጣን ነው 🚀 Read More »

በቅርብ ቀን!

የጊዜን ዋጋ ያከበረ፣ ምቾትዎን ወደ አዲስ ከፍታ የሚያሸጋግር የዲጂታል ሽግግር! 🚀 የባንክ አጠቃቀም ልምድዎን በዘመናዊ ጥበብ የሚቀይር ድንቅ ፈጠራ ይዘን በቅርብ ቀን እንመጣለን። ይጠብቁን፤ #ቡናባንክ #የዲጂታል_አብዮት #ዘመናዊነት #በቅርብ_ቀን #BunnaBank #FinTech #Innovationk

በቅርብ ቀን! Read More »

የባንክ ሒሳብዎን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር አስተሳስረዋል?

ውድ የባንካችን ደንበኞች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባስቀመጠው መመርያ መሠረት ሁሉም ደንበኞች የባንክ አገልግሎት ለማግኘት የፋይዳ ቁጥራቸውን ከባንክ ሒሳብ ቁጥር ጋር እስከ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ማጣመር እንዳለባቸዉ ተገልጿል። በመሆኑም ማፈንጠሪያዉን በመጫን https://verifayda.bunnabanksc.com የቡና ባንክ ሒሳብዎን በቀላሉ ከቤትዎ ሆነዉ እንዲያስተሳስሩ ወይም አቅራቢያዎት ወደሚገኝ ቅርንጫፍ በመሔድ እንዲያስተሳስሩ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ ለበለጠ መረጃ ወደ ጥሪ ማዕከላችን 8501 ይደዉሉ፡፡ ቡና ባንክ- የባለራዕዮች ባንክ

የባንክ ሒሳብዎን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር አስተሳስረዋል? Read More »

ዒድ ሙባረክ! 🌙

እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ቡና ባንክ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለታላቁ የዒድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ ልባዊ ምኞቱን ይገልጻል። በዓሉ “ሙባረክ ወመይሙን” የሆነ የሰላም፣ የፍቅር እና የደስታ እንዲሆንላችሁ፤ እንዲሁም ከቤተሰብ እና ከወዳጅ ዘመዶቻችሁ ጋር በበረካ የተሞላ የደስታ ጊዜ እንድታሳልፉ ከልብ እንመኛለን። ዒድ ሙባረክ! መልካም በዓል! ኻዲም ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት #EidMubarak #EidAlFitr1447 #BunnaBank #Khadim #InterestFreeBanking #Ethiopia #ዒድ_ሙባረክ #ቡና_ባንክ #የተባረከ_በዓል

ዒድ ሙባረክ! 🌙 Read More »

This will close in 0 seconds

Open Your Bank Account Today!

አካውንት ይክፈቱ የክፍያ ካርድዎን ያዝዙ ፣ ፈጣን አገልግሎት ማግኘት ይጀምሩ! ዛሬውኑ ይቀላቀሉን!

Open Bunna Account

You cannot copy content of this page