Bunna Bank

Uncategorized

ቡና ባንክ የደንበኞች ግንኙነቱን የሚያጠናክር የረመዳን የኢፍጣር መርሃ ግብር አካሄደ

ቡና ባንክ ከደንበኞቹ ጋር ያለውን ትስስር ይበልጥ ለማጥበቅ ያለመ ልዩ የረመዳን የኢፍጣር መርሃ ግብር ረቡዕ የካቲት 25 ቀን 2018 ዓ.ም በሀይሌ ግራንድ ሆቴል በድምቀት አከናወነ። በዚህ ልዩ መርሃ ግብር ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማ ጉባዔ ጽ/ቤት ኃላፊ ሸህ ሙሐመድ-ዘይን ዘህረዲንን ጨምሮ ሌሎች የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ አመራሮች፣ የባንኩ ደንበኞች፣ እንዲሁም የተለያዩ አጋር አካላት ተገኝተው የኢፍጣር የአብሮነት ጊዜን በጋራ አሳልፈዋል። በዚህም የባንኩ ኻዲም ከወለድ ነጻ አገልግሎት የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ አባላትን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከተጋባዦቹ ጋር ተገናኝተው የጋራ ቆይታ አድርገዋል። ይህ መድረክ አመራሩ ከደንበኞችና ከኃይማኖት አባቶች ጋር የጠበቀ ትስስር እንዲፈጥር፣ ፍላጎቶቻቸውን በቅርበት እንዲረዳና ተቋሙ ከፋይናንስ አገልግሎት ባለፈ ያለውን አጋርነት እንዲያረጋግጥ ምቹ አጋጣሚን ፈጥሯል። የቡና ባንክ ቺፍ ሪቴልና ቅርንጫፍ ባንኪንግ ኦፊሰር አቶ እስክንድር ዲበኩሉ በዝግጅቱ ላይ ባስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት እንዳስታወቁት፤ ቡና ባንክ በቅርቡ ባደረገው የሥትራቴጂ ክለሳ ለኻዲም ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ትልቅ ትኩረት እንደተሰጠው አንስተዋል። ባንኩ በዚህ ረገድ የደንበኞቹን ፍላጎት ለማርካት ሰፊ ስራዎችን እየሰራ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡ መርሃ ግብሩ የረመዳንን ወር እሴቶች ከማክበር ባለፈ በባንኩ አገልግሎት ተደራሽነት፣ በቀጣይ በሚኖራቸው የስራ ግንኙነት ዙሪያ ከአመራሩ ጋር ሀሳብ ለመለዋወጥ ዕድልን የፈጠረ ነበር። በዚህም በዝግጅቱ የታደሙት የእስልምና ጉዳዮች አመራሮችና ደንበኞች ባንኩ ላሳየው ተነሳሽነት ምስጋናቸውን አቅርበው፣ እንዲህ ያለው የፊት ለፊት ግንኙነት መተማመንን ለመገንባትና ባንኩ በቀጣይ ለሚቀርጻቸው ስራዎች ጠቃሚ ግብዓቶችን ለማግኘት የራሱን ሚና እንደሚጫወት ጠቅሰው ባንኩ በኻዲም ከወለድ ነጻ አገልግሎት በኩል የጀመረውን ስራ ከዚህ የበለጠ አጠናክሮ እንዲቀጥል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በመጨረሻም መርሃ ግብሩ በኢፍጣር ማዕድ መጋራትና በጋራ የምስጋናና ጸሎት ስነ-ስርዓት የተጠናቀቀ ሲሆን፣ የኢፍጣር ዝግጅቱ ቡና ባንክ አካታችነትንና ቀጥተኛ ተሳትፎን ቅድሚያ በመስጠት ለደንበኞቹ እሴቶች ያለውን አክብሮትና ለአብሮነት ልዩ ትኩረት የሚሰጥ ተቋም መሆኑን ያሳየበት አንዱ መድረክ ሆኖ አልፏል።   Bunna Bank Hosts Grand Ramadan Iftar to Strengthen Customer Relations and Community Ties Bunna Bank hosted a prestigious Ramadan Iftar program on Wednesday, March 4, 2026, at the Haile Grand Hotel, aimed at deepening its connection with customers and the wider community. The event was graced by high-profile guests, including Sheikh Mohammed-Zayn Zohreddin, Head of the Ulama Council Office of the Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council, along with other senior religious leaders, valued customers, and key stakeholders. Strategic Engagement and Leadership Presence Senior executives of the Bank and members of the Interest-Free Banking (IFB) Sharia Advisory Board joined the guests, creating a unique opportunity for direct engagement. This platform allowed the Bank’s leadership to foster closer ties with religious figures and customers, ensuring the institution remains responsive to the community’s needs beyond traditional financial services. Focus on “Khidmah” Interest-Free Services During the event, Ato Eskinder Dibekulu, Chief Retail and Branch Banking Officer, delivered a welcoming message highlighting the Bank’s recent strategic revision. He emphasized that Khadim Interest-Free Banking has been identified as a top priority within the new strategy, and the Bank is aggressively working to enhance its services to satisfy the growing demands of its clients. Collaborative Dialogue and Positive Feedback The program went beyond a ceremonial gathering, serving as a forum for constructive dialogue regarding service accessibility and future business relations. Guests and religious leaders commended Bunna Bank for its proactive approach, noting that such face-to-face interactions are vital for building lasting trust. They further encouraged the Bank to continue strengthening its dedicated Interest-Free service, known as “Khadim.” The evening concluded with a shared Iftar meal and a collective prayer for peace and gratitude. The event successfully demonstrated Bunna Bank’s commitment to inclusivity and its deep respect for the values and traditions of its customers, reinforcing its standing as a customer-centric and community-focused financial institution.

ቡና ባንክ የደንበኞች ግንኙነቱን የሚያጠናክር የረመዳን የኢፍጣር መርሃ ግብር አካሄደ Read More »

እንኳን ለካራማራ ድል መታሰቢያ ቀን አደረሳችሁ!

የካቲት 26/1970 ዓ/ም የሱማሊያን ዚያድባሬ ጦር ለመመከት በካራማራ ጀግኖች የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች የህይወት መሰዋዕትነት ከፍለው ወራሪውን ጦር ከሀገር ያባረሩበት እና የሀገራቸውን ሰንደቅ ያውለበለቡበት ቀን ነው። እንኳን አደረሳችሁ ቡና ባንክ- የባለራዕዮች ባንክ #BunnaBank #Karamara #Ethiopia

እንኳን ለካራማራ ድል መታሰቢያ ቀን አደረሳችሁ! Read More »

የቡና ባንክ መገለጫ

ቡና ባንክ እ.ኤ.አ. በ2009 ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተሰጠው ፈቃድ የተመሠረተ የግል ባንክ ነው። ባንካችን ፈጣን ዕድገት በማስመዝገብ በአገሪቱ ውስጥ ካሉ ጠንካራ የግል ባንኮች አንዱ ለመሆን በቅቷል። ከ5.1 ቢሊዮን ብር በላይ የተከፈለ ካፒታል እና ከ14,000 በላይ ባለአክሲዮኖች ያሉት ባንካችን፣ ለባለራዕይ ደንበኞቻችን ስኬት ፈጠራ የታከለባቸው የፋይናንስ መፍትሄዎችን በማቅረብ ታማኝ አጋር ለመሆን ቁርጠኛ ነው። ለላቀ ውጤት እንተጋለን – ደንበኞቻችንን የእሴቶቻችን ማዕከል በማድረግ፣ በላቀ የሙያ ብቃትና እንክብካቤ እናገለግላቸዋለን። ከ4,000,000 በላይ ደንበኞች ያሉትና ቁጥሩም በየጊዜው እየጨመረ የመጣው ባንካችን፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ሕዝብን መሠረት ካደረጉ የግል ባንኮች በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው። ራዕያችን እ.ኤ.አ. በ2030 በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ቀዳሚ ሶስት የፋይናንስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አንዱ መሆን ነው። ተልዕኮአችን ከአጋሮቻችን ጋር በመተባበር ዘመኑን የዋጀ የፋይናንስ አገልግሎት መስጠት፣ ለዋና ዋና ባለድርሻ አካላት የሚሰጠውን እሴት ከፍ ማድረግ እና የሕዝብን አመኔታ ማትረፍ ሲሆን ይህንን ግብ በተወዳጁ የቡና መገለጫችን፣ በዲጂታል እውቀት በበለፀጉ ባለሙያዎቻችን እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች በመደራጀት ለማሳካት ቁርጠኞች ነን። መሠረታዊ እሴቶቻችን 01 አሸናፊነት (WINNING) ለላቀ ደረጃ በመትጋት እና ከፍተኛ የሙያ ብቃትን በተግባር በማዋል፣ በዘርፉ ውስጥ ያለውን ውድድር በሙያዊ ስነ-ምግባር ታጅበን እንደምናሸንፍ ፅኑ እምነት አለን። 02 መከባበር (RESPECT) ለእያንዳንዳችን የልዩነት እሴት፣ ለደንበኞቻችን፣ ለባለአክሲዮኖቻችን፣ ለራሳችን፣ ለአቅራቢዎቻችን እና ለማህበረሰባችን የምናበረክተውን አስተዋጽኦ እናከብራለን። እያንዳንዱ ባለድርሻ አካል አስፈላጊ መሆኑን እና የራሱ ሚና እንዳለው እንገነዘባለን። 03 ኃላፊነት (RESPONSIBILITY) የባለድርሻ አካላቶቻችንን ፍላጎት በተገቢው መጠን ለማሟላት በኃላፊነት ስሜት እንሠራለን። 04 ትብብር (COLLABORATION) ደንበኞቻችንን፣ ባለአክሲዮኖቻችንን፣ ተቆጣጣሪ አካላትን እና ማህበረሰቡን ስናገለግል መደጋገፍ፣ መተባበር እና መተሳሰብ ላይ ትኩረት እናደርጋለን። 05 ፈጠራ (INNOVATION) የወደፊቱን ጊዜ አስቀድሞ ለመቅረጽ አዳዲስና ቀዳሚ የሆኑ የፈጠራ ሃሳቦችን ያለማቋረጥ እንከተላለን።

የቡና ባንክ መገለጫ Read More »

የነዳጅ ግብይትዎን በቡና ባንክ ይፈፅሙ!!

የነዳጅ ክፍያዎን በቡና ባንክ አቦል ሞባይል ባንኪንግ በመጠቀም ይክፈሉ፡፡ ቀላል እና ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት ያገኛሉ፡፡ 👉🏿ያለ ኢንተርኔት *820# በመጠቀም ከነዳጅ ማደያዉ በሚደርስዎት የማረጋገጫ መልዕክት በመጠቀም፣ 👉🏿ቡና ባንክ አቦል ሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ዉስጥ በመግባት ከነዳጅ ማደያዉ የሚሰጥዎትን የማጣቀሻ ቁጥር በመጠቀም ወይም 👉🏿QR ኮድ ስካን በማድረግ በቀላሉ ክፍያ መፈጸም ይችላሉ፡፡ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ከባንካችን ጋር በሚሰሩ የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች በመጠቀም ክፍያዎትን በቡና በቡና ባንክ ይክፈሉ፡፡ በአዲስ አበባ ቃሊቲ ካፍደም ፕላዛ አካባቢ በሚገኘዉ ኦላ ኢነርጂ፤ ቀበና አካባቢ በሚገኘዉ ኦላ ኢነርጂ፤ ደምበል አካባቢ በሚገኘዉ ኦላ ኢነርጂ፤ ጀርመን አካባቢ በሚገኘዉ የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም፤ ቃሊቲ ገብርኤል ቤ/ክርስትያን አካባቢ በሚገኘዉ የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም፤ ጀሞ መስታወት ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘዉ ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ፤ ሰሚት ጎሮ አይሲቲ ፓርክ አካባቢ በሚገኘዉ ስካይ ፔትሮሊየም፤ ወ.ዘ.ተ በሚገኙ የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች ነዳጅ ሲቀዱ ክፍያዎትን በቡና ባንክ ይፈጽሙ፡፡ ለበለጠ መረጃ ወደ ጥሪ ማእከላችን 8501 ይደዉሉ ወይም አቅራቢያዎት ወደሚገኝ የባንካችን ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡ ቡና ባንክ- የባለራዕዮች ባንክ #BunnaBank #FuelPayment #Abol #DigitalPayment #Easy #SecureBanking

የነዳጅ ግብይትዎን በቡና ባንክ ይፈፅሙ!! Read More »

የባንክ ሒሳብ ቁጥርዎን ከብሔራዊ መታወቂያ ቁጥርዎ (ፋይዳ) ጋር ያስተሳስሩ!

https://verifayda.bunnabanksc.com የባንክ ሒሳብ ቁጥርዎን ከብሔራዊ መታወቂያ ቁጥርዎ (ፋይዳ) ጋር ያስተሳስሩ! 📲 ለተጨማሪ መረጃ ወደ ባንካችን ነፃ የጥሪ ማዕከል 8501 ይደውሉ። ቡና ባንክ የባለራዕዮች ባንክ #bunnabank #fyda #link #account #nationalID #bunnafayda #fydanumber

የባንክ ሒሳብ ቁጥርዎን ከብሔራዊ መታወቂያ ቁጥርዎ (ፋይዳ) ጋር ያስተሳስሩ! Read More »

🌙 Ramadan Mubarak from Bunna Bank 🌙

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለታላቁ እና የተቀደሰው 1447ኛው የረመዷን ጾም በሰላም አደረሳችሁ። ፆሙ የሰላምና የደስታ ይሆንላችሁ ዘንድ ቡና ባንክ ይመኛል። 🙏✨ Special Ramadan Offer – 4% Extra Bonus! ውድ የቡና ቤተሰቦች፣ በረመዷን ወቅት ከውጭ ሀገር ወዳጅ ዘመድ በሀዋላ አስተላላፊ ወኪሎች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በባንካችን ሲቀበሉ እንዲሁም የውጭ አገር ገንዘብ ሲመነዝሩ ከእለታዊ የመግዣ ተመን ላይ 4% ተጨማሪ ጉርሻ ያገኛሉ። Visit your nearest Bunna Bank branch today! 💡 Bunna Bank – የባለራዕዮች ባንክ! #RamadanMubarak #BunnaBank #SpecialOffer #RemittanceBonus #BankingForYou #TrustedBank #ረመዳንሙባረክ #ቡናባንክ #ልዩእቅድ #ጉርሻ4% #የባለራዕዮችባንክ #ታማኝ_ባንክ

🌙 Ramadan Mubarak from Bunna Bank 🌙 Read More »

መልካም የአብይ ጾም!

✝️ ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለአብይ ፆም በሰላም አደረሳችሁ! ዘወረደ ብለን ጀምረን ለብርሀነ ትንሳኤዉ በሰላም እንድንደርስ ቡና ባንክ ምኞቱን ይገልፃል፡፡ ቡና ባንክ- የባለራዕዮች ባንክ #Bunnabank #Banking #ForYou #Visionaries #Ethiopian, #Ortodox, #Peace_Full_Time

መልካም የአብይ ጾም! Read More »

🚀 Stay ahead with real-time financial insights and updates!

Join our official Telegram channel @BunnaBankOfficial and experience seamless financial connectivity, instant updates, exclusive offers, and smart banking tips—all in one place. Be part of a growing digital community where convenience meets innovation, and your financial journey becomes faster, smarter, and more connected than ever. 👉 Join now and transform the way you bank. #DigitalBanking #TelegramChannel #FinancialServices #SmartBanking #MobileBanking #FinTech #OnlineBanking #BankingInnovation #EthiopiaBanking #CustomerExperience #FinancialUpdates #SecureBanking #DigitalFinance #BunnaBank #FinancialCommunity

🚀 Stay ahead with real-time financial insights and updates! Read More »

የባንክ ሒሳብ ቁጥርዎን ከብሔራዊ መታወቂያ ቁጥርዎ (ፋይዳ) ጋር ያስተሳስሩ!

https://verifayda.bunnabanksc.com የባንክ ሒሳብ ቁጥርዎን ከብሔራዊ መታወቂያ ቁጥርዎ (ፋይዳ) ጋር ያስተሳስሩ! 📲 ለተጨማሪ መረጃ ወደ ባንካችን ነፃ የጥሪ ማዕከል 8501 ይደውሉ። ቡና ባንክ የባለራዕዮች ባንክ #bunnabank #fyda #link #account #nationalID #bunnafayda #fydanumber

የባንክ ሒሳብ ቁጥርዎን ከብሔራዊ መታወቂያ ቁጥርዎ (ፋይዳ) ጋር ያስተሳስሩ! Read More »

This will close in 0 seconds

Open Your Bank Account Today!

አካውንት ይክፈቱ የክፍያ ካርድዎን ያዝዙ ፣ ፈጣን አገልግሎት ማግኘት ይጀምሩ! ዛሬውኑ ይቀላቀሉን!

Open Bunna Account

You cannot copy content of this page